Uploaded by Assocakazama

ቢሮው ባካሄደው ድንገተኛ ክትትል ከ70 ግራም በታች ዳቦ በመጋገርና የዋጋ ዝርዝር ሳይለጥፉ ሲሸጡ በተገኙ 165 ዳቦ ቤቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ

advertisement
Addis Ababa Trade Bureau
facebook.com/permalink.php
Favorites · oponrStsed95ff81271490f6fma00iu74g8cut6iitu14mc3h26tl32cg6uh ·
ቢሮው ባካሄደው ድንገተኛ ክትትል ከ70 ግራም በታች ዳቦ በመጋገርና የዋጋ ዝርዝር ሳይለጥፉ ሲሸጡ በተገኙ
165 ዳቦ ቤቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ፡፡
=========
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት በከተማችን ለህብረተሰቡ ዳቦ በሚቀርቡ
ቤቶች ላይ ድንገተኛ ክትትል በማድረግ ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ 165 ዳቦ ቤቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ
መውሰዱ ተገለፀ፡፡
በአሁኑ ወቅት በመዲናችን አዲስ አበባ 1 ሺህ 323 ዳቦ ቤቶች የሚገኙ ሲሆን ለህብረተሰቡ ከ70 ግራም በታች
ዳቦ በመጋገር እንዳያቀርቡ ክትትልና ቂጥጥር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በተለይም ቢሮው የሸማቾች መብትን ከማስጠበቅ አኳያ ዳቦ ቤቶች የሚቀርባቸው የዳቦ ምርቶች ዋጋ በዝርዝር
በግልፅ መለጠፍ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የሚዛን ከማጓደል ጋር በተያያዘ የሚስተዋል ህገ ወጥ ተግባር ለመከላከል
ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡
በዚህም በ2015 በበጀት ዓመት ብቻ ከ70 ግራም በታች ዳቦ በመጋገር ግራም አጓደለው የተገኙ 77 ዳቦ ቤቶች
በተደረገ ክትትል የተለዩ ሲሆን 88 ዳቦ ቤቶች ደግሞ የዋጋ ዝርዝር ሳያለጥፉ በመሸጥ የተገኙ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ቢሮው በበጀት ዓመቱ የተቀመጠ አሰራር በመጣስ በተገኙ 165 ዳቦ ቤቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ
የወሰደ ሲሆን ለ159 ዳቦ ቤቶች የመጀመሪያ ጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ከጥፋታቸው እንዲታረሙ
የተቀሩት 6 ዳቦ ቤቶች ደግሞ እንዲታሸጉ በማድረግ እርምጃ ወስጃለሁ ሲል በ2015 በጀት ዓመት ማጠቃለያ
ሪፖርቱ ላይ ይፋ አድርግዋል፡፡
1/1
Download