Uploaded by firaolnegn

ሲኖዶስ

advertisement
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በወቅታዊ የቤተ
ክርስቲያን ሁኔታ
ላይ ግንዛቤ
ለመፍጠር
የተዘጋጀ
የ ሰ ን በ ት ት /ቤ
ቶ ች አ ን ድነ ት
• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ን ላለፉት 2 Xg=
c ዓመታት ሰውን
እግዚአብሔር ላዘጋጀለት የድኅነት ዓላማ ለማብቃት ስትተጋ ኖራለች
፤ በመትጋትም ላይ ትገኛለች፡፡
• በዚህ አገልግሎቷም ፤ ዘር ቀለም ፤ ጎሣ ሳትለይ ለሁሉም
ኢትዮጵያውያን እና አቅም እንደ ፈቀደ በውጪውም ዓለም ተደራሽ
ለመሆን ስትሠራ ቆይታለች ፤ በመሥራትም ላይ ትገኛለች፡፡
• ቤተ ክርስቲያኗ ስለምትመራቸው ምእመናን ሁለንተናዊ ሕይወት
የሚገዳት ናት፡፡
• ይህም በመሆኑ ፤ ከመንፈሳዊ ሕይወት ባሻገር
ለሥጋዊና ምድራዊ ጤናማ አኗኗር የሚበጁ ነገሮችን
ሁሉ ለመምራት ውጤታማ ሚና ወስዳ ኖራለች፡፡
• በዚህም ከምእመናኗ በተጨማሪ ለመላው የኢትዮጵያ
ሕዝብ ወሳኝና ጠቃሚ ፤ በዓለም መለያ የሆኗቸውን
ጥበቦችና እሴቶች አስገኝታለች፡፡
• ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ
üሀገሩን የሚወድ ፤ በሕግና ሥርዓት የሚመራ
ሥልጡን ማኅበረሰብ በመገንባት
üየወንጌልን እና እውነተኛ ክርስትናን በርሃን
እንድታገኝ
üበቅኝ ግዛት እንዳትያዝና ሉዓላዊነቷ እንዲጠበቅ ፤
ልጆቿም በባርነት እንዳይያዙ፤
üየረጅም ዘመን ታሪክ ያለው ሀገረ መንግስት
እንዲኖራት
üየሥነ-ምግባርና የሞራል ምንጭ በመሆን
üየራሷ ቋንቋና ፊደል እንዲኖራት
üለሥልጣኔና መራቀቅ የሚጠቅሙ የተለያዩ የጥበብና
ምርምር መጻሕፍት እንዲኖራት
üየኪነ-ጥበብና ሥነ-ልሳን ስልጣኔ እንዲኖራት
üየመልክዓ ምድር ልማት ጥበብ እንዲኖራት
üለደንና የተፈጥሮ ሀብት መጠበቅ
üለሥነ-ሕንጻ ጥበብ ዕድገት
üሰፊ የቱሪዝም ሀብት እንዲኖራት
• በብዙ መልኩ በብቸኝነት ትልቅ አስተዋጽኦን
አበርክታለች፡፡ በማበርከትም ላይ ትገኛለች፡፡
ይሁን እንጂ የጥንካሬ ተምሳሌት የሆነችው ቤተ
ክርስቲያናችን ዛሬ
• ለቀጣይ ሕልውናዋ አስጊ የሆኑ የከበዱ ፈተናዎች
ተጋርጠውባታል::
• ባለማቻት ሀገርና ብዙ ውለታ በዋለችላቸው ልጆችዋ
ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃቶች እየተሰነዘሩባት
ይገኛሉ::
• ከብዙ በጥቂቱ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሉባትን ፈተናዎች
በሁለት ጎራ ከፍሎ ማየት ይቻላል::
üውስጣዊ ችግሮች
üውጫዊ አደጋዎች
ውስጣዊ ችግሮች
Ø የዘረኝነት አስተሳሰብ
Ø ፍቅረ ሲመት
Ø የሙስና እና ብልሹ አሠራር
Ø የሐዋርያዊ ተልእኮ መዳከም
Ø የሀብት አስተዳደር ደካማነት
Ø የምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት መደብዘዝ
ውጫዊ አደጋዎች
• የሀገሪቱ የዘር ፖለቲካ ችግሮች ዳፋ
• ሠርጎ ገብ መናፍቃን
• አክራሪ እስልምና
• የሉላዊነት አሉታዊ ተጽዕኖዎች
እና ሌሎችም ችግሮች ተጋርጠውባታል፡፡
ü ዛሬ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችን አጣምሮ
ቤተክርስቲያናችንን መለመበተታን ሰፊ
እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ፡፡
• ከዚህ ውስጥ ሀገራችን የፖለቲካ አሠላለፍ ዋነኛው ሲሆን ፤
እሱም በሀገሪቱ ላይ በሚያሳርፈው ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ተጽዕኖ
ቤተ ክርስቲያን ሰለባ እየሆነች ነው፡፡
• ዛሬ ለቤተክርስቲያን ከባድ ፈተና ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን
እየከፈለ ያለው “ ህገ ወጥ ሲመት እና ሲኖዶስ ምሥረታ ”
አሳብ ሴረኞች ሀገራትን ብዙ ጊዜ እርስ በእርስ ለመከፋፈል
ሚጠቀሙበት የተጠና ሂደት ነው ፡፡
• ለምሳሌም በ 2 ኛው የዓለም ጦርነት የተሸነፉ
የጀርመን ሚሺነሪዎች ዓለም ዓቀፍ የጸረ ሴም
ፕሮጀክት አካልን መጥቀስ ይቻላል፡፡
• እነዚህ ጎራዎች እርስ በርሳቸው በሚያደርጉት
ፉክክር ፤ ሀገራትን ከራሳቸው ፍላጎት አንጻር
ለመቃኘት ፤ ያቺን ሀገር በረቀቁ ሴራና አሠራሮች
እስከማፈራረስ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡
• ለዚህ ደግሞ ዜጎችን እርስ በርስ ማናከስ አንዱ
ማስፈጸሚያ ሊሆን ይችላል፡፡
• ስለሆነም ይህችን አንድነታችንን ያጸናች ቤተክርስቲያንን ከተቃጣባት
የጥፋት ወረራ ለመታደግ ሁሉም የድርሻውን በመውሰድ
ü
ü
ü
ü
ስለ ቤተክርስቲያንን ምንነት
ስለ ቤተክርስቲያን ባሕርያት
ስለ አደረጃጀቷ
ስለ ወቅታዊ ተግዳሮቶቿ እና የቅዱስ ሲኖዶስን
ውሳኔዎች ከነመልእክቶቻቸው አኹናዊውን
ችግራችንን ከመፍታት አንፃር
• ለቤተክርስቲያኒቱ የላእላይ እና የማእከላዊ መዋቅር አካላት
የተመጠነ እና ወቅታዊውን አደጋ ለመጋፈጥ በእውቀት ላይ
ተመሠረተ ኃይል የሚሰጥ፣ ለታህታይ መዋቅሩ ሰፊ ትንተና
ያለበት ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡
ክፍል አንድ
ቤተክርስቲያን
1 የቤተክርስቲያን ምንነት
• በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት
ቤተክርስቲያን ስንል ሦስት ነገሮችን ያመለክታል።
• እነዚህም የሚከተሉት ናቸው።
ሀ. እያንዳንዱ ምእመን
ለ. የምእመናን ኅብረት
ሐ. ሕንፃ ቤተክርስቲያን
ሀ . እያንዳንዱ ምእመን
በሥላሴ ስም ተጠምቀን፣ በሜሮን ከብረን፣ በሥጋ ወደሙ ታትመን፣
ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና የተቀበልን ምእመናን አካል ብቻውን
ቤተክርስቲያን ተብሎ ተጠርቷል።
ü1ኛ ቆሮ 3÷16-17 “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደኾናችሁ
የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር
እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ
ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።”
ü1ኛ ቆሮ 6÷19-20 “ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር
የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ
መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?”
ለ. የምእመናን ኅብረት
• ጥንቱን በዕብራይስጥ “ካሃል”፣ በኋላ ቅልክ የብሉይ ኪዳን
መጻሕፍት ወደ ግሪክ ሲተረጎሙ ደግሞ “አቅሌሲያ” በሚል ቃል
የተተካው የቤተክርስቲያን ስያሜ “ለተመረጠ ዓላማ የተጠራ
የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ የሚል ትርጉም ነበረው―"ቤተ
እሥራኤል" እንዲል።
• ይኸውም ሊታወቅ በሐዲስ ኪዳን “በቆሮንቶስ ያለች”፣ “በኤፌሶን
ያለች”…ወዘተ ቤተክርስቲያን ሲል ይገኛል።
• በዚኽ መልኩ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካልና በእርሱ ራስነት
አንድ አካል የኾኑ የምእመናን አንድነት ናት።
– ቆላ 1፥18 "እርሱም የአካሉ ማለት የቤተክርስቲያን ራስ ነው"
• በሌላ በኩል ይህችኛዋ ቤተክርስቲያን ኹለት ዓይነት ናት።
ü ተጋዳይዋ ቤተክርስቲያን
• በዚኽ ዓለም ውስጥ በጉዞና በተጋድሎ ላይ ያሉት ምእመናን አንድነት
ናት።
• የተጋዳይዋ ቤተክርስቲያን አንዱ ጠባይ በውስጧ ሐሰተኞች እና
ክፉዎች ከደገኞቹ ጋር ተደባልቀው መገኘታቸው ነው።
• ይኽም ምሳሌዋ በኾነችው በኖኅ መርከብ የምንረዳው ነው።
• በመርከቧ ውስጥ እባብ ከእርግብ ጋር የመርከቧ ሕይወት ተካፋይ
ነበር። ዘፍ 7፥9
• በተመሳሳይ መልኩ ይሁዳ ከሐዋርያት ጋር፣ ቢጽ ሐሳውያን ከሐዋርያት
ጋር፤ መናፍቃንም ከሊቃውንት ጋር ተደባልቀው በአንዲቷ
ቤተክርስቲያን ውስጥ ነበሩ።
• ይኽ መደባለቅ ግን በአንድ ወቅት ያበቃል። መቼ?
ተጋዳይዋ ቤተክርስቲያን ወደ ድል አድራጊዋ ቤተክርስቲያን
ስትቀየር‼
üድል አድራጊዋ ቤተክርስቲያን
• ይኽቺኛዋ ቤተክርስቲያን ተጋድሏቸውን ጨርሰው፣
መከራውን ኹሉ በድል አድራጊነት ተወጥተው ወደ
ሰማያዊው ዓለም የሔዱት ምእመናን አንድነት ናት።
• በውስጧ ያሉት ኹሉ በሥጋቸው መከራ፣
በሐሳባቸው ክፋት፣ በአንደበታቸው ስሕተት
የለባቸውም።
• ለዚኽቺኛዋ ቤተክርስቲያን ኀዘን፣ ሞት፣ ጩኸት፣
ሥቃይ አብቅቶላታል።
• ራእይ 21፥4 “እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው
ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥
ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ
ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት
አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።”
ሐ. ሕንፃ ቤተክርስቲያን
• ይኽ በአብዛኛው የሚታወቅና በግዘፍ የምንረዳው ወይም
የምናውቀው ነው።
• በበርካታ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍል ቤተ መቅደስ፣ ቤተ
እግዚአብሔር የሚል እናገኛለን።
• አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈጸምበት፣ ምሥጢራት
የሚከብሩበት ለእግዚአብሔር የተለየ፣ የተቀደሰ ቦታ ከጥንት
ጀምሮ ነበር።
– ዘፍጥረት 28፥16–17 "ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነሥቶ ፦
በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው፤ እኔ አላወቅሁም
ነበር አለ። ፈራ፥ እንዲህም አለ፦ ይህ ስፍራ እንዴት
ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ
አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው።"
2 የቤተክርስቲያን ባሕርያት
“ ከሁሉ በላይ የምትሆን ሐዋርያት የሰበሰቧት አንዲት፣
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን” የሚለው አንቀጸ ሃይማኖት
የቤተክርስቲያን ባሕርያት ለምንላቸው ጥቅል መጠሪያ ነው።
• እነዚህም
የቤተ ክርስቲያን አንዲትነት
የቤተ ክርስቲያን ቅድስትነት
ቤተ ክርስቲያን ኩሏዊትነት
ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትነት
üቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት!!
• ቤተክርስቲያን አንዲት (አሐቲ) ናት፡፡
§ አይጨመርባትም፡ አይቀንስባትምም፡፡
§ አትከፈልም ፣ሁለት ወይም ሦስት ወይም ከዚያ በላይ አትሆንም፡፡
§ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ …”በዚህ አለት ላይ ቤተክርስቲያኔን
እመሠርታለሁ” አለ እንጂ “ቤተክርስቲያኖቼን” አላለም፡፡ ማቴ 16፡
18
• በአንድ መሠረት ላይ አንዱ መሥራች የመሠረታት ስለሆነች
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት፡፡
• ቤተክርስቲያን አንዲት ናት ሲባል በእርሷ ያለውን አንድነትም
ያመለክታል፡፡
üቤተ ክርስቲያን ቅድስት ናት!!
• ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ መሥርቷታል፤ አንጽቷታል፤
ቀድሷታልና ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ናት ኤፌሶን 5 ፥ 26፡፡
• የቤተ ክርስቲያን ቅድስና የተገኘው ቅድስና የባሕርይ ገንዘቡ
ከሆነው ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ
በመሆኑ ወደ እርስዋ የገቡ ርኩሳን ይቀደሳሉ እንጂ
በውስጥዋ ያሉ ሰዎች በኃጢአት በክህደት ቢረክሱ እርስዋ
አትረክስም፡፡
• ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ባለው
መሠረት በእርሱ ያመኑ በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር
የተጠለሉ ሁሉ ቅድስናን ገንዘብ ሊያደርጉ ይገባል፡፡
ü ኩሏዊት ናት!!
ቤተክርስቲያን ኲላዊት ናት ሲባል የሁሉ (ዓለም ዐቀፋዊት- Universal)
እና ከሁሉ በላይ ናት ማለት ነው፡፡
• ይህም በጸሎተ ሃይማኖት “እንተ ላዕለ ኩሉ” በሚለው ይታወቃል፡፡
• ቤተክርስቲያን የሁሉ እንደሆነች ሁሉ ደግሞ ከሁሉ በላይ ናት፡፡
• በደመ ክርስቶስ የተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የዚህ ወገን
ናት የዚህ ወገን አይደለችም የማትባል በዘር፣ በቋንቋ፣ በጎጥና በቀለም
እንዲሁም በቦታ የማትከፋፈል የሁሉና በሁሉ ያለች ናት፡፡
• ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን የሁሉም መሆንዋን
እንዲህ ሲል ገልጾታል“አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም ባሪያ
ወይም ጨዋ ሰው የለም ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው
ናችሁና” ገላቲያን 3፥28፡፡
üሐዋርያዊት ናት
• ቤተክርስቲያንም ሐዋርያዊት ናት ስንል ሐዋርያዊት የሆነችው
በአራት ነገሮች ነው፡፡
• በአመሠራረት፤ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ
ክርስቲያኑን የመሠረተው በሐዋርያት መሠረትነት ላይ ነው “የዮና ልጅ
ስምዖን ሆይ አንተ ብጹዕ ነህ . . . እኔም እልሃለሁ አንተ ዐለት ነህ
በዚይች ዐለት ላይም ቤተ ክርስቲያኔን አሠራታለሁ የሲዖል በሮችም
አይበረታቱባትም፡፡ የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ
በምድር የምታስረው በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድርም የምትፈታው
በሰማይ የተፈታ ይሆናል”ማቴዎስ 16 ፥ 15፡፡
• ቤተክርስቲያን የተስፋፋችው በእነርሱ ነው፡፡
• በሢመት ሀረግ ከሐዋርያት አንስቶ ያልተቋረጠ የሢመት ሀረግ መኖሩ
ቤተክርስቲያንን ሐዋርያዊት አድርጓታል፡፡ ጌታችን ለሐዋርያቱ
የሰጠው የክህነት ስልጣን ሳይቋረጥ በቀጥታ እየተላለፈ መምጣቱ
አንዱ የሐዋርያዊትነቷ መገለጫ ነው፡፡
በትውፊትና በምሥጢር፡- ቤተክርስቲያን የሐዋርትን ትውፊት
ተቀብላ መተግበሯ ሐዋርያዊት አድርጓታል፡፡ እንደ ሐዋርያት
ሲኖዶስ አላት፡ እንደ ሐዋርያት ታጠምቃለች፡ እንደ ሐዋርያት
ትቀድሳለች፡ ሥጋና ደሙን ታቀብላለች፡፡ ሐዋርያት የሠሩትን
እንደ ሐዋርያት አድርጋ ትሠራለች፡፡ ከሐዋርያት የተለየ
ሥርዓት ሊኖራት አይችልም፡፡ ይህ የሐዋርያዊትነቷ ሌላው
መገለጫ ነው፡፡
በመጻሕፍት ትርጓሜ፡- ሐዋርያዊ ክትትሉን የጠበቀ የቅዱሳት
መጻሕፍት ትርጓሜ ስላላት ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት፡፡
ሐዋርያት እንደተረጎሙት አድርጋ ትተረጉማለች፡፡ ሐዋርያት
እንዳስተማሩት አድርጋ ታስተምራለች፡፡ ሐዋርያት
ያላስተማሩትን አታስተምርም፡፡ በዚህም ቤተክርስቲያን
ሐዋርያዊት ናት፡፡
ክፍል ሁለት
ሲኖዶሳዊት ቤተክርስቲያን
1 ሲኖዶሳዊነት
ከሐዋርያዊነት የሚወረስ ጠባይ ነው።
• ቤተ ክርስቲያን ዘክርስቶስ በቅዱስ ሲኖዶስ መመራት የጀመረችው ከዘመነ ሐዋርያት
ጀምሮ ለመሆኑ ምሥክሩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
• የመጀመሪያው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተደረገበትን ምክንያት ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ
ግብረ ሐዋርያትን በገለጸበት ጽሑፉ ላይ እንዲህ ተርኮታል፡ü አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና፥ እንደ ሙሴ ስርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም
ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር፡፡ በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ
ጥልና ክርክር በሆነ ግዜ ስለዚህ ክርክር ጳውሎስና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች
ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ቀሳውስቱም ወደ ኢየሩሳሌምም ይወጡ ዘንድ ተቆረጠ።
• ሐዋርያት ለመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን
የመጨረሻው ወሳኝ አካል እነርሱ ነበሩ ::
• ይህ ሐዋርያዊ ውርስ ባላት የክርስቶስ ቤተ
ክርስቲያንም የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪ አካል
ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡
• ለዚህም ነው ሲኖዶሳዊት ያልሆነች ቤተ
ክርስቲያን ሐዋርያዊት አይደለችም
የምንለው፡፡
2 የጵጵስና መንበር
የሐዋርያዊነት መገለጫ ጠባይ ነው።
üየቤተ ክርስቲያን እርከናዊ መዋቅር ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ
የነበረ መሆኑን ያስገነዝበናል ::
üሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቁና ያስተዳድሩ ዘንድ መንፈስ
ቅዱስ ጳጳሳት አድርጎ የሾማቸው ናቸው።
üበሐዋርያት ያደረ ቅዱስ መንፈስ በቅዱስ ጳውሎስም ያደረ ሆኖ
ሳለ ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ሌሎች ሰዎችን ጨምረው ለምን?
ወደ ሐዋርያት መሄድ አስፈለጋቸው? የሚለው መጠይቅና መልስ
ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለተዋቀረው
የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የተገዙ መሆናቸውን ያሳያል::
• ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደ ምንረዳው የመጀመሪያው
የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ
በሐዋርያው በቅዱስ ያዕቆብ ሊቀ መንበርነት ከ49 – 50
ዓ.ም ባለው ግዜ የተካሄደው ከላይ በተገለጸው መሠረት
ከአሕዛብ ወገን ክርስትናን በተቀበሉና ከአይሁድ ወገን
ክርስትናን በተቀበሉት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት
ምክንያት ለዚያ እልባት ለመስጠት ነበር።
• የጵጵስና ዋና ሥራው ሕዝቡን ማስተማር፣ ከሃድያንን ወደ
አሚነ ሥላሴ ማምጣት፣ ሕዝቡን ከገቢረ ኃጢአት ወደ
ገቢረ ጽድቅ መመለስ፣ ደጋጉን በመልካም ሥራ ማጽናት
ነው።
• የኢትዮጵያ ጵጰስና ከመንበረ ማርቆስ የተገኘ ነው፡፡
ክፍል ሦስት
የቤተክርስቲያን ወቅታዊ ተግዳሮቶች
• ከሀሰተኛ ትርክቶች የመነጩ የማጥቂያ ስልቶችን መከተል
• ኦርቶዶክሳዊያንን መግደል፣ ማሳደድ፣
• ቤተክርስቲያንን መዝረፍ፣ ማፍረስ፣ ማቃጠል፣
• በመጨረሻም የኦሮሚያ ሲኖዶስ የመመሥረት እንቅስቃሴና
ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን የመሰንጠቅ አካሔድ፣
•
በቋንቋችን መገልገል አልቻልንም
• ፍትሃዊ በጀት ክፍፍል የለንም
•
አገልጋይ ካህናት ከሌላ ብሔር ሚመጡ
ናቸው ወዘተ …….
ተጨባጭ እውነታዎች
የቋንቋ ነገር
• አንዱ ስሞታ በኦሮምኛ ቋንቋ መገልገል አለተቻለም ነው።
• ይኽ ኹኔታ ከፊል እውነትነት ቢኖረውም በዐማራ እና ትግራይ አካባቢዎች
ጨምሮ በኹሉም አካባቢዎች የሚታይ ነው።
• በአማርኛና በትግርኛ ቋንቋ የሚቀደስባቸው የትግራይና የአማራ ክልል
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አጥቢያዎች ከ25 በመቶ
አይበልጡም፤ ቅዳሴያቸው ቋንቋ ግእዝ ነው፡፡
• ምእመኑ በእምነት ተቀብሎት ስለሚኖር እንጂ አብዛኛው አገልግሎት
የሚሰጠው በግእዝ ነው፡፡
• አብዛኞቹ ለአገልግሎት የሚውሉት ቅዱሳት መጻሕፍት ወደ
አማርኛ ከተተረጎሙ ከ50 ዓመታት በላይ አይሆናቸውም፡፡
• ብዙዎቹም ታትመው የተሠራጩት በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ
ጳውሎስ ዘመን ነው፡፡
• ራቅ ያለውን የአማርኛ የትርጉም ሥራ ብንቆጥር እንኳን ከመቶ
ዓመት አይዘልም፡፡
• እነዚያ መጻሕፍት በስፋት ታትመው፣ ለሕዝቡ ተዳርሰው፣
ካህኑና ሕዝቡ ለምዷቸው ለአገልግሎት እስኪውሉ ዘመናትን
ፈጅተዋል፡፡
• አማርኛም የተመረጠው በወቅቱ በነበረው ሀገራዊ መግባቢያነቱ
እንጂ እንደዛሬው የአንድ ወገን ቋንቋ ተደርጎ አልነበረም፡፡
• የቤተ ክርስቲያን የጸሎት ቋንቋዋ ዛሬ የማንም ብሔር ያልሆነው
ግእዝ ነው፡፡
• ሌሎች ቋንቋዎች ሁሉ ለእርሷ እኩል ናቸው፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•
በሌሎች ቋንቋዎች በሚገባ ያልሄደችው ስለማትፈልግ አልነበረም፡፡
ፈተናው አላሠራ ብሏት እንጂ፡፡
ለዚህ ደግም ትልቁ ፈተና ቤተ ክርስቲያኒቱ ፋታ አለማግኘቷ ነው፡፡
ከግራኝ ጦርነት በኋላ ዘመነ መሳፍንት መጣ፣ ከዚያም የደርቡሽና
የእንግሊዝ ጦርነት ተከሠተ።
ከዐፄ ምኒልክ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ በተገኘው አንጻራዊ ሰላም ነው
ከግእዝ ወደ አማርኛ ለመሻገር የተሞከረው፡፡
ያ ዘመን ቢቀጥል ኖሮ ወደ ሌሎች ቋንቋዎችም ቀድሞ ለመሻገር ይቻል
ነበር፡፡ አልሆነም፡፡
መጀመሪያ የጣልያን ወረራ ተከሠተ፣ ቀጥሎም አብዮት ፈነዳ፡፡
ስለዚኽ ራሱ አማርኛ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሲውል ልጅ ነው፡፡
ያንን ያህል ቀድሞ የሄደ፣ተጉዞ የነጎደ አይደለም፡፡
• እንዲያውም ከግእዝ ወደ አማርኛ ከተደረገው ሽግግር ይልቅ
ወደ ኦሮምኛ የተደረገው ሽግግር አጭር ጊዜ ብቻ ፈጅቷል፡፡
• በአማርኛ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ለማግኘት አንድ
ምእተ ዓመት ሲፈጅ፣ በኦሮምኛ ከ50 በላይ መጻሕፍትን
ለማግኘት ከ25 ዓመት በላይ አልፈጀም፡፡
• ከቤተ ክርስቲያን ዋናዎቹ የጸሎት መጻሕፍት አንዱ ግብረ
ሕማማት ወደ አማርኛ የተተረጎመው በ1990ዎቹ መጨረሻ
ነው፤
• ስንክሳር ወደ አማርኛ የተተረጎመው በ1990ዎቹ መጀመሪያ
ነው፡፡
የኢኦተቤክ መምህራን እና ሌሎች ቋንቋዎች ቀደም ባሉት ጊዜያት
• እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ እነ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ እነ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
በመላ ኢትዮጵያ ሲያስተምሩ የጎበኟቸው ሕዝቦች አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ
እንዳልነበሩ ገድሎቻቸው ይናገራሉ፡፡
• ሁሉንም በየቋንቋቸው ነው ያስተማሯቸው፡፡
• የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዛሙርት በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ማስተማራቸውን
ገድሎቻቸው ምስክሮች ናቸው፡፡
• በአምሐራ፣ በትግራይ፣ በዳሞት፣ በጋፋት፣ በአርጎባ፣ በጉራጌ፣በሲዳማ፣ በጋሞ፣
በሐድያ፣በኦሮሞ፣ በሶማሌ፣ በጉምዝ፣ በወላይታ፣ ወዘተ. አካባቢዎች አስተምረዋል፡፡
• አማርኛ ወይም ግእዝ በእነዚህ አካባቢዎች ሁሉ የሚነገር አልነበረም፡፡
• ታድያ በየሀገሩ ቋንቋ ካልሆነ በምን ያስተምራሉ?
የቅርብ ጊዜያት ኹነቶች
• በኋላ ዘመን ይህንን የቤተ ክርስቲያን ቀደምት አገልግሎት
እንደገና ለመመለስ ቢያንስ ስድስት ጥረቶች ተደርገዋል፡፡
• ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በገዛ ገንዘባቸው አገልጋይ
መድበው ወንጌል በቋንቋቸው እንዲሰጥ ካደረጉባቸው አካባቢዎች
መካከል የዛሬው የኦሮምያ ክልል አንዱ ነው፡፡
• ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ገዳምና ማሠልጠኛን
ተክለው ከሠሩት ሥራ አንዱ በኦሮምኛ የሚያስተምሩና የሚቀድሱ
ካህናትና ሰባክያንን ማፍራት ነው፡፡
• ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያደረጉት ጥረት፡፡ በኦሮምያ አካባቢዎች
ሊያስተምሩ የሚችሉ ኦሮምኛ ተናጋሪ ካህናትን በመመደብ፣ ኦሮምኛ
ተናጋሪ ጳጳሳትን በብዛት በመሾም፣ መጻሕፍት ወደ ኦሮምኛ
እንዲተረጎሙ በማበረታታት ታላቅ ሥራ ሠርተዋል፡፡
• ከሀገረ ስብከቶቹ ሥራ አስኪያጆች 90% ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡
• በአቡነ ጳውሎስ ዘመን የተጀመረው የትርጉም ሥራ ተበረታትቶ መጽሐፈ
ቅዳሴና ተአምረ ማርያም በኦሮምኛ ተተርጉሟል
üየጽርሐ ጽዮን መንፈሳዊ ማኅበር፤ ከመነሻው በደቡብ ኢትዮጵያ
የሚከናወነውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማበርታት የተቋቋመው
የጽርሐ ጽዮን መንፈሳዊ ማኅበር የአገልጋዮች ማሠልጠኛ በኦሮምያ
ክልል የክህነት አገልግሎትና ስብከተ ወንጌል በኦሮምኛ ቋንቋ
የተጫወተው ሚና ምትክ የለሽ ነው፡፡ ወደ ማሠልጠኛው
ለመግባት አንዱ መመዘኛም ከአማርኛ ቋንቋ ውጭ ሌላ የኢትዮጵያ
ቋንቋ ለመናገር መቻል ነው፡፡ ከኦሮምያ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች
ተመርጠው የሠለጠኑና ዛሬም እያገለገሉ ያሉትን አገልጋዮች
ብዛትና ማንነት ከማሠልጠኛው ፋይል መመልከት ይቻላል፡፡
üደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ ማኅበር፡፡ በ1998 ዓም በጅማ አንዳንድ
ቦታዎች የተከሠተውን ችግር መነሻ በማድረግና በአካባቢው
ያለውን የአገልግሎት መዳከም ለማበርታት የተቋቋመው የደጆችሽ
አይዘጉ ማኅበር በዋናነት የሚሠራው በኦሮምያ ክልል ጅማ አካባቢ
ነው፡፡ በአካባቢው ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን በገንዘብና በቁሳቁስ
በመደገፍ፣ በኦሮምኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ ካህናትንና ሰባክያንን
ማሠልጠኛ ገንብቶ በማሠልጠን፤ ለአገልጋዮቹ ደመወዝ በመክፈል፣
በየጊዜው ወደ አካባቢው መንፈሳዊ ጉዞ በማዘጋጀት፣ በአካባቢው
አገልግሎቱ እንዲበረታ ከ15 ዓመታት በላይ ደክሟል፡፡
– የብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስን ጅምር ለፍሬ ያበቃው ማኅበረ
ቅዱሳን ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ከምሥረታው ጀምሮ ነው
ለልዩ ልዩ ቋንቋዎች አገልግሎት ትኩረት የሰጠው፡፡ ከሀገር
ውሰጥ ለኦሮምኛና ትግርኛ፣ ከውጭ ለእንግሊዝኛ ቋንቋዎች
ትኩረት በመስጠት ላለፉት ሃያ ዓመታት ሠርቷል፡፡
üበኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን
በመርዳት
üአገልጋይ ለሌለባቸው በገንዘብ በመመደብ
üበኦሮምኛ ቋንቋ ለሚያገለግሉ ካህናትና ሰባክያን ሥልጠና
በማዘጋጀት
üበኦሮምኛ ቋንቋ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ
üበኦሮምኛ ቋንቋ መጻሕፍትን በማዘጋጀት
üበኦሮምኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ አገልጋዮችን በዋናው ማዕከል ደረጃ
መድቦ እጥረት ያለባቸውን አካባቢዎች እንዲረዱ በማድረግ
üበኦሮምኛ ቋንቋ የሚዲያ አገልግሎት በመስጠት
üበኦሮምኛ ቋንቋ መዝሙሮችን በማዘጋጀት፤- የሚቻለውን ሁሉ አድርጓል፡፡
üበምዕራብ ወለጋ ቂልጡ ካራ ያለውን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳምና
ማሠልጠኛ እንዲመሠረት በማድረግ ከምዕራብ ኦሮምያ የሚመጡ
አገልጋዮቸ ተገቢውን ሥልጠና እንዲገኑ ለማድረግ ጥሯል፤
üበግቢ ጉባኤያት በኦሮምኛ ቋንቋ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማስተማር፣
•
ቤተክርስቲያን ይህንን ያህል ጥረት እያደረገች ሳለ ስም የማጥፋት ዘመቻው ፍላጎት ሌላ እንደሆነ ግልጥ ነው
የኦሮሚያ ሲኖዶስ የመመሥረት እንቅስቃሴና
ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን የመሰንጠቅ አካሔድ፣
የችግሩ አነሣሥ እና እዚኽ ደረጃ የደረሰበት ኹኔታ በሚገባ ሊታወቅ
ይገባል። ጉዳዩ ኹለት መልክ አለው።
• አንደኛው መልክ የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነቶች
ነው።
1. ጣልቃገብነቱ በዓለም ላይ ኦርቶዶክሳዊነትን እንዲኹም
ኢትዮጵያዊነትን ለማክሰም የሚደረገው እንቅስቃሴ አካል ነው።
2. ይኽም በራሱ የተለያዩ አካሔዶች ያሉት ነው (በፖለቲካ፣
በሃይማኖት፣ በኢኮኖሚ፣ በጦርነት፣ ወዘተ)።
• ኹለተኛው መልክ የሀገር ውስጥ የብሔር
ጽንፈኞች አልፎ አልፎም ተላሎ ች ያላቸው
የተንሸዋረረ አረዳድ ነው።
• እነዚኽ አካላት በማወቅም ይኹን ባለማወቅ ከላይ ያየናቸውን የውጭ
ጣልቃ ገቦችን ተንኮል በመቀበል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያንን ጨቋኞች ካሏቸው ጋር ማያያዝን ምርጫ በማድረግ
ጠላት አድርገው ሥለዋል።
• እናም ተዘርዝረው የማያልቁ ክሶችን ቆልለውባታል።
Ø ጨቋኝ ጨፍጫፊ ነገሥታትን ቀብታ አንግሣለች፤
Ø ነገሥታቱ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ላካሔዱት ጦርነት ይኹንታ ሠጥታለች፤
Ø ግፈኞች አፄዎችን ዛሬም በጸሎቷ ትዘክራቸዋለች፤
Ø በአቡነ ተክለሃይማኖት አማካኝነት ኩሻውያንን ከመንበር አሳድዳለች፤
Ø ነገሥታቱ ከኦሮሞ በነጠቁት መሬት ቤተክርስቲያኗን የሢሶ ርስት ባለቤት
አድርገዋታል፤
Ø የነፍጠኛ ሃይማኖት ነች፤
በእንተ ወቅታዊ በጀት
• ቅዱስ ሲኖዶስ በኦሮምያ ክልል ለሚገኙ አህጉረ
ስብከቶች በ2014 ዓ.ም የሰጠው በጀት እና የ2015 ዓ.
ም የጸደቀው በጀት የፍትሐዊነቱ ማሳያ ነው፡፡
• ቅዱስ ሲኖዶስ በአብዛኛዎቹ በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ
አህጉረ ስብከት የሚልከው በጀት ሀገረ ስብከቶቹ
በፐርሰንት ለማዕከላዊው መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ
ጽ/ቤት ከሚከፍሉት የበለጠ እንደሆነ የ2014 ዓ.ም
የበጀት ሪፓርት ያሣያል።
• አብዛኛው አብነት ትምህርት ቤት ከሚገኝባቸው በሰሜን
ሀገራችን ክፍል ካሉ አህጉረ ስብከቶች ይልቅ ፤ ብዙ
የአብነት ትምህርት ቤቶች ለሌሉባቸው በኦሮሚያና ደቡብ
ለሚገኙ አህጉረ ስብከቶች ከፍ ያለ በጀት የተመደበበት
ሁኔታ ይታያል፡፡
• በ2015 ዓ.ም ለአብነት ትምህርት ቤት ማጠናከሪያ
ከተመደበው በጀት ከሁሉም በሀገሪቱ ከሚገኙ በህጉረ
ስብከቶች ከፍተኛውን የበጀት ብልጫ የሚወስደው ሀገረ
ስብከት የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሲሆን ከዚያ ቀጥሎ
ሁለተኛው የዳውሮ ሀገረ ስብከት ነው፡፡
ለማነጻጸሪያ እነዚህን ለአብነት ትምህርት ቤት የተመደበ አህጉረ
ስብከት ድጋፍ መመልከት ይቻላል ፡፡
• ምዕራብ ጎጃም - - - - - - - - 1,604,140
• ማዕከላዊ ጎንደር - - - - - - - - - 1,108,000
• ቄለም ወለጋ - - - - - - - - - - - 1,016,000
• የባሌ ሀገረ ስብከት- - - - - - 1,272,000
• ምዕራብ ሀረርጌ - - - - - - - - - 1,006,000
• ሰሜን ሸዋ ሰላሌ - - - - - - - 1,549,100
• ጉራጌ - - - - -- - - - - - - - - - - 1,427,100
• ሰሜን ኦሞ - - - - - - - - - - - - - 1,559,100
• ሐዲያና ሥልጤ . . . . . .. . . . . . 1,519,980
• ዳውሮ - - - - - - - - - - - - - 1,633,380
የካህናት ማሰልጠኛ
ከካህናትን በሁሉም አህጉረ ስብከቶች ለማሰልጠን የተያዘው በጀት
በንጽጽር መመልከት ይቻላል፡፡
ለ2015 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ባጸደቀው በጀት ለአህጉረ ስብከት፡• ለመቀሌ ሀገረ ስብከት ……………………..304,000
• ለአፋር ሀገረ ስብከት ………………………..360,400
• ለሰሜን ወሎ……………………………….....120,000
• ለምሥራቅ ሸዋ …………………………….....828,000
• ለባሕር ዳር ………………………………...... 784,000
•
•
•
•
•
•
•
•
ኢሉባቡር …………………………………...... 816,032
ጅማ ………………………………………….....593,280
ለቦረና ………………………………………......380,000
ለምዕራብ ጎንደር ………………………….....100,000
ለምዕራብ አርሲ ………………………….. ...190,000
ምዕራብ ወለጋ ………………………………....288,000
ለደቡብ ጎንደር……………………………… ....30,000
ይሄም በጀት ሲነጻጸር ቤተክርስቲያን ዘርና ብሔርን መሠረት
አድርጋ እንደማትሠራ ማሳያ ብቻ ሳይሆን ማስረጃ ነው፡፡
• ሀገረ ስብከቶች በራሳቸው ፋይናንስ በየአህጉረ ስብከቱ መሪ
ሊቃነ ጳጳሳትና በአስተዳደር ጉባኤያቸው ይበጀናል ያሉትን
ተግባር በነጻነት የመሥራት መብታቸው ሁልጊዜም
እንደተጠበቀ ነው፡፡
• አንድ ሀገረ ስብከት ዋነኛ ስኬት በመሪዎቹ ትከሻ ላይ
የወደቀ ነው፡፡
• በየገጠሩና በየበረሀው ከህዝባቸው ጋር ሆነው ወንጌልን
ሥራ ያደረጉ እና በመንፈሳዊ አባትነት አገልግሎቱን
የሚያከናውኑ አባቶች ስኬታማ ናቸው፡፡ አገልግሎታቸው
ከተማ ተኮር የሆነ አባቶች እንዴት የሕዝቡን ጥያቄ መመለስ
ይችላሉ። ባለው አቅምስ ሠርተው ምን ውጤት አመጡ ?
• አገልግሎታቸው ከተማ ተኮር የሆነ አባቶች እንዴት
የሕዝቡን ጥያቄ መመለስ ይችላሉ።
• ባለው አቅምስ ሠርተው ምን ውጤት አመጡ ?
• በአንድ ጊዜ ፖለቲከኛም የሃይማኖት አባትም መሆን
አይቻልም፡፡
• የፖለቲካ መሪ ለተወሰነ የማኅበረሰብ ክፍል በዋናነት የቆመ
በየጊዜው በሚቀያየር ዓለማዊ ርዕዮት እና አስተውሎት
የሚመራ ሲሆን የሃይማኖት አባት መሆን ግን ዘር ቋንቋ
ሳይሉ ሁሉንም የሰው ልጅ በፍቅርና በክብር በማገልገል
ዘለዓለማዊ ሕይወትን ዓላማ ያደረገ መንፈሳዊ ሕይወት
ነው፡፡
• ቤተክርስቲያንን ያለ ስሟ ስም መስጠቱ በማስረጃ የሚመዘን
እንጂ በስሜት የሚለካ አይደለም፡፡
• ቤተ ክርስቲያናችን ከሁለት ሺህ ዘመናት በላይ
በአንድነቷ ጸንታ የኖረችው
ሐዋርያዊት፤ታሪካዊት፤ዓለማቀፋዊት እና ጥንታዊት
የሆነችዋን አንዲት፤ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈልና ለማዳከም
አቅደው ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ጥሰው ንጹኃንን
ሕዝበ ክርስቲያን ለማደናገርና ለመከፋፈል በዚሁ
ሒደት ሀገራዊ አንድነትን ለማፍረስ ታቅዶ እየተሠራ
ያለ መሆኑን ሁሉም ሊረዳ ይገባል።
ክፍል አራት
ግብረ መልስ
• የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ምንነት፣
• የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ምክንያታዊነት
• የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተከታታይነት
• ልዩልዩ የቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አደረጃጀቶች
ች እና ምእመናን ጉዳዩን የተረዱበት መንገድና
የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን የተቀበሉበት ሁኔታ
ከእኛ ምን ይጠበቃል?
• ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድራት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
ነው ፡፡
• እግዚአብሔርን የሚቀድመዉ ስለሌለ መስጋት አያስፈልግም።
• እምነታችን እንዲጨምር የሚያስጨንቀንን ለበጎ እንዲቀይርልን
መፈለግና መጠየቅ መጣርም ይጠበቅብናል።
• ቤተክርስቲያን ሆነች እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ ለብሔር
ብሔረሰቦች የሚከፋፈል አይደለም።
• እንኳን ኢትዮጵያውያኑን ይቅርና ከውጭ የመጡትንም አባት
አድርጋ የምትቀበል ቤተ ክርስቲያን ናት።
ስለሆነም
• የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲከበር ማድረግ
• ቤተክርስቲያን አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩሏዊትና ሐዋርያዊት መሆናን
ማስተማር ማስረዳት
• ስለ መንበረ ጵጵስና ፣ ሲኖዶሳዊ ሥርዓት ፣ ሢመተ ጵጵስና
የሢመት ሕግጋት ፣ ስለ የሥርዓት መጻሕፍት እንደ ፍትሐ
ነገሥት (ፍትሕ መንፈሳዊ) ፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያን እና ቃለ ዓዋዲ
በመጠቀም ጉዳዩ ማብራራት
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበር
ምንጭና መጽሐፍቅዱሳዊ ማብራራት
• የእስክንድርያ መንበር (መንበረ ማርቆስ) እና የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማብራራት
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወደመንበረ
ጵጵስና ያደረገችው ጉዞ መግለጽ
• የቅዱስ ሲኖዶስ ወቅታዊ አደረጃጀት መደገፍ
• የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ና የትግራይ ክልል ጳጳሳት በጦርነቱ
ወቅት ያወጁትን ዐዋጅ በደንብ ማብራራት
• የአህጉረ ስብከት አስተደደራዊ መዋቅር ፣ልዩ ልዩ
የአደረጃጀቶች (መዋቅሮች) አስፈላጊነት ማብራራት
• የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ምንነትና ምክንያታዊነት ለሁሉም
በሚገባው ቋንቋ ማስረዳት
• ምእመናን ጉዳዩን የተረዱበት መንገድና የቅዱስ ሲኖዶስ
ውሳኔን የሚቀበሉብትን ሁኔታ ማመቻቸትና መትጋት
• የውጉዛኑ ህገወጥነት እንቅስቃሴ መረጃ መሰብሰብ
ሁኔታዎችን ማጋለጥ
• ችግሩን ለመመከት የሚረዱ አፋጣኝ ዘላቂ እርምጃዎች እና
የመፍትሔ ሐሳቦች ማቅረብ፣ መተግበር።
• ተግዳሮቱን ለመልካም አጋጣሚ መጠቀም
• የአጋር አካላት በመለየት በጋራ መስራት
– እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን የኦሮሞ ልጆች መለየት፣ማሰባሰብ
– በፍትሕ የሚያምኑ የኦሮምያ ባለሥልጣናትና ሌሎች የመንግሥት
ባለሥልጣናት መለየት
– በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ የታወቁና የተከበሩ ግለሰቦች መለይት
– ልዩ ልዩ ማኅበራትና የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች መለይትና መስራት
– ሌሎች የእምነት ድርጅቶች በተዘዋዋሪ ድጋፍ ወይም ገለልተኝነትን
ማበረታት
• ዋና ዋና ሚዲያዎች እና ማህበራዊ ፕላትፎርሞች መጠቀም
•
Download