Uploaded by yohannes5kebede

Geez Amharic Dictionary - Geez

advertisement
ሀለወ
ሀለወ (ግስ) ⑴ ኖረ፤ ⑵ አለ፤ ⑶ ነበረ፤ ወሀሎ አሐዱ ብእሲ።
አንድ ሰው ነበረ። [ሀለወ]
ሃ (ምዕላ.) ⑴ - ን።፤ ሳሙኤልሃ. . . ሳሙኤልን. . . ዳንኤልሃ. .
. ዳንኤልን. . .፤ ⑵ (የተሳቢ ምልክት፤ ከተጽውኦ ስም ጋራ ብቻ
ጥቅም ላይ የሚውል።) [ሃ]
ህየ (ተ.ግ.) እዚያ፥ በዚያ፤ ወበይእቲ ሌሊት ተንሥኡ ዮሴፍ
ወማርያም ምስለ ውእቱ ሕፃን ወሰሎሜ ወሖሩ ኀበ ምድረ ግብፅ
ወነበሩ ህየ እስከ አመ ሞተ ሄሮድስ። በዚያች ሌሊት ዮሴፍ እና
ማርያም ከሕፃኑ እና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብፅ አገር ሄዱ፣ በዚያም
ሄሮዱስ እስከ የሚሞት ድረስ ኖሩ። [ህየ]
ለምንት (ስም) ለምን፤ ለምንት ሖርኪ አንቲ ኀበ ቤተ መጻሕፍት?
አንቺ ለምን ወደ ቤተ መጻሕፍት ሄድሽ? [ለምንት]
ለበሰ (ግስ) በቁሙ።፤ ወከዋክብትኒ ወደቁ፣ ዲበ ምድር፣ ወፀሐይ
ጸለመ፣ ወወርኅ ለበሰት ደም አመ ተሰቀለ ክርስቶስ። 25.
ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ኮከቦች ምድር ላይ ወደቁ፣ ፀሐይ
ጨለመ፣ ጨረቃም ደም ለበሰች። [ለበሰ]
ላዕለ (መስተዋ.) ላይ፤ ሳምራዊት ኖመት ላዕለ ዐራት። ሳምራዊት
አልጋ ላይ ተኛች። [ላዕል]
ላዕል = ላዕለ [ላዕል]
ሎቱ (ተው. ስ.) ⑴ - ለት፤ ወመጽኡ ሠለስቱ ነገሥት ኀበ ሕፃን
እምብሔር ርሑቅ ወሰገዱ ሎቱ ወአምጽኡ ሎቱ መባእ። ሦስት
ነገሥታት ከሩቅ አገር ወደ ሕፃኑ መጡና ሰገዱለት እንዲሁም
ስጦታም አመጡለት።፤ ⑵ እሱን፥ ለእሱ፥ እሱ [ሎቱ]
ሐመ (ግስ) ታመመ፤ ዘይሰቲ ወይነ ብዙኅ ይስከር ወየሐምም።
ወይን ብዙ የሚጠጣ ይሰክር እና ይታመማል። [ሐመ]
ሐመድ (ስም) አመድ፤ ወጸላእቱሂ ሐመደ ይቀምሑ። ጠላቶችሽ
አመድ (አፈር) ይቅማሉ። [ሐመድ]
ሐሠር (ስም) ጉድፍ፥ ገለባ፥ አሰር፤ ርኢከ ሐሠረ ዘውስተ ዐይነ
እኁከ። በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ተመለከትክ።
[ሐሠር]
ሐሤት (ስም) ደስታ [ሐሠየ*]
ሐራ (ስም) ⑴ ወታደር፤ አኮ ሐራ አቡአ። አባቷ ወታደር
አይደለም።፤ ⑵ ጭፍራ፥ ተከታይ፥ (ነጠላም ብዙም ሐራ
ይባላል)፤ እልኩ ሐራ ቀተሉ አንበሳ ገዳም። እነዚ ወታደሮች የዱር
አንበሳ ገደሉ። ሐራ ኢትዮጵያ ኃያላን እሙንቱ። የኢትዮጵያ
ወታደሮች ኃይለኛ ናቸው። [ሐራ]
ሐቅል (ስም) ዱር፥ ሜዳ፥ ውድማ፤ አውፅኡ አፍራሶም ኀበ
ሐቅል። ፈረሶቻቸውን ወደ ሜዳ አወጡ። [ሐቅል]
ሐዘነ (ግስ) አዘነ፤ ሐዘኑ ሐዋርያት አመ ተሰቅለ ክርስቶስ።
ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ሐዋርያት አዘኑ። [ሐዘነ]
ሕልም (ስም) እልም፥ ሕልም፤ ዳንኤል ሰምዐ ቃለ እግዚአብሔር
በሕልሙ። ዳንኤል በሕልሙ የእግዚአብሔርን ቃል ሰማ። [ሐለመ]
ሖረ (ግስ) ሄደ፤ ሖረት ኀበ ኢየሩሳሌም ማርያም። ማርያም ወደ
ኢየሩሳሌም ሄደች። አነ ሖርኩ ኀበ ደብረ ሊባኖስ። እኔ ወደ ደብረ
ሊባኖስ ሄድኩ። [ሖረ]
መሀረ (ግስ) አስተማረ፤ አቡነ ሰላማ መሀረ ሃይማኖተ ክርስቶስ
በምድረ ኢትዮጵያ። አቡነ ሰላማ በኢትዮጵያ አገር የክርስቶስን
ግእዝ ዐማርኛ መዝገበ ቃላት በብሩክ በየነ
ሤጠ
ሃይማኖት አስተማሩ። (ማስታወሻ፦ በዐማርኛ እንጂ በግእዝ አንቱታ
እንደሌለ ልብ ማለት ያስፈልጋል።) [መሀረ]
መምህር (ስም) በቁሙ።፤ እስክንድር መምህር። እስክንድር
መምህር ነው። እስከንድር መምህር ውእቱ። እስክንድር መምህር
ነው። [መሀረ]
መስቀል (ስም) በቁሙ።፤ ወባሕቱ መጽኡ ኅቤሁ በዕለተ ዓርብ
ወሰቀልዎ ዲበ ዕፀ መስቀል። ነገር ግን በዕለተ ዓርብ ወደ እርሱ ዘንድ
መጡ እና በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉት። [ሰቀለ]
መባእ (ስም) እጅ መንሻ፥ ገጸ በረከት፥ ስጦታ፤ ወመጽኡ
ሠለስቱ ነገሥት ኀበ ሕፃን እምብሔር ርሑቅ ወሰገዱ ሎቱ ወአምጽኡ
ሎቱ መባእ። ሦስት ነገሥታት ከሩቅ አገር ወደ ሕፃኑ መጡና
ሰገዱለት እንዲሁም ስጦታም አመጡለት። [መባእ]
መኑ (ስም) ማን፤ መኑ ሖረ ኀበ አሜሪካ? ወደ አሜሪካ የሄደው
ማን ነው? [መኑ]
መካን (ስም) ቦታ፥ ስፍራ፥ አካባቢ [መካን]
መዋዕል (ስም) ዘመን፥ ክፍለ ዘመን፥ ጊዜ፤ ተሰቅለ በላይ ዘለቀ
በመዋዕለ ዓፄ ኀይለ ሥላሴ። በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በላይ ዘለቀ
ተሰቀለ። [መዋዕል]
መዝሙር (ስም) በቁሙ።፤ መዝሙረ ዳዊት = መዝሙረ ዳዊት
(የዳዊት መዝሙር)። [ዘመረ]
መጽአ (ግስ) መጣ፤ መጽኡ ሰብአ ሰገል እምብሔር ርሑቅ። ሰብአ
ሰገል ከሩቅ አገር መጡ። [መጽአ]
ምሥያጥ (ስም) ገበያ፥ መደብር፥ መርካቶ፥ የገበያ ቦታ፥ ሱቅ፤
ውሉድኪ ሖሩ ኀበ ምሥያጥ። ልጆችሽ ወደ ገበያ ሄዱ። [ሤጠ]
ምስለ (መስተዋ.) ጋራ፥ ጋር፥ ከ. . . ጋር፤ ሕፃኑ ኢየሱስ ሖረ
ኀበ ምድረ ግብፅ ምስለ ዮሴፍ ወማርያም። ሕፃኑ ኢየሱስ ወደ ግብፅ
አገር ከዮሴፍ እና ከማርያም ጋር ሄደ። [ምስለ]
ምንት (ስም) ምን፤ አንትን ምንት ሰረቅክን? እናንተ (ሴቶች) ምን
ሰረቃችሁ? [ምንት]
ምንትኒ (ስም) አንዳችም፤ ንሕነ ምንትኒ ኢሰረቅነ። እኛ
አንዳችም (ነገር ) አልሰረቅንም።
ምድር (ስም) አገር፥ ምድር፤ ዮሴፍ ወኢየሱስ ሖሩ ኀበ ምድረ
ግብፅ ምስለ ማርያም ወሰሎሜ። ዮሴፍ እና ኢየሱስ ወደ ግብፅ አገር
ከማርያም እና ከሰሎሜ ጋር ሄዱ። [ምድር]
ምድረ አሜሪካ (ስም) አሜሪካ አገር
ምድረ ኢትዮጵያ (ስም) ኢትዮጵያ አገር
ምድረ ግብፅ (ስም) ግብፅ አገር
ሞተ (ግስ) ሞተ፤ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ሞተ
ወተቀብረ በመቅደላ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ በመቅደላ
ሞቶ ተቀበረ። [ሞተ]
ሠለስቱ (ስም) ሦስት፤ ወመጽኡ ሠለስቱ ነገሥት ኀበ ሕፃን
እምብሔር ርሑቅ ወሰገዱ ሎቱ ወአምጽኡ ሎቱ መባእ። ሦስት
ነገሥታት ከሩቅ አገር ወደ ሕፃኑ መጡና ሰገዱለት እንዲሁም
ስጦታም አመጡለት። [ሠለሰ]
ሠናያት (ብዙ ቊ., ቅ.) ቆንጆዎች፥ መልካሞች፥ ጥሩዎች፥
ደጎች፤ አይዳ ወሠሚራ ሠናይት እማንቱ። አይዳ እና ሠሚራ
ቆንጆዎች ናቸው። [ሠነየ]
ሤመ (ግስ) ሾመ [ሾመ]
ሤጠ (ግስ) ሸጠ፤ ከበደ ሤጠ ቤቱሃ። ከበደ ቤቱን ሸጠ። [ሤጠ]
ገጽ 1
ረከበ
ተሰቅለ
ረከበ (ግስ) አገኘ፤ ዝብእሲ ሖረ ኀበ ምሥያጥ ወረከበ ህየ ዛቲ
ሠናይት ወለት። ይህ ሰው ወደ ገበያ ሄደና እዚያ ይህችን ቆንጆ ልጅ
አገኘ። [ረከበ]
ራእይ (ስም) በቁሙ። [ርእየ]
ርሑቅ (ቅ.) ሩቅ፤ ወመጽኡ ሠለስቱ ነገሥት ኀበ ሕፃን እምብሔር
ርሑቅ ወሰገዱ ሎቱ ወአምጽኡ ሎቱ መባእ። ሦስት ነገሥታት ከሩቅ
አገር ወደ ሕፃኑ መጡና ሰገዱለት እንዲሁም ስጦታም አመጡለት።
ቀደመ (ግስ) በቁሙ። [ቀደመ]
ቀደምት (ቅ.) የቀድሞ ሰዎች፤
ሰማዕክሙ ዘተባህለ
ለቀደምትክሙ። ከእናንተ ለሚቀድሙት (ለአባቶቻችሁ) የተባለውን
ነገር ስሙ። ቀደምትክሙ ሰገዱ ለእግዚአብሔር አምላኮሙ።
አባቶቻችሁ ለእግዚኣብሔር አምላካቸው ሰገዱ። [ቀደመ]
ቀዳሚ (ተ.ግ.) መጀመሪያ፤ በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ
ወምድር። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ።
[ርሕቀ]
[ቀደመ]
ርሕቀ (ግስ) ራቀ [ርሕቀ]
ርእየ (ግስ) ዐየ፥ ተመለከተ፤ ወሶበ ርእየ እግዚእ ኢየሱስ ብዙኃነ
ሰብአ ዘተለውዎ አዘዘ ይሑሩ ማኦዶተ ባሕር። ብዙዎች
እንደተከተሉት ጌታ እየሱስ ባየ ጊዜ በባሕር ላይ እንዲሄዱ
አዘዛቸው። [ርእየ]
ሰ (ምዕላ.) ግን፤ ያዕቆብሰ. . . ያዕቆብ ግን. . . አስቴር አፍቀረት
ሰሎሞንሃ። ወሰሎሞንሰ አፍቀረ ማርያማዊትሃ። አስቴር ሰሎሞንን
አፈቀረች። ሰሎሞን ግን ማርያማዊትን አፈቀረ። [ሰ]
ሰምዐ (ግስ) ሰማ፥ አዳመጠ፤ ሙሴ ሰምዐ ቃለ እግዚአብሔር
በሕልሙ። ሙሴ በሕልሙ የእግዚአብሔርን ቃል ሰማ። [ሰምዐ]
ሰረቀ (ግስ) ሰረቀ፥ ዘረፈ፤ መኑ ሰረቀ አልባሰኪ? ልብሶችሽን
የሰረቀው ማን ነው? [ሰረቀ]
ሰቀለ (ግስ) በቁሙ።፤ ወባሕቱ መጽኡ ኅቤሁ በዕለተ ዓርብ
ወሰቀልዎ ዲበ ዕፀ መስቀል። ነገር ግን በዕለተ ዓርብ ወደ እርሱ ዘንድ
መጡ እና በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉት። ስቅል አልባሲከ ላዕለ
ዕፅ! ልብስህን ዛፉ ላይ ስቀለው! [ሰቀለ]
ሰበከ (ግስ) በቁሙ።፤ ሰበከ አንተ ወንጌለ ክርስቶስ። አንተ
የክርስቶስን ወንጌል ሰበክ። [ሰበከ]
ሰብእ (ብዙ ቊ.) ሰው፥ ሰዎች፥ የ "ብእሲ" ብዙ ቊጥር፤
ወአምጽኡ ሰብእ ኀቤሁ ድውየ መፃጉዐ በዐራት። ወደ እርሱም
ድውያንንና መፃጉዕንን ሰዎች በአልጋ ተሸክመው አመጡ። [ሰብእ]
ሰዐለ (ግስ) ለመነ፥ ጠየቀ፥ ተማፀነ፤ ወለኵሉ ዘሰዐለከ ሀቦ!
የጠየቀኽንም ሁሉ ስጠው! [ሰዐለ]
ሰገደ (ግስ) በቁሙ።፤ መጽኡ ሰብአ ሰገል ኀበ ኢየሩሳሌም
እምብሔር ርሑቅ። ወሖሩ ኀበ ቤተ ልሔም ወሰገዱ ለሕፃን
ዘተወልደ እማርያም ድንግል። ሰብአ ሰገል ከሩቅ አገር ወደ
ኢየሩሳሌም መጡ። ወደ ቤተ ልሔም ሄዱ እና ከድንግል ማርያም
ለተወለደው ሕፃን ሰገዱ። [ሰገደ]
ሰጠጠ (ግስ) ቀደደ፤ ዕፅ ሰጠጠው አልባሳ። ልብሷን እንጨት
ቀደደው። [ሰጠጠ]
ሶበ (ተ.ግ.) በ. . . ጊዜ፥ ጊዜ፥ ያን ጊዜ፥ ሲሆን፥ በዚህ ጊዜ፥
በዚያ ጊዜ፥ ወዲያው፤ ወሰፍሐ እግዚእ ኢየሱስ እዴሁ ኀበ
ዘለምጽ ወይቤሎ ንጻሕ እምለምጽከ፤ ወነጽሐ እመለምጹ በጊዜሃ።
ወሶበ ቦኣ ቅፍርናሆም መጽአ ኅቤሁ መስፍነ ምእት። ጌታ ኢየሱስ
ለምጻሙ ሰው ከለምጽ በሽታህ ንጻ አለው እሱም ወዲያው ከለምጹ
ነጻ፥ ቅፍርናሆም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደሱ መጣ። [ሶበ]
ሶቤ = ሶበ
ቀብረ (ግስ) ቀበረ፤ [ቀብረ]
ቀተለ (ግስ) ገደለ፤ ዝንቱ ብእሲ ቀተለ ከልበ። ይህ ሰው ውሻ
ገደለ። [ቀተለ]
ቀትል (ስም) ግድያ፥ ጦርነት [ቀተለ]
ቅድመ (መስተዋ.) ፊት፥ በፊት፤ ሖርነ ኀበ ኢየሩሳሌም ወቆምነ
ቅድመ ቤተ መቅደስ። ወደ ኢየሩሳሌም ሄድን እና በቤተ መቅደስ
ፊት ቆምን። [ቅድመ]
ቆመ (ግስ) በቁሙ።፤ ለምንት ቆምክን ቅድመ ንጉሥ? ከንጉሥ
ፊት ለምን ቆማችሁ? [ቆመ]
ቆም (ስም) ቁመት [ቆመ]
በልዐ (ግስ) በላ፤ ዝንቱ ብእሲ በልዐ ኅብስተ። ይህ ሰው እንጀራ
በላ። [በልዐ]
በበይናት (ተ.ግ.) እርስ በራስ፥ በመካከል፤
ተፋቀሩ
በበይናቲክሙ። እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ። [በይናት]
በእንተ (ተ.ግ.) ስለ፤ ወአንሰ ሐዘንኩ ጥቀ በእንተ ዝንቱ ነገር። እና
እኔም (ስለ) በዚህ ነገር በጣም አዘንኩ። በእንተ ማርያም! = ስለ
ማርያም! [በእንተ]
ባሕቱ (ተ.ግ.) ግን፥ ነገር ግን፥ ሆኖም ግን፤ አኮ ሠናይት
ብእሲቴ ወባሕቱ ውእቱ ሠናይ ግብራ። የእኔ ሚስት ቆንጆ
አይደለችም ሆኖም ግን ምግባሯ ቆንጆ ነው። [ባሕቱ]
ባሕቲት (ስም) ብቻ፤ ዘበልዐ ባሕቲቶ ይመውት ባሕቲቶ። ብቻ
የሚበላ ብቻውን ይሞታል። ወፃእኩ እምብሔር ርሑቅ ባሕቲትየ።
ብቻየን ከሩቅ አገር መጣሁ። (ወጥቼ መጣሁ/ ወጥቼ ሄድኩ)
ግእዝ ዐማርኛ መዝገበ ቃላት በብሩክ በየነ
[ባሕቲት]
ቤት (ስም) በቁሙ። [ቤት]
ቤተ መቅደስ (ስም) በቁሙ።
ቤተ ምግብ (ስም) ምግብ ቤት
ቤተ ንዋም (ስም) መኝታ ቤት
ቤተ ክርስቲያን (ስም) በቁሙ።
ቤተ መጻሕፍት (ስም) በቁሙ።
ብሔር (ስም) አገር፤ መጽኡ ሰብአ ሰገል ኀበ ኢየሩሳሌም
እምብሔር ርሑቅ። ወሖሩ ኀበ ቤተ ልሔም ወሰገዱ ለሕፃን
ዘተወልደ እማርያም ድንግል። ሰብአ ሰገል ከሩቅ አገር ወደ
ኢየሩሳሌም መጡ። ወደ ቤተ ልሔም ሄዱ እና ከድንግል ማርያም
ለተወለደው ሕፃን ሰገዱ። [ብሔር]
ብእሲ (ስም) ⑴ ሰው፤ ወሀሎ አሐዱ ብእሲ። አንድ ሰው ነበረ።፤
⑵ ባል [ብእሲ]
ብእሲት (ስም) ⑴ ሴት፤ ⑵ ሚስት፤ አኮ ሠናይት ብእሲቴ
ወባሕቱ ውእቱ ሠናይ ግብራ። የእኔ ሚስት ቆንጆ አይደለችም
ሆኖም ግን ምግባሯ ቆንጆ ነው። [ብእሲ]
ቦ (ግስ) አለ፤ ቦ ብእሲ ውስተ ቤትከ። እቤትህ ሰው አለ። [ቦ]
ተሐሠየ (ግስ) ተደሰተ፥ ረካ፤ ወደቂቅ እስራኤል ይትሐሠዩ
በንጉሦሙ። የእስራኤል ልጆች በንጉሣቸው ይደሰታሉ። [ሐሠየ*]
ተሰቅለ (ግስ) ተሰቀለ፤ ጸልመ ፀሐይ አመ ተሰቅል ክርስቶስ።
ገጽ 2
ተቀብረ
ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመች። [ሰቀለ]
ተቀብረ (ግስ) ተቀበረ፤ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ሞተ
ወተቀብረ በመቅደላ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ በመቅደላ
ሞቶ ተቀበረ። [ቀብረ]
ተንሥአ (ግስ) ተነሣ፤ ተንሥአ ክርስቶስ እመቃብር ወዐርገ ውስተ
ሰማይ። ክርስቶስ ከመቃብር ተነሣ እና ወደ ሰማይ ዐረገ። [ነሣ]
ተፈቅረ (ግስ) ተፈቀረ፤
ተፈቅረ ዮሐንስ እምሐዋርያት።
ከሐዋርያት ይበልጥ / ይልቅ ዮሐንስ ተወደደ። [ፈቀረ*]
ኀልቀ (ግስ) አለቀ፥ ተፈጸመ፥ ተጨረሰ፤ ወኢገብአ ቋዕ እስከ
ኅልቀ ማይ እምነ ምድር። ቁራ የመሬት ውኃ እስኪያልቅ ድረስ ገብቶ
ተቀመጠ። [ኀልቀ]
ኀበ (መስተዋ.) ወደ፤ ይእቲ ሖረት ኀበ ኢየሩሳሌም። እሷ ወደ
ኢየሩሳሌም ሄደች። [ኀበ]
ኀብአ (ግስ) ደበቀ [ኀብአ]
ኅብስት (ስም) እንጀራ፥ ዳቦ፥ ምግብ፤ ዝንቱ ብእሲ በልዐ
ኅብስተ። ይህ ሰው እንጀራ በላ። [ኅብስት]
ነበረ (ግስ) ኖረ፥ ተቀመጠ፥ ዐረፈ፤ ብእሲ ጽድቅ ነበረ ላዕለ
መንበር። ጻድቁ ሰው ወንበር ላይ ተቀመጠ። ዝንቱ ብእሲ ነበረ
ውስተ ቤቱ ለባሕቲቱ። ይህ ሰው ለብቻው በቤቱ ውስጥ ይኖር
ነበር። [ነበረ]
ንዋም (ስም) መኝታ፤ ሠናይ ንዋም። መልካም መኝታ/ እንቅልፍ።
ቤተ ንዋም። መኝታ ቤት። [ኖመ]
ንጉሥ (ስም) በቁሙ።፤ ለምንት ቆምክን ቅድመ ንጉሥ? ለምን
ንጉሥ ፊት ቆማችሁ? [ነገሠ]
ኖመ (ግስ) ተኛ፤ ዮሴፍ ኖመ ዲበ ዐራት። ዮሴፍ አልጋ ላይ ተኛ።
[ኖመ]
አልቦ (ግስ) የለም፥ የ "ቦ" አፍራሽ፤ እበድ በልቡ ይብል አልቦ
እግዚአብሔር። ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል። [ቦ]
አመ (መስተዋ.) በ . . . ጊዜ፤ አመ ተወልደ. . . በተወለደ ጊዜ. .
. ጸልመ ፀሐይ አመ ተሰቅል ክርስቶስ። ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ
ጨለመች። [አመ]
አሜ = አመ
አሜሃ = አመ
አምላክ (ስም) በቁሙ።፤ ቀደምትክሙ ሰገዱ ለእግዚአብሔር
አምላኮሙ። አባቶቻችሁ ለእግዚኣብሔር አምላካቸው ሰገዱ።
[መለከ*]
አምሳል (ቅ.) ምስያ፤ ወረደ መንፈስ ቅዱስ ላዕለ ሐዋርያት
በአምሳለ ርግብ። መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በሐዋርያት ላይ
ወረደ። [መሰለ]
አብ (ስም) አባት፤ አቡየ ውእቱ መምህር። አባቴ መምህር ነው።
[አብ]
አንበበ (ግስ) አነበበ፤ ወልደ ንጉሥ አንበበ መዝሙረ ዳዊት።
የንጉሥ ልጅ መዝሙረ ዳዊትን አነበበ። [ነበበ*]
አእመረ (ግስ) ዐወቀ፥ ተረዳ፥ ተገነዘበ፤ ውእቶሙ ውሉድ
አእመሩ ትርጓሜ መጻሕፍት። እነዚያ ልጆች የመጻሕፍትን ትርጉም
ዐወቁ። [አእመረ]
አኮ (ግስ) አይደለም፤ አኮ ሐራ አቡአ። አባቷ ወታደር አይደለም።
ግእዝ ዐማርኛ መዝገበ ቃላት በብሩክ በየነ
እንስት
[አኮ]
አዋልድ (ብዙ ቊ.) ሴቶች ልጆች፤ እላ አዋልድ አንሥኣ
መጻሕፍቲሆን። እነዚያ ሴት ልጆች መጻሕፍቶቻቸውን አነሡ።
[ወለደ]
አውራኅ (ብዙ ቊ.) ወሮች፤ ዝንቱ ብእሲ ወረደ ኀበ ምድረ ግብፅ
ወነበረ ህየ ሠለስተ አውራኅ። ይህ ሰው ወደ ግብፅ አገር ወረደና
ሦስት ወር በእዚያ ተቀመጠ። [ወርኅ]
አይቴ (ተ.ግ.) የት፥ ከወዴት፤ አይቴ መጽአ እላ ሠናያት አንስት
(አዋልድ)? እነዚህ ቆንጆ ሴቶች (ሴት ልጆች) ከወዴት መጡ?
[አይቴ]
አፍቀረ (ግስ) ወደደ፥ አፈቀረ፤ ማርታ አፍቀረት ሳምሶንሃ፤
ወሳምሶንሰ አፍቀረ ርብቃ። ማርታ ሳምሶንን አፈቀረች፤ ሳምሶን ግን
ርብቃን አፈቀረ። [ፈቀረ*]
እለ (ቅ.) እነ፤ እለ መኑ እንትሙ? እናንተ እነማን ናችሁ? እለ መኑ
ቀተሉ ከልበነ ? ውሻችንን የገደሉት እነማን ናቸው? እመ
እግዚአብሔር ኢሐነጸ ቤተ ክንቶ ይጻምው እለ የሐንጹ። ቤትን
እግዚአብሔር ካላነጸው የሚያንጹ በከንቱ ይደክማሉ። [እለ]
እላ (ተው. ስ.) እነዚያ፥ (ሴቶች)፤ እላ አዋልድ አንሥኣ
መጻሕፍቲሆን። እነዚያ ሴት ልጆች መጻሕፍቶቻቸውን አነሡ። [እላ]
እልኩ (ተው. ስ.) እነዚያ፥ (ወንዶች)፤ እልኩ ሰብእ ሮማውያን
እሙንቱ። እነዚያ ሰዎች ሮማውያን ናቸው። [እልኩ]
እልክቱ = እልኩ
እልክቶን = እልኮን
እልኮን (ተ.ግ., ተው. ስ.) እነዚያ፥ (ሴቶች)፤ እልኮን ደናግል
መጽአ እምገዳም። እነዚያ ደናግል ከገዳም መጡ። [እልኮን]
እማንቱ ⑴ (ተው. ስ.) እነርሱ (ሴቶች)፤ ⑵ (ግስ) ናቸው፥
ነበሩ፤ አይዳ ወሠሚራ ሠናይት እማንቱ። አይዳ እና ሠሚራ
ቆንጆዎች ናቸው።፤ ⑶ (ተ.ግ.) እነዚያ፥ (ሴቶች) [እማንቱ]
እም 1 (ስም) እናት [እም]
እም 2 (መስተዋ.) ⑴ ከ . . .፤ እምሰማይ = ከሰማይ፤ ⑵ ከ.
. . ይበልጥ፥ ከ. . . ተለይቶ/ ይልቅ፤ እምሐዋርያት =
ከሐዋርያት ይበልጥ/ ይልቅ፤ ⑶ ዘንድ፤ እምፍጥረት ዓለም =
የዓለም ፍጥረት ዘንድ፤ ⑷ ጀምሮ፤ እምይእዜ ወእስከ ለዓለም።
ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም። ("እም" የ"መ" ዘር ሲከተለው "ም"
ይዋጣል፤ እምማርያም = እማርያም (ከማርያም)፣ እምመንበር =
እመንበር (ከወንበር))፤ ⑸ = እምነ [እም]
እምነ (መስተዋ.) ከ. . .፤ እምነ ማርያም ዘተወልደ ክርስቶስ
ተሰቅለ በዕለተ ዓርብ ዲበ ዕፀ መስቀል። ከማርያም የተወለደ
ክርስቶስ ዓርብ ዕለት በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ። [እም]
እምአይቴ (ተ.ግ.) ከወዴት፥ የት፤ እምአይቴ መጽአ እላ ሠናያት
አንስት (አዋልድ)? እነዚህ ቆንጆ ሴቶች (ሴት ልጆች) ከወዴት
መጡ? [አይቴ]
እበድ (ቅ.) ሰነፍ፤ እበድ በልቡ ይብል አልቦ እግዚአብሔር። ሰነፍ
በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል። [እበድ]
እንስት (ብዙ ቊ.) ⑴ ሴቶች፤ ውእቶን አንስት ሰገዳ
ለእግዚአብሔር አምላክ እስራኤል። እነዚያ ሴቶች ለእስራኤል
አምላክ እግዚአብሔር ሰገዱ።፤ ⑵ ሚስቶች፤ አንስት ያፈቅራ
ገጽ 3
እንትኩ
ምቶን ወውሉዶን ወአዋልዲሆን ወአዝማዲሆን። ሚስቶች
ባሎቻቸውን፣ ወንድ ልጆቻቸውን፣ ሴት ልጆቻቸውን እና
ዘመዶቻቸውን ይወዳሉ። [ብእሲት]
እንትኩ (ተው. ስ.) ያቺ፤ እንትኩ ወለት ሠናይት ይእቲ። ያቺ ሴት
ልጅ ቆንጆ ናት። [እንትኩ]
ከልብ (ስም) ውሻ፤ ዝንቱ ብእሲ ቀተለ ከልበ። ይህ ሰው ውሻ
ገደለ። [ከልብ]
ካልእ (ተ.ግ.) ሌላ፥ መሰል፥ ሁለተኛ፤ ካልእከ፣ ካልእኪ፣ ወዘተ .
. . ሌላኛህ፣ ሌላኛሽ፣ ወዘተ . . . ዘትፈቅድ ለርእስከ ግበር
ለካልእከ። ለራስህ የምትፈልገውን ለሌላው (ለጓደኛህ) አድርግ።
[ካልእ]
ክልኤ (ቅ.) ሁለት፥ ሌላኛ፤ ክልኤሆሙ ሖሩ ኀበ ቤቶሙ።
ሌላኛዎቻቸው ወደ ቤታቸው ሄዱ። [ክልኤ]
ኮነ (ግስ) ሆነ፤ ወይእቲ ወለት ኮነት ሠናይት ጥቀ። እና ይቺ ሴት
ልጅ በጣም ቆንጆ ሆነች። [ኮነ]
ኵሉ (ተ.ግ.) ሁሉ፤ ኵልነ አግበርተ እግዜአብሔር ንሕነ ሁላችንም
የእግዚአብሔር ባርያዎች ነን። መጽኡ ኵሎሙ ወተሳአሉ በእንተ
ንጉሥሙ። ሁሉም መጡና በንጉሣቸው ስም ለመኑ። [ኵሉ]
ወ (መስተጻ.) ⑴ እና፤ ዳንኤል ወሮቤል = ዳንኤልና ሮቤል፤ ⑵
- ም፤ ወጴጥሮስ = ጴጥሮስም (የዐርፍተ ነገር መጀመሪያ ሆኖ
ሳይተረጎም ይቀራል።) [ወ]
ወሀበ (ስም) ሰጠ፤ ብላዕ ኅብስተከ ዘወሀበከ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር የሰጠኽን እንጀራ ብላ። [ወሀበ]
ወለት (ስም) ሴት ልጅ፤ ዛቲ ወለት አርሴማ ይእቲ። ያቺ ሴት ልጅ
አርሴማ ናት። [ወለደ]
ወለደ (ግስ) በቁሙ።፤ ማርያም ወለደት ክርስቶስሃ። ማርያም
ክርስቶስን ወለደች። [ወለደ]
ወልድ (ስም) ወንድ ልጅ፤ ወልደ ንጉሥ አንበበ መዝሙረ ዳዊት።
የንጉሥ ልጅ መዝሙረ ዳዊትን አነበበ። [ወለደ]
ወረደ (ግስ) በቁሙ።፤ ወወረደት ወለተ ፈርዖን ኀበ ተከዚ
ወረአየት ዛተ ነፍቀ። አሜሃ ፈነወት ወለታ ወአምጽአታ ለነፍቅ።
የፈርዖን ሴት ልጅ ወደ ወንዝ ወረደች እና በዚያም አንድ ቅርጫት
አየች። ወዲያውኑ ገረዷን ላከቻት እና ቅርጫቱን አስመጣቻት።
[ወረደ]
ወራዙት (ብዙ ቊ.) ወንዶች፥ ጎልማሶች፥ ዐዋቂ ሰዎች [ወሬዛ]
ወሬዛ (ስም) ጎልማሳ፥ ዐዋቂ ሰው፤ ወለትከ አፍቀረት ወሬዛ።
ሴት ልጅህ ወንድ አፈቀረች። [ወሬዛ]
ወርኅ (ስም) ⑴ ወር፤ ⑵ ጨረቃ፤ ወከዋክብትኒ ወደቁ፣ ዲበ
ምድር፣ ወፀሐይ ጸለመ፣ ወወርኅ ለበሰት ደም አመ ተሰቀለ
ክርስቶስ። ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ኮከቦች ምድር ላይ ወደቁ፣ ፀሐይ
ጨለመ፣ ጨረቃም ደም ለበሰች። [ወርኅ]
ወንጌላዊ (ስም) በቁሙ።፤ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ መሀረ ወንጌለ
ክርስቶስ በግብፅ። ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊው የክርስቶስን ወንጌል
በግብፅ አስተማረ። [ወንጌላዊ]
ወደቀ (ግስ) በቁሙ።፤ ወከዋክብትኒ ወደቁ፣ ዲበ ምድር፣ ወፀሐይ
ጸለመ፣ ወወርኅ ለበሰት ደም አመ ተሰቀለ ክርስቶስ። 25.
ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ኮከቦች ምድር ላይ ወደቁ፣ ፀሐይ
ጨለመ፣ ጨረቃም ደም ለበሰች። [ወደቀ]
ግእዝ ዐማርኛ መዝገበ ቃላት በብሩክ በየነ
ድቀት
ወድቀ (ግስ) ወደቀ፤ አነ ወደቁ ልዕለ መሬት። መሬት ላይ
ወደቅኩ። [ወድቀ]
ውሉድ (ብዙ ቊ.) ወንድ ልጆች፤
እልክቱ ውሉድ
ኢትዮጵያውያን ውእቶሙ። እነዚያ ወንድ ልጆች ኢትዮጵያውያን
ናቸው። [ወለደ]
ውስተ (መስተዋ.) ውስጥ፥ ወደ ውስጥ፤ ውስተ ሰማይ = ወደ
ሰማይ፣ ወደ ሰማይ ውስጥ። ክርስቶስ ተንሥአ እመቃብር ወዐረገ
ውስተ ሰማይ። ክርስቶስ ከመቃብር ተነሣና ወደ ሰማይ ዐረገ።
[ውስተ]
ውእቱ (ተው. ስ.) ⑴ እሱ፤ ውእቱ ሖረ ኀበ ደማስቆ። እሱ ሄደ
ወደ ደማስቆ።፤ ⑵ (ግስ) ነው፤ ⑶ (ተው. ስ.) ያ፥ (እሱ)
[ውእቱ]
ውእቶሙ ⑴ (ተው. ስ.) እነርሱ፥ (ወንዶች)፤ ⑵ ናቸው፥
ነበሩ፥ (ወንዶች)፤ ኢሳያስ ወኤርሚያስ ነቢያት ውእቶሙ።
ኢሳያስ እና ኤርሚያስ ነቢያት ናቸው።፤ ⑶ እነዚያ፥ (ወንዶች)
[ውእቶሙ]
ዓመታት (ብዙ ቊ.) በቁሙ። [ዓመት]
ዓመት (ስም) በቁሙ።፤ ክርስቶስ መሀረ ሠለስተ ዓመት ለውሉደ
እስራኤል። ክርስቶስ የእስራኤልን ልጆች ሦስት ዓመት አስተማረ።
[ዓመት]
ዕፅ (ስም) ዛፍ፥ እንጨት፥ ትንሽ ዛፍ፥ በቁሙ፤ ክርስቶስ ተሰቅለ
በዝንቱ ዕፅ። ክርስቶስ በዚህ እንጨት ላይ ተሰቀለ። [ዕፅ]
ዘ (ምዕላ.) ⑴ የ. . .፤ ዘወሀበ = የሰጠ፤ ዘሖረ = የሄደ፤ ⑵
የእገሌ፤ ዘፊሊጶስ የፊሊጶስ [ዘ]
ዛ = ዛቲ
ዛቲ (ተው. ስ.) ያቺ [ዛቲ]
ዝ = ዝንቱ
ዝስኩ = ዝኩ
ዝንቱ (ተው. ስ.) ይህ፤ ዝንቱ ብእሲ ሖረ ኀበ ድሬ ዳዋ። ይህ ሰው
ወደ ድሬ ዳዋ ሄደ። ዝብእሲ ሖረ ኀበ ድሬ ዳዋ። ይህ ሰው ወደ
ድሬዳዋ ሄደ። [ዝንቱ]
ዝኩ (ተው. ስ.) ያ፤ ዝኩ ብእሲ መምህረ ቅኔ ውእቱ። ይህ ሰው
የቅኔ መምህር ነው። [ዝኩ]
ዝክቱ = ዝኩ
ዝየ (ተ.ግ.) እዚህ፤ ቦ መጽሐፍ ዝየ። እዚህ መጽሐፍ አለ። [ዝየ]
ይእቲ (ተው. ስ.) ⑴ እሷ፤ ይእቲ ሖረት ኀበ አስመራ። እሷ ወደ
አስመራ ሄደች።፤ ⑵ (ግስ) ናት፥ ነች፤ ⑶ (መስተዋ.) ያቺ
[ይእቲ]
ይእዜ (ተ.ግ.) አሁን፤ ውእቶን ይቤላ ናሁ አምታቲነ አፍቀሩ
አንስተ ክልአተ፣ ምንተ ንግበር ይእዜ? እነርሱ ይላሉ አሁን
ባሎቻችን ሌላ ሴቶችን አፈቀሩ፣ ምን ይደረግ እንግዲህ በዚህ ጊዜ?
[ይእዜ]
ዲበ (መስተዋ.) ላይ፤ ወባሕቱ መጽኡ ኅቤሁ በዕለተ ዓርብ
ወሰቀልዎ ዲበ ዕፀ መስቀል። ነገር ግን ወደ እርሱ በዕለተ ዓርብ
መጡና በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉት። [ዲበ]
ድቀት (ስም) መውደቅ [ወድቀ]
ገጽ 4
ገብረ
ፍቁራን
ገብረ (ግስ) ሠራ፥ አደረገ፥ ፈጠረ፤ በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር
ሰማየ ወምድረ። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን
ፈጠረ። [ገብረ]
ገብአ (ግስ) ⑴ ገባ፤ ሖራ ኀበ ደብረ ማርቆስ ወነበራ ህየ ሠለስተ
አውራኀ ወገብአ ኀበ ዝንቱ መካን። ወደ ደብረ ማርቆስ ሄዱ እና ወደ
ቦታው ገብተው በዚያም ለሦስት ወራት ተቀመጡ።፤ ⑵ ተመለሰ
[ገብአ]
ጊዜ (ተ.ግ.) በዚህ ጊዜ፥ በዚያ ጊዜ፥ ወዲያው [ጊዜ]
ጥቀ (ቅ.) በጣም፥ እጅግ፤ ወይእቲ ወለት ኮነት ሠናይት ጥቀ።
ይቺ ሴት ልጅ በጣም ቆንጆ ሆነች። [ጥቀ]
ጸለመ (ግስ) ጨለመ፤ ወከዋክብትኒ ወደቁ፣ ዲበ ምድር፣ ወፀሐይ
ጸለመ፣ ወወርኅ ለበሰት ደም አመ ተሰቀለ ክርስቶስ። 25.
ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ኮከቦች ምድር ላይ ወደቁ፣ ፀሐይ
ጨለመ፣ ጨረቃም ደም ለበሰች። [ጸለመ]
ጸለየ (ግስ) በቁሙ።፤ ከሣቴ ብርሃን ጸለየ በእንተ ኢትዮጵያ።
ከሣቴ ብርሃን ስለ ኢትዮጵያ ጸለየ። (ማስታወሻ፦ አንቱታ በግእዝ
እንደሌለ ልብ ማለት ያስፈልጋል) [ጸለየ]
ጸሐፈ (ግስ) ጻፈ፤ አንትን ጸሐፍክን መጽሐፈ ታሪክ ዘነገሥተ
ኢትዮጵያ። እናንተ የኢትዮጵያ ነገሥታትን መጽሐፍ ጻፋችሁ።
(ለሴቶች) [ጸሐፈ]
ጻድቅ (ስም, ቅ.) እውነተኛ፥ ቀና፥ በቁሙ፥ ቀናዒ፥ ታማኝ፤
ዝንቱ ብእሲ ጻድቅ ውእቱ። ይህ ሰው እውነተኛ ነው። [ጸደቀ]
ፍቁራን (ብዙ ቊ.) ወዳጆች፥ ጓደኛሞች፤ አንተ ወአነ ኮነ
ፍቁራነ። አንተ እና እኔ ወዳጆች ሆንን። [ፈቀረ*]
ግእዝ ዐማርኛ መዝገበ ቃላት በብሩክ በየነ
ገጽ 5
Download