FastMereja.net - Posts | Facebook facebook.com/fastmereja/posts/pfbid02gEBCftCkYBNXiL76i5bqrK91gZUupJbJbGNvFj9X8w5WbxYyYntexz63M244rY tnl «ጎተራ » የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ ተዋወቀ ጎተራ ህይወት ንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር አርሶ አደሮችን ፣ ነጋዴዎች እና ሸማቾችን በአንድ ላይ የሚያስተሳስር እና የንግድ ስርዓቱን የሚያጠናክር « ጎተራ » የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት እና ባለሙያዎች አስተዋወቀ። የጎተራ ህይወት ንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሻምበል የሺዋስ በትውውቅ መርሃግብሩ ላይ እንዳብራሩት አክሲዮን ማኀበሩ የተሻለ እውቀቶችን ወደ ስራ በመቀየር እና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በአገር አቀፍ ደረጃ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ባለፉት አመታት ወጣቶችን የስራ ዕድሎች በማመቻቸት እንዲሁም ራሳቸውና ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ በማድረግ ረገድ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በርካታ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አውስተዋል። የግብይት ስርዓቱን በማዘመን የግብርና ምርቶችን እና ግብዓቶችን በቀጥታ ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ፣ በጥራት ፣በፍጥነት እና በታማኝነት የሚያደርስ እንዲሁም ምርቶችን እሴት በመጨመር ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡ ሀገር በቀል ኩባንያ መሆኑን ኢንጂነር ጌታሰው ማኀተቤ የጎተራ ህይወት ንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ከፍተኛ ሼር ሄልደርስ እና የቦርድ አመራር እና የቴክኖሎጂ ፈጣሪው ገልጸዋል። ከተመሠረተ አንድ አመት የሆነው ጎተራ ህይወት አክሲዮን ማህበር «ባላገሩ » የተሰኘ የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት በቅርቡ የሚያስተዋውቅ ሲሆን በዲጅታል ግብይት ፣ በእርሻ ሜካናይዜሽን እና መሠል ስራዎች ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ ተቋም ነው።ጎተራ ህይወት አ/ማ በሀገር ውሰጥ እናበወጪ ሀገር በሚኖሩ ታታሪ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተመሰረት ሲሆን ዘመናዊ የግብይት ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ የግብርና ምርቶችን እና ግብዓቶችን በቀጥታ ለተጠቃሚዎች በጥራት በፍጥነት እና በታማኝነት እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ካሉበት ቦታ ለማድረስ እየሰራ የሚገኝ ግዙፍ ራዕይ ሰንቆ የግብይት ስርዓቱን አለም ከደረሰበት ደረጃ ጋር በማጣጣም የሚሰራ የወደፊቱ የአፍሪካ ኩራት እና ተመራጭ የግብይት ስረአት እንዲሁም ታስቦ የተመሰረተ አክሲዮን ማህበር ነው። ማህበሩ የመተግበሪያ አፑን በመጠቀም ምርታቸዉን መሸጥ እና አገልግሎታቸዉን ማስተዋወቅ ለሚፈልጉ ግለሰቦችንና ድርጅቶች ምቹ ሁኔታዎቾን አመቻችቷል። በአሁን ሰአት ድርጅቱ ቴክኖሎጂ መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የግብይት ስረአትን በተለይ ገበሬ ነጋዴ እንዲሁም ሸማቹን ህብረተሰብ እሚያገናኝ ጊዜ ና ገንዘብን የሚቆጥብ አዲስ የፈጠራ ስራ ለባለድርሻ አካላት እና ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 28 2015 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘዉ ሳፋዬር አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቷል። 1/1