የአሞሌ ጨው ዋና - 4 አሞሌ ባሕሩ ውስጥ እየሟሟ ነው። አንዴ በአንድ አቅጣጫ ሰብሰብ ብሎ፣ ደርቆ አሞሌ ለመሆን ይሞክራል፤ ማዕበሉ ይመጣና ጠርጎ ያሟሟዋል፤ ሌላ ጊዜ ፀሐይ ዳር ተሰጥቶ ቆቋር መፍጠር ይፈልጋል፤ ጎርፉ ይመጣና ጠርጎ ይወስደዋል። የሟሙት ቆቋሮች ጨንቋቸው ካሉበት ባሕር ውጭ "ተባበሩ፤ አትከፋፈሉ" የሚል መፈክር ሰሙ። "አቅቶን ነው እንጂ ጠልተን መሰላችሁ" ይላሉ ቆቋሮቹ። አንዱ ዩቱበር ባሕር ዳር ሆኖ "አሞሌ በባሕሩ በስተ ሰሜን፣ በስተ ደቡብ፤ በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ እያጠቃ ነው፤ ርዳታ እንሰብስብ" ሲል ሰሙት። "አይ ጅላንፎ፤ አሞሌ ቢንከራተት ምን ዋጋ አለው። ለጎል ነው እንጂ ለጨዋታ ነጥብ የለውምኮ። በጨዋታ ታስጨበጭባለህ፤ በጎል ግን ታሸንፋለህ። አሞሌ እህል መሰለህ እንዴ ሲዘራ የሚበቅል! ድሮስ የሟሟ አሞሌ በየቦታው ላይበተን ነው? ነገር የመጣውኮ አሞሌ በብርሌ ሲመራ ነው።" አሉና ከባሕሩ ማዕበል ጋር ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ትግል ቀጠሉ። https://www.facebook.com/tsilat23/posts/pfbid0ZxdsNLEUQv73cqcAKHjNJikvHWzZPgdvxgvuaMbAtbKWQsKs56bEEyfAsyVBEiAgl