ወደ ራስ

advertisement
ወደ 'ራስ
ናትናኤል ዳኛው
2012 ዓ.ም
| ናትናኤል ዳኛው
ለኩኩሻ
2
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ከልጂቷ
ከነበሩበት የመቅነዝነዝ ማማ አውርዶ... የሚያነጥፍ...
እንደዚህ
ጧ
.
አ
.
አ አድርጎ
የሚጥል... ቅንዝንዝ... ሽቷም... ቅባታም... ሎሽናም...
ባለታኳም… የነበረችን... በአልፎ ሂያጅ.... ቀዝቃዛ ነፋስ…
ሽንሽን ቀሚስን ገለብ አድርጎ… የመከከ ጭንን… የማጋለጥ…
የማሾፍ… የማስቀንዘር… አባዜ… ሱስ የነበረባትን…ሰውነቱን
በቦዲ ስለወጠረ……ታቶ ስላዥጎረጎረ… የዘነጠ የመሰለውን...
ዐይኑ ፈጦ… ግንባሩ ገጦ… ምላሱ ወጥቶ..…ለሃጩ
ሲዝረበረብ…አይቶ መፈንደቅን… ሰንደቋ ያደረገችን…አውርዶ
እንደዚህ…
ዥ
3
| ናትናኤል ዳኛው
.
ው
.
ው
አድርጎ... ድባቴ በሚመስል... ጸጥታን አሳዶ...የፀሓይ ዛላን
ፈልጎ (ምእዛር ነው የሚባለው ብሎኝ ነበር ያ ቆለኛ...) አረንጓዴ
ሳር ላይ ተንጋሎ…ሰማዩን የማየት… ዙሪያን የከበቡ አበቦችን…
ዛፎችን… ቅርንጫፎች ላይ ተፈናጠው የሚዘምሩ..…
የሚንጨዋለሉ ወፎችን… እውይ!… ድምጻቸው ሲያምር…
እንድትል የሚያደርግ.… ከተንጋለልኩባቸው ሳሮች አልሞት
ባዩአ… ተጋዳዩአ… አፈትልካ ጭኔን ለመዳበስ ስትታገል...
እየተሽኮ ረመምኩ… እየተሽኮመኮምኩ…ሂሂሂሂ
.
.
ያለፈው... ምንዝር... ቅንዝር… ያልኩበት… አላጋጭ ግን
ደግሞ ብርሃናም… ጣይ… ስሁት ጨረራቸውን ልከው... እባጭ
ደረትን በስተው… ልብ የሚያባቡ... ዐይኖቸን ተማምኜ…
የባከንኩበት (ብክነት የምለው ማንፀሪያዬ አሁን ስለሆነ
እንጅ… ያኔማ… Life is not short… it’s too Short… let’s
chill out... ጠጡ እንጠጣ… ቀንዝሩ እንቀዝር... Cheers!
4
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በጠርሙ ሶቻችን… ከዛም በብልቶቻችን… ያልንበት…
ህይወትን ከትንኝ እግር አቅጥነን… ከጤፍ መጠነ ዙሪያ
አሳንሰን… እንደዛ ተሰብከን… እኛም እንደዛ ሰብከን… እያደር
የሚከስም ደስታ ያሰስንበት.…)
.
.
.
ይሁን!…መስሎን ነበራ!!… እንደዛ… (ማን ይፈራል
መውደቅ?… ክፉ አለመነሳት ነውና እሱን ፍራ)… ህይወት
ወንዝ ናት… ሁለቴ አትሻገራትም… ብለን… የረገጥነው መልሶ
ሊረግጠን… ቁማር መሆኗ ሳይገባን… ቆምራብን…
ተቆምረንላት።
መልካም ነው። ያም!…ይሄም።
.
.
.
የፀጉሬን ዞማነት (ዞማ ግን ምንድን ናት?… ፈረስ
ትመስለኝ ነበር... ካልሆነች ግድ የለም… ’ዞማዬ’ እላታለሁ…
5
| ናትናኤል ዳኛው
ስገዛ ፈረሴን… ኩንስንሴን)… የዐይኖቼን አረንጓዴ ብርሃን
ረጭነት… ጎምዥተው
“የቆየ ይያት…!” እያሉ አሳድገውኝ
...ወሬ
አንፋሾች…
ኳሾች...
ኩሸትረሃባቸው…
ጥማታቼው… ጥጋባቼው… ተቅማጣቼው… የሆነ። አፈ
ጨብጣሞች!!
.
.
ልጅናት ብለው… ሞሳነቴን ከአላዋቂነት አሰናስለው...”
እንደ እናቷ… ወንዱን ስታተራምሰው… ዕድሜ የሰጠው
ያያል።” ብለው ተንብየውልኝ… የእናቴን ስህተት (ተሳስታ
ከሆነ? ደግሞስ ማን ትክክል ሆኖ እሷ ስህተት እንደሆነች
ሳይገባኝ?)… እኔ እንድደግመው... ቢችሉ ዕድሜ ደግሞ
ካሳያቼው… የኔ ልጅም እንድትሰልሰው… በተለይ እኔን መስላ
ከተፈጠረች… እኔ እናቴን እንደመሰልኳት... (እናንተዬ
ሀጥያትም እንደመልክ ይወረሳል እንዴ?)
ሀጥያት እና ጽድቅ የእጅ አሻራ አይደለምን!?
.
.
6
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በህጻን እወዳለሁ ሰበብ…በእናቴን አቀርብሻለሁ…
በልጅሽን እንወድልሻለን ኩሸት… የልጅነት ጉንጮቼን
መጥምጠው… ሥስ ከንፈሮቸን እየዳበሱ… አሳድገውኝ…
ስኮረድድ…
ሰማይ
ቀርቦ
ያስጎነበሳቼው
እንኳ…
በምርኩዞቻቼው… ቂጤን እየጎነተሉ.......
” እናቷን መሰለች እኮ!.. መውለድ ደጉ!” እያሉ
በሾርኒያቼው አንገቴን ሊያስደፉ... ሊሰብሩኝ… ከቻሉ
በጭኖቼ መሃል ሊሰርጉ… ስርግርግ ሁላ!!
.
.
.
ጭብርሩ ወጣትስ ወጉ ነው…’ አይ አም ቅንዝራም’…
የሚል ፊት ያጠለቁ ባለትዳሮች… የእናቴ ጎረቤት ሴቶች
ባሎች… ብይ አክለው የፈጠጡ ጡቶቼን… ከለበስኳት መናኛ
ቲሸርት ነጥለው እያዩ እየጎመዡ… ሊጠቅሱኝ… በዐይኖቻቼው
ሊያባብሉኝ… እየኳተኑ... በለስ የቀናቼው ቀን… የእናቴን ባል
አለመኖር ምክንያት አድርግው… ቤታችንን ተላምደው…
ሲመጡ... እማዬ ከሌለች… ከኋላዬ ቀሚሴን እየነኩ....” ይ’ች...
እዚህ ላይ ፊን ያለችው ምንድን ነች?” እያሉ… አፍጣ መውጣት
በጀመረች የኮረዳነት ቂጤ ሊያሳፍሩኝ...መጎንተል ምን እንደሆነ
7
| ናትናኤል ዳኛው
ሊያስተምሩኝ... ውጭ ለሚጠብቀኝ... ኮረዳ የመሆን ‘ርግማን
እያዘጋጁኝ....
መጉበጥ ጀምሬ ነበር... ማጎጥጎጥ… መኮርደድ…
እርግማን እስኪመስለኝ ድረስ... ሲያበሽቁኝ… አላጎጠጎጥ ኩም
ለማለት…ደግሞ ‘ጎባጢት’ የሚለው ልጥፋቼው… ከማጎጥጎጥ
የከፋ ሆኖ...እስኪጠዘጥዘኝ ድረስ…
እግዜር ሆይ ለምን ለልጅነታችን አልተውከንም?
.
.
.
የጡት አብዮት ተነሳ... አሸማቃቂዎቻችንን ማሸማቀቅን
አጽሙ ያደረገ... የሚያብረቀርቅ የጡት ስንጥቅን አጋልጦ.…
የጡት መልክን የሚገልጡ… ስስ ቀሚሶችን ቀምሶ… አዳምዬን
የማዥረብረብ... አብዮት!! መልሶ የግብዝነቱን ሰበብ…
ቀሚስን እንዲያደርግ... ይህ የጡት አብዮት ነው!!
ጡት ይወድ የለ…በተለይ ወንድ ደግሞ............
“ከሳች እኮ!!” ሲባል
“እያጠባች ነዋ!?”
8
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
“ደ’ሞ ወንድ ነው መሰለኝ የወለደችው?”
“አዎ…”
“እ… እሱማ ስቦ ነው የሚጨርሳት!!” ነውና ከነ ወጋችን
እንኳ....…
.…የወጠጠውን (ምነው... እዚህ እድሜ ላይ ጅልነት
ይበዛልሳ?) የገረጀፈውን… ለበቀል.… በሚወደው ተሰለ
ፍንበት… በጡት!!.… ውጥር… ሾል… ግትር ያለ ከሆነማ…
አለቀ… ትንሽ ዘይት እላዩ ላይ ደፋ አድርገሽ...
እንዲያብረቀርቅ… እንዲያጥበረብር ይደረግ እና... ከፈት ሰሳ
ያለች ‘ስከርት ከላይ ጣል ተደርጎ.… አጉልቶ የሚያወጣ...
የተንጀላጀለውን ሳይቀር... ተራራ የሚያስ መስል… የክርታስ
ማቀፊያ ታጅሎ.... ዝ የጡት አብዮት!!!
.
.
አሁን ያ ጊዜ አልፏል...በተለይ ለ’ኔ። ከእንዲህ አይነት
የህይወት መንደባለል ወጥቼ መኖር ከጀመርኩ ሰነባብቻለሁ።
ለብዙ ጊዜ መሰልቼቴ ይታወቀኝ ነበር። ሲነጋ ከጎን የማያገኙትን
ገላ አቅፎ ማደሩ.…ጠረኑን ከማያስታውሱት... አልፎ ትዝታ
ከማይቀሰቅስ...አልፎ
ሂያጅ ገላ
መጋራቱ... ጠረን
መማጉ...እያቆሰለኝ ነበርና።
9
| ናትናኤል ዳኛው
.
.
.
መውጣትን ሳቅድ ቆይቻለሁ… ግን ያለፋል…የምድር
ክብነት… ያደክማል... መልሶ መላልሶ እዛው ነው። በቃ
እስኪል… እግዜርዬ… አዙሪቱ ሲበቃው ወይንም በቃህ ሲባል
ያስታውቃል… ልባችሁ ወይን ሳይጠጣ ያርፋል… ፊታችሁ ላይ
ወለላ ይዘንባል... ያም ይሄም… ያያ ሁሉ..” ከፊትሽ ወዘና
አስቀጅንና የእኛም ልብ ትረፍልን…” ይላል
.
.
አልፎ አልፎ ነፋሱ እያመጣ አፍንጫዬ ውስጥ
ከሚሞጅረው የትንባሆ ሽታ በቀር በናፍቆት የሚወሰውሰኝና
ኋላዬን የሚያስናፍቀኝ ነገር የለም። ዛሬ ንቁና ብቁ ለመኾን
ሜታምፎታሚንስ* መዉሰድ አይጠበቅብኝም። ድሮውንም
ፍቅር መሳይ ነውና እንዲህ ያደረገኝ።
ፍቅር ደርጋማው... መደናበስ ሲወድ!?
.
.
10
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
.
የወደድኩት መሰለኝ... ደግሞም የወደደኝ... ከብቸኝነት
ሙዳዬ በተስረቅራቂ… እንዲያውም ቀለሙ ራሱ ሰማያዊ
ይመስለኛል… በዛ ቀለማም ሳቁ ጠርቶ አውጥቶ... እንትፍ
ብቸኝነት… ደግሞ የምን ማሰብ አቦ... ፋሻ ነው እንጅ...
ብሎኝ... አምኜው... የሼሚዜን ቁልፍ ፈትቶ… ፍንድቅ
ጡቶቼን ሲዳብሰኝ... ሳልከለክለው (ደግሞ የኮረዳነት መሻት
ተቋጥራ አለችበት) የእንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ሂሳብ ክፍለ
ጊዜዎችን...በለዛው አስረስቶኝ።
.
ሳቁ.... ሂሳቤ (ሳቅን Undefined የሚያደርግ ኢኮዥን
የላችሁም?)
ዐይኑ.......... ፊዚክሴ
ፍቅሩ እና ጨዋታው....…ኬሚስትሪዬ
ወሬው....... ሂስትሪዬ
......ሆኖኝ እሱን ስማር… ስመረምር… መመራመር አፈር
‘ፈተናው ደረሰን ምንም ሳለጠናን…’ በጋራ ዘምረን ነበር።
11
| ናትናኤል ዳኛው
ጊዜ እንዴት ሃያል ነው ጃል!? ስንቱን አየን በዚች ነጥብ
ዕድሜ?
.
.
.
የምቆጭ አይነት አይደለሁም...ያተረፍኩት...’ፍቅር
ምንድን ነው?’.…’ የትስ ነው ያለው?’...’ትናንት ያን ሁሉ
የሆንኩለት…ልጅህን በመንገዱ ምራው ባደገ ጊ ዜ ከዛ ፈቀቅ
አይልም ባይ እናቴ ያሲያዘችኝን (ከራሷ ተምራለችና) ፈር ለቅቄ
ከፈሩ የተደባለቅኩለት… ኩሸት ነበርን?’.....ማለት ቢሆንም.…
.
.
.
ደስተኛ ነኝ ከነጥርጣሬዬ።…ዛሬ ቢያንስ የዚች ወፍ ጩኽት
ያሳርፍኛል... የሰላላ ሳር ዳበሳ ያነቅኛል… በ’ነሱ የህይወት
ረቂቅነት ይገባኛል። ተራነት ውብ ነው። የትናንት መጓጓቴ ዛሬ
የለም... አብሮኝ ያለው ሳር ላይ አንጋሎ… የጠራውን ሰማይ
እያሳዬ ሰላም የሚሰጠኝ እረፍቴ ብቻ ነው። ይሁን ሰላም ውብ
ነውና!!
12
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ነገ ሆይ መጣውልህ!!… የተስፋ መንገድ እስከሞት ነው…’
የምንኖረው ሞታችንን’ የሚያኖረን ደግሞ ተስፋችን ነው።
አንድ ዕለት፦ ወጀቧማ ነበር… ነፋሱ ቅዝቃዜውም
አነፋፈሱም… ለሰው አይመችም።… ከበሬ ለግታ ያለች ትንሽየ
ሶፋ ላይ ቡልኮየን ተኮናንፌ ተቀምጨ ውጭ ውጩን
እማትራለሁ… ሰው መጣሁ ብሎ የቀረብኝ አይነት። ፊት ለፊቴ
ቀጭን የሚም ዛፍ ትታየኛለች… የዛፏ አንደኛ ቅርንጫፍ ላይ
ደግሞ ሞሳ እርግብ(ሌላው የዝንብ ጠንጋራ አውቃለሁ ብሎ
ይዘባነናል… እኛ የእርግብ ሞሳ እምናውቀው ምን እንበል?)
…ነፋሱ ቀጭኗን ዛፍ ያላጋታል… የመሰበር ያህል አጎንብሳ
ትቃናለች። የቀጭኗ ዛፍ ቀጭን ቅርንጫፍ ላይ ያለች እርግብ
ግን በሰላም ታንቀላፋለች። …ገርሞኛል!። ዛፏ ይህን ያህል
እየተላጋች እንዴት እርግቧ አትረበሽም?... ምናልባት እየሆነ
ያለውን የሚያሳውቅ ህልውና አይኖራት ይሆን? እላለሁ።
ህይወት ያለው ሁሉ ደህንነቱ የሚያሰጋው ይመስለኝ
ነበር። ይሄ እንግዳ ቢሆንብኝ… ወይንስ በክንፏ ተማመነች?…
ክንፍ አገልግሎቱ ለመብረር እንጅ የምትላጋ ዛፍ ቅርንጫፍ
ላይ ሆኖ ላለመረበሽ አይመስለኝም... ወይንስ ተስፋዋ
ቅርንጫፏን ቆልፋ በያዘችበት እግሮቿ?… ይሄስ ቅርንጫፏን
ተገንጥላ ከመውደቅ ይታደጋታልን?... እላለሁ::
የዚች እርግብ ሰላም እንዲኖረኝ ተመኜሁ.… በወጀብ
መሃል የሚያፀና... ውጭ ስለሚሆነው አስረስቶ… በራስ ገላ
13
| ናትናኤል ዳኛው
ውስጥ ባለ ኃይል የሚያስተማምን... የራስ በሆነ ክንፍ
የሚያስመካ።
ይባልስ የለ “መርከብን የሚያሰምጠው በዙሪያው ያለ
ወጀብ ሳይሆን ውስጡ የሚገባ ውሃ ነው!”... እንዳዛ እንደዛ!!
~
* ~
14
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ኪልኪልታ... የህይወት ደዎል
ሰማዩ ምነው ዳመነ? …በጠራራ በጋ ምን ሆንኩ ብሎ ነው
ያኮረፈው? …ፀሓይ ጋር ለምን ተኳረፉ? ...አኩርፋ በደመና
ተከለለች? …ወይንስ እሱ አኩርፎ ከለላት? …ይሄ ተሲያትስ
ለምን ረዘመብኝ? …ምን እንደሆነ በውል ባይነግረኝም…
ውስጤ አዲስ ነገር መሞከር ፈልጓል... ይመስለኛል።
~
* ~
እየጠበቃት ነው... ዙሪያውን ክብ የሰሩ የካፌ
ጠረንፔዛዎችና ወንበሮች..… በሰዎች ተሞልተዋል… ጉራማይሌ
ሰዎች… ጉራማይሌ ትዕዛዞች። የሴቶቹ ሳቅ አድፍጦ እየቅየ…
ቡግግ ይልና… የካፌውን የዝምታ ቆሌ ያስደነብረዋል።
በሰዎች የተሞሉትን ወንበሮች እያስተዋለ …ጥግ ላይ
ብቻውን ተቀምጧል... የቀረችው መዘግየት... ሲብስም
መቅረት። የሚመጣው ድንገት ብትመጣ እንዳታጣኝ እያለ
ነው። መቅጠር… መቀጠር... መዘግየት... መቅረት… ሲሞላ
ሲጎድል… እንደ ህይወት።
ሰዎች እህትህ ቆንጆ ናት ይሉታል... አይናደድባ ቸውም...
አብረው ሲሆኑ እንደዛሬው ቀጥራው… አስጠብቃው
15
| ናትናኤል ዳኛው
ስትመጣ… በዙሪያቼው ለሚኖሩ ወንዶች ‘ወንድሜ ነው
ትላቼዋለች’።
እንደታናሿ እንደምትቆጣው… እንደምትመክረው…
ደግሞ ቦርሳዋን በርብራ የሻይ ብላ ጥቂት የብር ኖቶቸን
እደምትሸጉጥለት ያደርጋትል። ድሮ ድሮ ይሄ ፀባዩአ
ሲጀማምራት… ሲረዳት… ከልቡ ተነስቶ እየፋቀው…
እየቧጠጠው… በደም ስሮቹ አድርጎ… ዐይኖቹ ላይ ተቁቶ
ሊደፋ የሚታገለውን እንባ አንጋጦ ሊመልሰው እየታገለ…
ድልህ የመሰለ ፊቱን… በጠይም ረዣዝም ጣቶቹ ያራግባል።
ደጋግሞ ውሃ ይጠጣል… ጨውን ውሃ… በጣዕም የለሽ ውሃ
ሊመልስ!!
ምክንያቱ እሷ እንደሆነች ብታውቅም… ፊት ለፊቷ
ማኪያቶ… ቡና… ሻይ… ካፑቹኖ... ወይንም ቢራ...
ጠረንፔዛቸውን ለሞላው ወጣቶች የአዛኝ ፊቷን ፎቶ ልትረጭ
ቅጭም (ይሄ ቃል ሲያስቀኝ) ትልና እጇን ሰዳ ክንዱን
ትዳብሰዋለች።
...ይታለላል.… ሆዱ ውስጥ ያለች ቢራቢሮ እየተርገ
በገበች..… በክንፎቿ ልቡን ኮርኩራ ታስቀዋለች…ፈገግ ብሎ
እጆቿን በእጁ ሊይዝ ሲሞክር ታሸሻቼዋለች።
[....]
Her fingers number every nerve,
16
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
Just as a miser counts his coin
She lives upon his shrieks $ cries,
And she gets young as he gets old.
[…..]
William Blake
~
* ~
ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ይሄ ነገር... ሊተውኝ የማሳዝናቼው...
አብረውኝ ሊሆኑ የምሰለቻቼው ናቼው በመንገዴ
የተገደገዱት። ይሄን ነገርም ለምጀዋለሁ ብየ አስብ ነበር…
ወድቋል ሲሉኝ እየተነሳሁ... ዘገየ ስባል ከፊት እየተገኜሁ ነበር
እዚህ የደረስኩት... ታዲያ ለምን ለ’ሷ ሲሆን ከበደኝ??
ቀሽም ነው!…ጌታን ፍቅር ቀሽም ነው!!
~
* ~
እሁድ ማለዳ ነበር ወላጆቹ የኮቷ እጅጌ ከልኩ የተረፈች
ካኪ ሱፍ አልብሰውት… በእጁ ቡናማ ደረቅ ልባስ ያለት የአዲስ
ኪዳን መጽሓፍ አሲዘው ወደ አጥቢያ የማምለኪያ
ቤተክርስቲያን ወሰዱት። ሞሳ ነበር… የአራት ዓመት ግልገል።
17
| ናትናኤል ዳኛው
የካቴድራሉ አዳራሽ አራት ማዕዘን ነው። ከፍ ያለ
መድረክ... ከመድረኩ ፊት ለፊት ከሁለት የተከፈለ የአግድም
ወንበሮች ሰልፍ ያለው። በቀኝ በኩል ካለው ሰልፍ …
የመጀመሪያው አግዳሚ ወንበር ከወላጆቹ መሃል ተቀምጦ...
የሚዘምሩ ህጻናትን እያዩ እናቱ “ናታንዬ…” አለችው አፏን
አሞጥሙጣ የጆሮዎቹ ቀዳዳ ላይ ለግታ… የሞሳ ፊቱን አዙሮ
ሲያያት “ኳየር ውስጥ ላስመዝ ግብህ?” አለችው… ቀልቡ ግን
ከህጻናቱ ይልቅ ፒያኖ የሚኮረኩር ቀይ መላጣ ሰው ላይ አርፋ
ነበር “እንደ ሰውየው…” አላት - በሌባ ጣቱ እየጠቆመ።
ደስ ብሏታል.… ፀጉሩን ዳብሳ ወደ ባሏ ዞራ ተንጠራርታ
ሹህ አለችው። በፈገግታ ተውጦ ፊቱን ወደልጁ አዞረ… ናታን
ከፒያኒስቱ የእጅ እንቅስቃሴ ጋር… ዐይኑን ያንዤዋዥዋል።
…እናቱ ‘ቤሪ ከበደ’(?) እሱን ከመውለዷ በፊት… አባቱን
አግብታ ፕሮቴስታንት ከመሆኗ በፊት…ዓለማዊ ሙዚቀኛ
እንደነበረች ማን ነግሮት?
~
* ~
ፒያኖ ከህይዎቱ ቀጭን ክር ላይ ተጠልፎ ዜማ መስጠት
ጀመረ። የሞሳነት ቀጭን ጣቶቹን እንደፈቃዱ የፒያኖው ሆድ
ላይ እያተራመሰ እያንሼራሼረ… ያስለቅስ፣ ያስፈነድቅ ያዘ።
18
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ እሁድ የአምልኮ መድረኩ ላይ ወጥቶ
ወላጆቹንና አምላኪዎቹን በእንባ ችርስ የሚያባብልበት.…
የሙዚቃ ኖት ይፅፋል…ያጠናል።
ከሙዚቃ የሚለይባት አፍታ…ከዕድሜ እየረዘመች...
ድብታ ይጫጫነዋል። ከፒያኖው ሲለይ ሞጋስ የለውም...
ይገረጣል… ይነጣል… ይደበራል።
መድረኩ ላይ ከፒያኖው ጋር ሞገሱን አይተው
የማለሉለት ኮረዳወች …ያለዕረፍት ከተደበቀበት የፒያኖው
ዋሻ… የሙዚቃ ገዳሙ... እየጎተቱ …ከራሱ ወጥቶ እነሱ ጋ
ሲመጣ...ሞገሱ
ሲያንስባቼው...
ከዕድሜው
‘ርቆ
ሲገረጅፍ…እያዩት ሲገረጣ…እዛው ዋሻው መልሰው ትተውት
ይሄዳሉ… ይተውላቼዋል።…ደግሞ ያገግማል…የፒያኖው
ስቅስቅታ ወዳጅ ሆኖት… እንባውን ተጋርቶለት…ደግሞ
አስቆት።
ህይወት ክብ ሆና መልሳ እነሱ ጋ ስትጥለው… ሲጥሉት…
ሲነሳ
.
.
.
እየጠበቃት ነው………ሁለት የውሃ ኮዳዎች…አንድ
የላስቲክ ጠርሙስ ከጠረጴዛው ላይ...ሁሉም ተጨልጠው
ባዷቼውን የቀሩ…..ደለል ያረገዘ የቡና ስኒ።
19
| ናትናኤል ዳኛው
በማንኪያ የቡናውን ደለል ያተራምሰዋል...ሰልችቶት
ይተወዋል። ማንኪያውን ከስኒው ሆድ አውጥቶ…
የማስቀመጫ ክብ ሸክላው ላይ ሲያስቀምጠው ‘ኪል’
አለ…አነስቶ መልሶ ጣለው... ’ኪል’ አለ።
ጆሮው ዜማ የሰም መሰለው…… ጣቶቹ የማንኪ ያውን
ቂጥ
አንቀው…
ዜማ
ለማውጣት
ፈጠኑበት።
…ቀሰስ…ለሰስ…እያደረገ ሸክላው ላይ በማንኪያ ኖት መሳል
ጀመረ።
…ህመሙ… ፍቅሩ… በሚወጣው ውስጥ ሲጥም ሲገዝፍ
እያሰበ ዐይኖችን ከድኖ ለራሱ ግጥም ሊያወጣ……
አትመጣም አውቃለሁ...ግዴለም ባትመጣም
ከመቅረቷ ይልቅ…መምጣቷ ነው የሚያም
እ…ኪል…ኪልል…እ…እ’ም… ህም…ህመም
ፍቅር ያደክመኛል... አድክሞ ሊገድለኝ
ሰው መሆን አስንቆ… ክርስቶስ ሊያረገኝ
ኪ...ል.…ኪ…ል…ል…
ትናንት ገድላኝ ሄደች…እኔም ሞትኩላት
ደግማ እንድትገ’ለኝ…ዞሬ መጣሁላት
20
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
..ኪል…ኪልል…’ህም…ህመም
~
* ~
“ሃና እባላለሁ…ጣቶችህ የተባረኩ ናቼው” አለችው…
አጎንብሶ የፒያኖውን እግሮች እየፈታ ነበር። የአምልኮ ሰዓት
አብቅቶ…ሁሉም አዳራሹን እየለቀቀ ሲወጣ…ስስ ቡናም
አጭር
ቀሚስ
የለበሰች
ጠይም…አማሃይ
ቁመት
ያላት…ፀጉሯን ልጋ ከጀርባዋ አስተኝታ..ጥቁር መጽሓፍ ቅዱስ
ያቀፈች ሴት።
በአጎነበሰበት የታዩት ከጫማዋ አፈትልከው የወጡት
የእግሮቿ
ጣቶችነበሩ።…ረዣዥም
ቢሆኑም
የታጠፉ
ናቼው…ጠባብ ጫማ ያጎበጣቼው አይነት።…ምናልባት
ስታድግ በእሷ ‘ልክ’ ያልነበሩ ሽፍን የጎማ ጫማዎች አዘውትራ
ይሆናል።
((ልክ ግን ስንት ነው?…አንፃራዊ ነው። በጊዜና ቦታ
የሚለወጥ። ልክ ማለት ናታን ነው።
ልክ=ናታን
እዛ የአዳራሹ መድረክ ላይ ከፒያኖው ጋር የታየው
ሞገሳም ናታን እዚች ካፌ ከሙዚቃው ተነጥሎ ባለበት
ብትፈልግበት አታገኜውም። እነዛ እንስቶች ከሙዚቃው፣
የፒያኖውን ሆድ ሲያስጮህ… ፊቱ ተቀምጠው ዘላዓለም
21
| ናትናኤል ዳኛው
ድረስሊሰሙት ሊያዩት ይችላሉ… ውበቱ
ሳይነጥፍ። ሲነጠል ይኮሰምናል…ይገረጣል።
ከዐይናቼው
በልጅነት እግርህ ልክ የተገዛልህን ጫማ አድገህ
ልትለብሰው አትችልም።…እዛ አዳራሽ ልኩ ነው ብለው
በውዴታ የቼሩት ከፒያኖው ውጭ ሲያገኙት ይሰፋዋል።))
…እፒያኖው ስር ቁጢጥ እንዳለ ቀና ብሎ ሲያያት
መልሳ…”ሃና…” ብላ እጇን ዘረጋችለት።
~
* ~
እየጠበቃት ነው…. ከዜማው ጋር እንባው መፍሰስ
ሲጀምር… ጫንቃውን… ሁለት ትከሻውቹን… ሁለት እግሮቹን
አንፈራጦ… በጥፍሮቹ ቧጦ ይዞት የነበረ… ጥቁር አሞራ
ተነስቶ የበረረ ያህልሰውነቱ ሲፍታታ ታወቀው።…አይኖቹ
እንደተከደኑ ለአፍታ ፀጥ ብሎ ቆይቶ በሃይል ተንፍሶ ተዘረጋ።
ያላያት…ከኋላው መቼ መጥታ እንደተቀመጠች
የማውቃት ቀይ ሴት የብርጭቆ ውሃ ይዛ በጣቷ ጠንቁላ ፊቱን
ስትረጨው ደንግጦ ነቃ።
.
.
.
ሃና ደጋግማ እየደወለችለት ነበር…ለሳምንት ያህል
በዝምታ ተመለከታት። እልኋን ባያነሳላትም ደጋግማ
22
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በመደወል
ልታሳየው
ሞከረች...ቆይቶ
መሰናበት…
ማሰናባት…እንዳለበት አስቦ…የፅሑፍ መልዕክት ላከላት
“ምን አልባት እንዲህ ለመሆንሽ(እስቲ ምን ሆንኩ ብለሽ
ጠይቂ)…የኔ ድርሻ ብዙ ሊሆን ይችላል…ወይንም
ምንም!..በተፈቀደልኝ መጠን ልታግስና ልረ’ዳሽ ጣርሁ..ይሄስ
ገብቶሽ ያውቃል?። ባለፈው እዛ ቦታችን ሆኜ ምን እያደረግኩ
ነው? ብየ ጠየቅኩ…መጠየቅ የመለየት ጅማሮ ነውና…የዛኔ
ማብቂያው ላይ እንደደረስን ገባኝ።
ልብ
የሚያጠፋው
ሳቅሽ…ስልብ
የሚያደርገው
ዐይንሽ…ፍቅሬን
ቢያብሰውም…ለስህተትሽ
መሸፈኛ
ስትጠቀሚበት ማየት ግን ክብርሽን ያጎድለዋል።…ክብር የአቦ
ዝክር ነውን?…በርግጥ ነው እንደዳቤ ተቆራርሶ ያልቃል።
ስለምወድሽ ብቻ ሳታከብሪኝ…ሳላከብርሽ…የምኖር ጤባ
አይደለሁ እኔ…ይህስ ገብቶሽ ያውቃልን?
አትስጊ በልቤ ቂም የለም…ቂምስ የደካም ልብ ተግባር
አይደለ?…ልቤ ሰነፍ አለመሆኑን ታውቂያለሽ።…ደህና
ሁኝ…ደህና
ልሁን…ደህና
እንሁን…ያሳለፍናቼው
አያረሳሱንም።”
23
| ናትናኤል ዳኛው
ፀሓይና ፀሓይ
ህመም ነው አምቀው ሲይዙት የሚብስ……
እንደምወዳት አታውቅም አይደል?… አትወቃ!!… እኔስ
እንድታውቅ መች ጣርኩ? አልጥርምም። ደስታዬ “እንዴት
ናት?” ከማለትና ከሁኔታዎቿ ”ምን እየተሰማት ነው?” ከማለት
የዘለለ አልነበረም።
ማለዳ የጊቢያችን በር ላይ ወጥቼ እቀመጣለሁ።
ከቤታቼው ጓሮ ሾልካ ከምትወጣው ፀሓይ ጋር እሷ ፒጃማዋን
ለብሳ…በ’ጇ የአስር ብር ኖት ጨብጣ ዳቦ ለመግዛት
ትወጣለች።
የጧት ፊቷን አይቼ አዳሯን ለመረዳት እሞክራለሁ ጸጉሯ
በሻሽ ከተጠቀለለበት አፈትልኮ ጫንቃዋ ላይ እንደተኛ ነው።
ፊቷ በዉሃ ነጠብጣብ ተውጧል።
ሁልጊዜ ከቤቷ የምትወጣው በውሃ የራሰ የቅንድቧን
ጸጉር በጣቷ እየላገች ነው…የታጠፈ ክረምት አግባ የመሰለ
ቅንድብ አላት…ምላጭ አልነካውም…ክፈፉ ተገጥቦ አይቼ
አላውቅም።
ፒጃማዋ ትንሽ ሰፋ ያለ ቢመስልም…ስትራመድ ግን
ከሰውነቷ እየተለጠፈ የሰውነቷን ቅርፅ ያወጣዋል።
24
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
~
* ~
“ጠዋትና ማታ ውጭ ላይ የምሰጣው ፀሓይ ስትወጣና
ስትገባ ለማየት ነው።” ብየ ተቀኚቼባታለሁ… እሷ ግን የገባት
አትመስልም። ጠዋት ከማየው አዳሯን… የስራ ቦታዋ ውላ
ስትመለስ ከምሽኜው ደግሞ ውሎዋን ለማንበብ እንደሆነ
አልነገርኳትም።…ቢሆንም ግን ጥቂት ለማይባሉ ጊዜያት
አድርጌዋለሁ።
ጠዋት ፀጉሯ ተፈላልሶ ሳየው ሌሊቷ በቅዠት የተሞላ
እንደነበረ ገምቼ ፍርሃቷን ላስስ እሞክራለሁ።(ምክንያቴ ምን
እንደሆነ ባላውቅም አብረዋት ከሚኖሩት በ’ሷ ልጠረጥረው
የምችለው ወንድ የለም።)
ጧት ከቤቷ ስትወጣ ሰላም ያየሁት ፀጉሯ ከስራ
ስትመላስ ተፈላልሶ ካገኘሁት…የሆነ ምንትስ የሚባል ሆቴል
ማንትስ ከሚባል ወንድ ጋር እጠረጥራታለሁ።
ይሄን እሷ አታውቅም.…
እንደሚገለባበጥ።
.
.
አዳሬ
እንደሷ
ሁኔታ
.
አልጋየ ላይ በጀርባየ ተንጋልዬ ተዛንቃ ያየኋትን
እያንዳንዷን የፀጉር ዘለላዋን ጧት ባየሁባት ሁኔታ
ላስተካክላት ስሞክር አድራለሁ። ወረቀት አውጥቼ በእርሳሴ
ይች ዘለላ እዚህ ጋ ነበረች...ያ ች! ደግሞ እዛ ጋ…እያልኩ
25
| ናትናኤል ዳኛው
አሰልፋቼዋለሁ። ይች የፀጉሯ ዘለላ እዚህ ተነስታ እ…ዛ ጋ
እንዴት ደረሰች?..…ምናልባት ያደረጉት wild sex…ሊሆን
ይችላል!።…እሷ ፈረስ እሱ ፈረሰኛ ሆነው ጋማዋን ይዞ
ሲያሰግራት ነበር ማለት ነው?…በዚች የፀጉር ዘለላ እና
በዛችኛዋ መሃል…አንዲት ቀጭን ዘለላ ነበረች…የት ገባች??
ስትነጭ
ጣቱ
ውስጥ(ምናልባት
ቀለበቱ
ውስጥ)
ተሰክታ...ለመጣል እጁን ሲያርገፈግፍ ይታየኛል።
.
.
.
ዐይኖቼ ለአፍታ መከደን ሲጀምሩ.…በሷ ስም አእምሮዬ
ላይ የተሰነቀረ አውራ ዶሮ መጮህ ይጀምራል።…ወዲያው
ተነስቼ ሦስት እግር ኩርሲዬን ይዤ እወጣለሁ።
ብዙ ጊዜ የምደርሰው ጨለማና ብርሃን የሚገናኙባት
ቅፅበት ላይ ነው።…ወዲያው በሰላማዊ ርክክብ ጨለማው
ብርሃኑን ወደ ውስጥ አስገብቶ ሲያንሰራፋው በሰው ልጅ
አቆጣጠር ቀን ይሆናል። ይህን ማየት የምንችለው…
የቻልነው…ምን ያህሎች እንደሆንን አላውቅም።
እንደ’ኔ የጨለማና የብርሃን መገናኛ ላይ የሚታደም ሌላ
ሰው የማውቀው ፊሽን ነው።..እኔ ሦስት እግር ወንበሬን
አንጠልጥየ የግቢ በር ከፍቼ ስወጣ… ፍስሃ ምድር
‘ርቃው…መቆም ተስኖት…እየተንገዳገደ የእናቱን በር አስከፍቶ
26
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ይገባል። እሱ ወደ ሌሊቱ እኔና መሰሎቼ ወደቀናችን
እንሰለፋለን።
የፀሓዩአ ጨረር እየጎላ ሲመጣ ነው ሰው ወደ ላይ እና
ወደታች መራወጥ የሚጀምረው። እሷም የዛኔ…የፊቷ ውሃ
ሳይደርቅ የቁርስ ዳቦዋን ልትገዛ ትወጣለች። ከማውቃቼው
ወጣት ሴቶች የፊት ቀለማቼውን በትክክል ለይቼ የማውቀው
የእህቴን፤ ወላጆቼ ቤት የተከራዩ ሁለቱ ሴቶችን እና የእሷን
ነው። እነዚህንም ቢሆን በማለዳ ስለማውቃቼው እንጅ
ከቁርሳቼ በኋላ ወደስራ ሲወጡ ያለው ሌላ መዛነቅ
ነው…መጣረስ...ምናልባት
ራስን
እንዲጠረጥሩ
የሚያደርግ(ይሄ ነገር እስካሁን አልተጠናም አይደል?)
እሷን
እንደምወዳት
ብነግራት.…ጧት
ከቤቷ
ስትወጣ…ማታ ወደ ቤቷ ስትገባ…ተቀምጨ የምታገኜኝ እሷን
ጥበቃ እንደሆነ ብነግራት…ፊቷ ላይ ከምታጠልቀው ጭንብል
ቀለም ይልቅ…..ማለዳ በውሃ ስትታጠብ ፊቷ ላይ የነበረው
የተሻለ እንደሆነ..ያ ይበልጥ እንደሚ ያምርባት… እኔም አልቄ
እንደምወደው… እነግራት ነበር። ፀጉሯም የሚያምረው…ጧት
ከቤቷ ስትወጣ እንዳበ ጠረቼው..… ሰላም እንደሆነ
እንጅ...አንዳንድ ማታ ቤቷ ስትገባ… ብዙ የፀጉር ዘለላዎቿ
ቦታቼውን ስተው ሲፈላለሱ እንዳልሆነ አስረዳት ነበር።
~
* ~
27
| ናትናኤል ዳኛው
እርጥብ እጇን የፒጃማ ቲሼርቷ ላይ እየጠረገቼ…
ሰላም..ካለችኝ በኋላ…ዝቅ ብላ ከቁምጣ ተርፎ በፀጉር
ከተሼፈነው እግሬ ላይ አንዷን ፀጉር ስባ ቆንጥጣኝ ታልፋለች።
ህመሙ ፀጉሯ ተፈላልሶ የማየውን ያህል አይህንም…ቢሆንም
ግን ሳቋን ለመስማት አክብጆ እታመመዋለሁ።
ሁለቱ ህመሞች … የፀጉሯ መፈላለስ እና የእግር ፀጉሬ
መነጨት.… በህመም ደረጃ እኩል ናቼው።
ልዩነታቼው፦በፀጉሬ መነጨት የመጣው ህመም የአፍታ
ህመም መሆኑ ነው።…ሁለቱም በሷ ደስታ ላይ የተሳሉ
ህመሞች
ናችው።
ልዩነታቼው
በፀጉሯ
መፈላለስ
የምታመመውን ዝልግልግ ህመም አታውቀውም።
የእግሬን ፀጉር ነጭታ… በአፍታ ህመሜ ትፈነድ ቃለች።
የአፍታዋ ህመሜ ስታልፍ…አብሮ ካላለፈው ሳቋ ጋር አብሬ
‘ስቃለሁ። ይህን ለምን እንደማደርግ አታውቅም…ወይንም እኔ
እንደምታውቅ አላውቅም።
መውደዴን ብነግራት… ሌቶቻችንን አብረን አሳልፈን
ቀኖቻችን
አብረው
ቢጀምሩ…ነፀጉርሽ
መፈላለስ
የታመምኩትን ዘላለም መሳይ ህመም ረስቼ… ከሳቅሽ ጋር
አብሬ እስቃለሁ እያልኳት ነው።
.
.
.
28
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በየቀኑ እየወፈረች መሄዷን አስተውል ነበር… ፊቷ…
ሽንጧ መሙላት ጀመረ። እየቆየችም ብርጫም እየሆነች
መጣች… ”ምነው ተዝረከረከች?” ማለት አበዛሁ ለራሴ።
ፒጃማዋ ተለውጦ…ሰፋፊዎችን ማዘውተር ጀመረች።
ከስራዋ ስትመለስም ለብሳ የማያት ከዚህ በፊት
የማላውቃቼውን ልቅ ቀሚሶችንና ቲሸርቶችን ሆነ።…እግሯ
እያበጠ እንደ መንከስ አለች።…ከወራት በኋላ ሆዷ ወደፊት
ጎልቶ ወጣ።…የዛኔ ማርገዟ ገባኝ።
.
.
.
ፀሓይን ተሻግሮ ፀሓይ አለ ወይ፦ ከዚህ በኋላ ውጭ
ወጥቼ መቀመጥ ተውኩ።…በሁለተኛው ቀን ‘ግቢያችን
ውስጥ ተቀምጨ ‘ምዕዛር’ የሚል መፅሃፍ እያነበብኩ በር
ተንኳኩቶ ታናሽ እህቴ ስትከፍተ....እሷ ናት።
እዛው በሩ ላይ እንደቆመች እህቴን “የት ሄዶ ነው ሰሞኑን
ያላየሁት?” ስትላት ሰማሁ…እህቴ “ያው እዛ..” ብላ
ወደተቀመጥኩበት አሳይታት ተመለሰች።
“እ…ሰውየው…ፀሃይን
ማየት
አቆምክ
እንዴ?”
አለችኝ…እዛው ባለችበት ሆዷ እንዳይታይ አንገቷን ብቻ
አስግጋ
“ሌላ ፀሓይ ግቢያችን ውስጥ ተገኜች!” አልኳት…በቀስታ
ሳቀች
29
| ናትናኤል ዳኛው
የእግሬን ፀጉር መቆንጠጥ የናፈቃት ትመስላለች። እግሬን
ዝቅ ባላ ስታይ ሙሉ ቱታ ለብሻለሁ…የእግሬ ፀጉር አይታይም።
እዛው በቆመችበት ከንፈሯን ነከስ አድርጋ… በጣቶቿ
የመቆንጠጥ ምልክት አሳይታኝ ሄደች።
30
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ወደ ‘ራስ
“እውን እኔ ይች ነኝ?” ትላለች… ራቁቷን ከቁም
መስታውቱ ፊት ቁማ። ገንዳ ዉስጥ ገላዋን እየታጠበች
ሰውነቷን ስታዳብስ… ከወትሮው የተለየ ነው የተሰማት። …”
ጥድፊያ ውስጥ ሆኜ ራሴን ያወቅኩበት ጊዜ የለም…የመጣደፍ
አቅሜ ከእድሜዬ ጋር አብሮ ነዉ የጨመረው።” እያለች ገንዳ
ውስጥ የተዘረጋ ራቁት ገላዋን አተኩራ እያየች ትዳብሰዋለች።
በአፍላ የውርዝና ዕድሜ ስደት ደብዳቤ ልኮላት ጊዜ
ተነጥፎ ከሚተኛበት ሃገር አውሮፕላን ወደሆነበት መጣች።
ከት/ትና ከስራ የተረፋት ጊዜ የለም።
“በየአደባባዩ ቆንጆ ሆነው ከሚታዩት ሴቶች ስንቶቹ
ከጋላችው ጋር ይግባባሉ? ሰውነታቼውንስ ያውቁታል?” ብላ
ስትጠይቅ ነው ገላዋን ማስተዋል የጀመረችው
-የጡጣቼው ጫፍ ላይ ያለች ክብ ጥቁረት ምን ያህል
ትሰፋለች?
-በልጅነታችን ማሪያም ሳመችን የምንላት ዛሬስ አለች?
-ጡቶች ማደግ በጀመሩበት ወራት(ማጎጥጎጥ ነው
የሚባለው አይደል?)…በዚያን ጊዜ ማፈር ነበር…አንዴ
ማደጋቼው ከታወቀ በኋላስ…ሁሉም እንደሚያደርገው ለእይታ
31
| ናትናኤል ዳኛው
አሳምሮ ከመውጣት የዘለለ …አስተውለው… ለነሱ ምን
ስሜት እንደሚሰጧቼው የተረዱ አሉ?..... እያለች
ጡቶቿ ፈርጣማ እና ትልቅ ናቼው። ዳበስ ማድረግ
ስትጀምር አፍታ ህመም ይሰማታል። ሁለቱን ጫፎች
በረዣዥም ጣቶቿ ቁንጥጥ ታደርጋቼውና ፍንድቅድቅ
ትላለች።..ከብልቷና ከቂጧ መጋጠሚያ ሸምቀቅ ያደርጋታል።
የወገቧን ስፋት በሁለቱም እጆቿ ለክታ የወፈሩ ስለመሰላት
ነው ተነስታ ወደ መስታውቱ የመጣችው።
ዐይኖቿን ማየት ያስፈራት ነበር…በልጅነቷ። የወጣትነት
ጉልበት ግን ጥቂት ቢሆን አስችሏት… ፀጉሯን ማስተካከል
የምትችልበትን ያህል መቆም ቻለች።
መስታውት ፊት ስትቆም…የሚያፈጡባት…ግራና ቀኝ
ሆነው የሚንገዋለሉ ሞላላ ነገሮች የእሷ ዐይኖች መሆናቼውን
መልመድ አልቻለችም ነበር።
ስለዐይኖቿ ውብነት የነገራት ሰው አታውቅም።
…የወላጆቿ ቤት ውስጥም የምታስታውሰው መስታውት
የለም።…አባቷ “ደም ግባት ከንቱ ነው።” እያሉ ነው ያሳደጓት ።
ስነምግባር የሰው ፊት ቀና ብሎ አለማየት ሲመስላት ነው
የኖረችው። የት.ቤት እኩዮቿ ጋር እየሳቀች ጮክ ባላ
ያወራችበትን ጊዜ አታስታውስም።…የሴት ጓደኞቿ ከወንድ
እኩዮቻቼውም በነፃነት መነጋገር መቻል የአሳዳጊዎቻቼው
ስህተት ሲመስላት ነበር።
32
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ዩኒቨርስቲ ገብታ እሷና ጥቂት እኩዮቿ ባይተዋር ሆኑ።
…የእስካሁን ህይወቷን የኖሩላት ወላጆቿ …ኮሌጅ ምን
እንደሆነ እና እንዴት እነደሚኖርበት አልነገሯትም። በራስ…
እንደራስ ፈቃድ መኖር ምን እንደሆነ አታውቅም። የሷን
አለባበስ የሚደግም ሰው አጣች።…ብቸኝነት መነጠል ይሰማት
ጀምር። እንደ’ሷ ኑሯቼውን ወላጆቻቼው ያልኖሩላቼው…
ፈቃዳቼውን ኖረው ያወቁት… የዶርም ተጋሪዎቿ… በኑሯቼው
ተውጠው የረሷት መሰላት። ሰሜቷን..ፍላጎቷን መነገር እንጅ
መናገር አታውቅም። ድባቴው… ራስ ህመሙ ደጋገማት… እና
መሸሻ ፈለገች። መደበበቂያ ስታስስ ትምህርቷን አገኜች።
…የዛኔ ነው ከእንቅልፍ እና ከስራ ጊዜ አለማስ ተረፍን
የለመደችው። ዕድሜና የአእምሮዋ ንቃት እየፈቀደላት
ጥቂትም ቢሆን ወደ ዘመኗ መጠጋት ጀምራ ነበር።
ዩኒቨርስቲ ከተመረቀች በኋላ ለሁለተኛ ዲግሪ
ከለመደችው በረዥሙ ወደሚያርቃት ሃገር ተሻገረች።..ይሄ
ደግሞ በተለየ የማህበረሰብ አውድ ውስጥ የመኖር ሌላ ጣጣ
ነው።…ልጅነቷን የኖሩላት አባቷ ‘ውጪ ሃገር” ከማለት የዘለለ
የመጣችበትን ሃገር ስም እንኳ በውል አያውቁትም…ካርታ ላይ
አይለዩትም።
ጊዜ ጌታ፦ ሃገሯ እያለች መስራት እና መማር ተፈራርቀው
የሚመጡ ጉዳዮች ነበሩ…እዚህ ደግሞ ዘውድና ጎፍር ሆነው
ገጠሟት።…ከእንግዳው ባህል እና የአኗኗ ዘይቤ ለመራቅ ጥሩ
አጋጣሚ ሆነላት።
33
| ናትናኤል ዳኛው
አባቷን… ያደገችበትን ማህበረሰብ…እነዛን የዶርም
ተጋሪዎቿን
መውቀስ
አትችልም።…ማምለጫ
እንጂ
መፋለሚያ የማርያም መንገድ ስትፈልግ አልኖረች።
ዩኒቨርሲቲ እያለች ‘MIND BLACK MAIL’ የሚባል የስነ
ልቦና ሽቀባ አንብባ ነበር።…አእመሮዋ ወደ አስተዳደጓ መልሷት
አባቷን “ዋቴ ሰርተውሻል” ሊላት ቢፈልግም አማትባ ገሰፅኩህ
አለችው።
~
* ~
ራሷን ያየችበት.… ዙሪያዋን የተረዳችበት... አብራቼው
የምትኖረውን ያወቀችበት ጊዜ… የዕድሜ ሰሌዳዋ ውስጥ
የለም።
የመስታውቱ ፊት ቆማ ራቁት ራሷን ስታየው ስትፈራቼው
ያደገቻቼው ዐይኖቿ እንባ አቅርረው ደበዘዘባት። በዐይኖቿ
ቆብ ጨምቃ ስታወርደው መልሳ ከገላዋ ጋር ተፋጠጠች።
ፈርጣማ ክንድ ያልዳበሳቼው ክንዶቿ እንደቆቆሩ
ናቼው…ለአፋታ አፍጣ በእጆቿ ዳበሰቻቼው…በአፏ የቀኝ
ጡቷን ጫፍ ነከስ አድርጋ በተሰማቻት አፍታ ህመም ፈገግ
አለች።
ቁመቷ አማሃይ መሆኑን ያወቀችው ዛሬ ይመስል…
ረዘምኩ ለማለት... በእገሮቿ ጣቶች ቆማ ተንጠራራችና ዞራ
34
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ኋላዋን ለማየት ሞከረች።…ቂጧ ተሽሞጥሙጦ የወጣ
ነው…በቀኝ እጇ ዳበስ አድርጋው ተደላድላ ቆመች።
ዳሌዋ ሰፊ ነው…በመንገድ የምታያቼውን የተጋለጡ
እፍኝ ገላዎች…ተጠቅሎ ከዕይታ ከተሰወረው ዳሌዋ ጋር
አስተያይታ ስቃለች።
ዐይኖቿን አይታ “eyes are a window to soul…እና
በ’ነዚህ ፊደል ጠገብ ምስኪን ዐይኖች አሻግሬ ሳይታ የ’ኔዋ
ጎስቋላ ናት። ” አንሾካሾከች ለራሷ…
~
* ~
ቦርሳዋን በርብራ ብእርና ወረቀት አውጥታ መፃፍ
ጀመረች
ህይወት አንድ አይደለችምን?…የሙከራ የምትባልስ
አለች?...ታዲያ ሙከራ እና መከራችን ለምን በዛ?…ሚላን
ኩንዴራ የሚሉት ፍራንኮ ቼክ ይች የምንኖራት ህይወት ራሷ
የሙከራ ናት ይላል..የት ካልክ…The unbearable lightness
of being’ን ግለጥ ….ይሄ ይኄ ነው ህይዎት መጨረሻዋ
‘absurdity’
ነው የሚያስብለኝ…ማን
አለብኝ…ተይ
የሚል…ድክድክ ባይ ካሞዩ ነኝ ብልስ!?
በደስታ የተጀመረው ሁሉ መጨረሻው ‘Disappointment’ ነው። ያም! ይሄም! እኔ ለዚህ! እኔ ለዚያ! ነው
የተፈጠርኩት ይል ይሆናል። የሰው ልጅ መንገድ ጫፍ ላይ
35
| ናትናኤል ዳኛው
ያለው ግን ‘You the Fool’ የሚል ታፔላ ብቻ ነው።
…አስተዳደጌ የፈለገውን ሊሆን ይችላል።…ምናልባት በዚህ
መልኩ ባልኖር…በሌላ ገጽ ባድግ…ራሴን በሌላ ግራ መጋባት
ውስጥ አገኜዋለሁ።…አሁንም የዚህ አስተዳደጌ እና አኗኗሬ
ጫፍ ላይ ደርሼ ስመረምር ያገኜሁት ‘ግራ መጋባትን’ ነው።
~
* ~
ከራሴ ጋር አስተዋወቀኝ...ገላየን አጣጣምሁት ያለችበት
ቀን ሊገባደድ ነው። አዲስ ህይወት ልትጀምር... ሌላ የአኗኗር
ዘዬን ለመሞከር ምናልባትም ተመልሳ ወዳሳደጋት ማህበረሰብ
ስትሄድ “ውጪ መኖር የሃገሯን ወግ አስረሳት” እንዲላት
የሚያደርግ...…”በልጄ
ብቻ
መንግስተ
ሰማያትን
እወርሳለሁ…የሚገባውን መንገድ አሳይቻታለሁና!” የሚሉ
አባቷን
ወደ
አእምሯቼው
ሲኦል
እንዲመለከቱ
የሚያደርጋቼውን አኗኗር ልትሞክር እስከሚጠብቃት ሌላ ግራ
መጋባት ድረስ ልትከተለው.… ከዕኩለ ቀን በኋላ ዐይኖቿን
በመነጽር ከልላ የገዛቻቼውን እየለካች…የክት የነበረ አካሏን
የአዘቦት
የሚያደርጉላትን
እየለበሰች
ውበቷን
እያደነቀች...ለራሷ ታወራለች
“ገላዬ ዳባሽ ያስፈልገዋል። ጡቶቼ ድንጋይ ሆነው
እንዲቀሩ
አልፈርድባቼውም፤
ፈረካክሶ
ሃውልቱን
የሚያቆምባቼ እፈልጋለሁ!።… የጥርሴ ብርሃን ለዓለም
እንዲታይ…የዐይኖቼን አንጸባራቂነት...የፀጉሬን ዞማነት…
36
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ከቆዳየ የሚፈልቀውን ሃምራዊ የወለላ እዥ…ለነፍሴ
የሚያስታውሳት...ፍቅረ አዋቂነቴን ደጋግሞ ሹክ የሚለኝ
እፈለጋለሁ” ትላለች ጮክ ብላ።
የቤቷን በር ከፍታ ስትወጣ የማታስታውሰው የከተማው
የምሽት ውበት ታያት። ቀዝቃዛው ነፋስ ቆዳዋን ዳብሷት
ሲያልፍ ዐይኖቿን ጨፍና በሃይል ተንፍሳ…ለመብረር
እንደተዛጋጄች ሲላ ዘረጋች።…ከሩቅ ወደታያት የከተማ ብርሃን
አመራች።
~
* ~
37
| ናትናኤል ዳኛው
ቤል ኤልዛ-ቤል
ከተወለደ አስራ ስምንተኛውን የገና በዓል እየተከበረ ነው።
ከፊቱ ያለው ክብ ጠረጴዛ ላይ ክብ ቶርታ አለ…ቶርታው ላይ
አስራ ስምንት ሻማዎች ክብ ሰርተው ይንቀለቀላሉ።
እሱ፤እናቱ እና አንዲት ጠይም የቆዳ ቀለም ያላት ሴት
ሻማዎቹን ለማጥፋት ይሰናዳሉ። አባቱ ግን የለም?። “ቢያንስ
በዚህ ቀን እንዴት ከጎኔ መሆን አልቻለም?” ይላል ለራሱ
ትዝ ይለዋል። ጭል ጭል በምትል ትውስታው…
ከተንጋለለበት አልጋው ላይ ሆኖ ከሚስቱ ጋር የሚነታረክ…
ግዙፍ አካል ያለው ወርቃማ ሉጫ ፀጉሩ የሚስቱን ያህል
የረዘመ…ሰፊ ትክሻው ላይ ጥቁር ጊንጥ የተነቀሰ ሰው...
ወዲያው እየተቻኮለ ትንሽዬ ሻንጣ ይዞ ሲወጣ... ሚስቱ ከልጇ
ጎን ተቀምጣ እያነባች ነበር።ደግሞ ማልቀሷ እንዳይታወቅባት
ወደ ውስጧ ስትስገው።
ያች ሴት እናቱ ኤልዛቤል መሆኗን ያወቀው አድጎ ነው። ያ
ፊቱን በውል የማያውቀው ንቅሳታም ደግሞ አባቱ።
የዕናቱን ብዙ መመሰቃቀሎች እያዬ ነው ያደገው…ያ
ደግሞ ጭምት እና ድብርታም አድርጎታል። በውትርትር
እግሮቹ እየተፍገመገመ እጆቹን ይዛ በላቮቷ እንጀራዋን
38
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የምትጋግርበት ቦታ ስትወስደው ያውቃል። የክንዶቿን
ፈርጣማነት…የፊቷን ማድያት…የባቷን ጥንካሬ... ወንዳ ወንድ
የሚያስብላት አካል ምክንያት በዐይኖቿ አይቷል። …በላቯ
የተቦካ እንጀራ በልቶ ነው ያደገው።…ላቯ ከልክ በላይ ጨዋማ
ነበር። …”የእማዬ ላቭ ደም ደም ይላል” ይላል ለ’ራሱ
~
* ~
‘የአባቴ ስም ማነው?””
ማለዳ የጎረቤቶቻቼው ማንኮራፋት ባየለበት... በረዷማ
ጠዋት ተነስታ…መጣጣ ፊቷን ውሃ ሳይነካው…አቅሟን ሟጦ
ስጋ አልቦ ወዳደረጋት ስራ ስትሄድ አይቷል።…ማታ
ስትመለስ…ድክማና ምሬቷን መታገስ ያቅተዋል።
.
.
.
ይህ ሁሉ ስለ’ሱ የተደረገ እንደሆነ ያውቃል።...ከቡርዥዋ
ልጆች ጋር ይማራል…አቀማጥላ የምታኖረው ድባቴ ነው።
ቡርዥዋ ቅምጥሎች ባንድ ነገር ይበልጡታል።…ወላጆቻቼው
ት.ቤት ድረስ ይመጣሉ አንዱ የሌላውን ቤተሰቦች ከነ መኪና
ቀለሞቻቼው ለይቶ ያውቃል። እነዚህ ማቲዎች የ’ሱን ወላጆች፤
የወላጆቹን መኪና ቀለም ለይተው አያውቁም።...ከነ ስሙ
እንኳ ቤል ድባቴ ነው የሚሉት።
.
.
.
39
| ናትናኤል ዳኛው
ኤልዛቤል ጋር የሚያወሩት የት.ቤት ክፍያውን
በምትሰጠው ቅፅበት ብቻ ነው። የዛኔ ትለዋለች “ቤልዬ ለ’ኔ
አታስብ!”። ምንም ነው የሚላት። አይኖቹ እንባ ያቀርራሉ። በየ
ቀኑ ስትወጣና ስትገባ የሚያያትን ሴት “ እማ ናፍቀሽኛል።
እንደ ሞሳነቴ አንገትሽ መተኛትን እናፍቃለሁ” ሊላት
ይፈልጋል።
ለጓደኞቹ “እነኋት ከእናንተ እኩል የምታደርገኝ…
ለይታችሁ የምታውቁት አይደለም የመኪና…የፊት ቀለም
እንኳ የላትም!” ልላቼው ‘ፍልጋለሁ ይላል ለራሱ
ፊቱ ስትቆም እንባው ይቀድመዋል። እንባውን ለመደበቅ
ፊቱን አዙሮ ብሩን አንስቶ ይወጣል።
.
.
.
የቀድሞ ስራዋን መቀየሯን ያውቃል። አሁን ምን
እንደምትሰራ ግን አያውቅም። “ይህ ሁሉ ገንዘብ ምን ሰርታ
ታመጣዋለች?” ይላል…ጠይቆ ሊያስቅቃት አይፈልግምና
ይተወዋል።
እኒህና እኒያ ተደማምረው ድብርትን ወለዱ።
~
* ~
40
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ስለአባቱ ማሰብ ረስቷል። አእምሮው ደምና ስጋዋን እንደ
ስሟ ቆርሳ በሰጠችው…ቢቆዳዋ ላቮት የኑሮ አዳፋውን
በሚለቃለቅባት ኤልዛ-ቤል ብቻ ተሞልቷል።
ስሙን ቤል ስትለው ለራሷ ቃል እየፈፀመች ነበር። እኔ
እስካለሁ…ስሜ እስካለ ከራሴ አለይህም ስትል።
.
.
.
በረዷማው ጎዳና ላይ እግሮቹን በእጆቹ አቅፎ
ተቀምጧል።…ብርዱ ሰውነቱን ያንቀጠቅጠዋል… እሱ
በድብርቱ ጠፍቷል። አእምሮው ብርዱን ረስቶታል። ይች ቀይ
ቀሚስ…ቀይ ቀሚስ…ቀይ ኮት...ቀይ ካፖርትና ቀይ የእጂ ጓንት
የለበሰች ባለ ቀይ ሊፕስቲክና ቀይ ፀጉር ከቆዳዋ በቀር
ሁለመናዋ ቀይ የሆነች ሞጃ መኪናዋን ከጎኑ ስታቆም
አላስተዋላትም።
ከመኪናዋ ወርዳ ከ ጎኑ ስትቆም…በጣም ተቻኩላ ነበር።
....ጤነኛ ወጣት በዚህ ሰዓት ቤቱ ከእሳት መሞቂያ ጎን የጥጥ
ካፖርቱን ለብሶ ሲጋራውን ለኩሶ ቢራውን እየተጎነጨ በብርድ
የምትዝናና ፍቅሩን ከጎኑ ሽጦ “Love in the time of
cholera”*ን እያነበበ ምናልባትም “Love in the time of
icecold”ን ለመጻፍ እያሰላሰለ ሊሆን እንደሚችል ነው
የምታውቀው።
41
| ናትናኤል ዳኛው
ይሄ ባለ ወርቃማ ፀጉር ቀጫጫ ወጣኒ በዚህ
ሁኔታ…በዚህ ብርዳም በረዶ ለያውም ከቪላዋ ጥቂት
እርምጃዎች ቀርቦ መምን ይሰራል? ዕዴትስ freeze
ሳያደርግ?…ልጁ ሳይኮቲክ መሆን መሆን አለባት!?… እንዲህ
እያሰበች ለአፍታ ስታስታውለው ቆየች። ሊያዋራት
እንደማይችል ገብቷታል።…ባለበት ጥላው ለመሄድ እግሯ
አልዞረላትም። ካፖርቷን አልብሳ ደግፋ ወደ መኪናዋ
ልትወስደው አስባ...ልታነቃው ሰውነቱን ፀጉሩንና ሰውነቱን
መዳበስ ጀመረች። ...ሲነቃ ብዙ አላለፋትም።
በሰው እጅ እንዲህ ከተዳበሰ ብዙ ጊዜው ነበር....ቀና ብሎ
አይቷት ሴት መሆኗን ሲያውቅ… ለዐይኗ ከጭጋጋማው ቀን
ተለይታ ስትታየው ዐይኖቹ የለመዱትን እንባ አቀረሩ። እጁን
ይዛ ስትስበው … የእጆቿ ልስላሴ...ለቡን ሲያሞቃት ታወቀው
እና ከንፈሩ ላይ ፈገግታ ለመሳል እየሞከረ ቀና ብሎ አያት።
አእምሮው ለጥያቄ ፋታ ሳያገኝ ተከትሏት መኪና ውስጥ ገባ።
አእምሮዋ እየፈበረከ ከሚወረውራቼው ጥያቄዎች
እየተሽሎከሎከች የቪላ ቤቷ በር ላይ ደርሰው አቅፋ
አስገባችው። የእሳት ማሞቂያዋን አብርታ...ወንበር ላይ
አስቀመጣው…እዛው ሳሎን “ምን ላድርግ” እያለች
ስትንጎራደድ ቆየች።
ይች ቅፅበት ብዙ አስረስተዋለች።...ራሱን… ድብርቱን…
የድብርቱን ሰበቦች... እናቱን... ቤቱን... ት/ቤቱን... የት/ቤቱን
42
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ማቲዎች.…የማቲዎቹን ወላጆች.… የወላጆቻቼውን መኪኖች...
የመኪኖቻቼውን ቀለሞች።
~
* ~
ማናት ይ’ች ሴት?...ብሎ አልጠየቀም። የት?…ምን
ስሆን?…ለምን?…አላለም።
ዳብሶ
ያነቃው
የእጅ
ራቢንግ*.....ጎትቶ ያስነሳው ክንድ ሙቀት.…ከጭጋጉ ጎልቶ
የታየው ቀለም ወስደውታል። አተኩሮ እያያት ብቻ
ተቀምጧል።
.
.
.
አውቃለች…እሳቱ በጥልቀት ገብቶ የሚያንቀጠ ቅጠውን
ብርድ ሊያጠፋለት እንዳልቻለ። ምን ላድርግ?… እያለች ነበር።
ስትዳብሰው እጆቿን እንዴት በፍቅር እንዳያቼው
አስተውላለች። ዐይኖቹ ላይ ያየችው እንባ ያቀረረ ፍቅር ነው።
ደግማ መዳበስና ደግማ እነዛን ፍቅራም እንባዎች ማየት
ፈለገች።
ተጠግታው ከተቀመጠበት ጀርባ ሆና በግራ እጇ ወርቃማ
ፀጉሩን እያሻሼች …በቀኝ እጇ ቀኝ ክንዱን መዳበስ ጀመረች።
ቁልቁል ስታየው ዐይኖቹ ተከድነው እንባ ያንጃርራሉ። ልቧን
ሲበርደው መልሶ ደግሞ ሲሞቀው ይታወቃታል።…ማቀፍ
አሰኛት።
43
| ናትናኤል ዳኛው
በዐይነ ‘ርግብ የምትሼፍነው ፊቷ…በስልጡን አልባሳት
የምትጠቀልለው ገላዋ...ቀለም የሸፈነው ከንፈሯ.…ዕረፍት
አልባ ጠይም ሰውነቷ...ሰው እንደናፈቀው ገብቷታል።
...ባይተዋር ነበረች…እንደሷው ከጠይሟ ሃገር የኮበለለ ጠይም
ቆዳ የምታየ አልፎ አልፎ በምትታደምባቼው የሙዚቃ
ኮንሰርቶች ነው…ሌላውም እንደሷው ለህይወት የተረፈ ጊዜ
የለውምና።…አንዳንድ ጊዜ ብቻዋን ስትሆንና መታከት
ሲሰማት...“ምነው ለመኖር እየሰራን ሳንኖር ማለፋችን?”
ትላለች።
~
* ~
ይሄ ጉስቁል መጥኔ ከምግብ ይልቅ ዳበሳ
የሚያጠግበው… ንክኪ የራበው ዓይነት መሆኑን
ጠርጥራለች። ወደፊቱ ዙራ አስነስታው...በቅርብ ወዳየቻት ሶፋ
ወሰደችው…ከደረቷ ለግታ…ጡቶቿን አስደግፋው።…እንቅልፍ
እስኪያሼልበው ድረስ ዐይኖቹን መክፈት ፈርቶ ነበር።
~
* ~
ማለዳ ሲነሳ ራሱን ያገኜው ሶፋዋ ላይ ብቻውን ተጠቅሎ
ተኝቶ ነው። ደረቷን አንተርሳው…አፍንጫው የጡቶቻን ከርቤ
ሲያሼትና ከንፈሮቹ የቱቶቿ መጋጠሚያ መሃል አርፈው
ካሼለበ በኋላ ጠዋት እስኪነሳ ድረስ የሆነውን አያስታውስም።
44
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
እዚህ ሶፋ ላይ ያሳለፋት ሌሊት ከማያውቃቼው ብዙ
ሌሊቶች አንዷ ናት።…የዕድሜው ብዙ ሌሊቶች ሰቀቀናሞች
ናቼው…እነሱን አይረሳም።
ከሶፋዋ ትራስ ስር ቁራጭ ወረቀት አግኝቶ ሲያነባት ከሷ
የተተወች መልዕክት ናት።
Hey…morning! Hope that you got
enough sleep…Gud 4 health yuh!?
See you for lunch at elmuda hotel
…I will arrive there at 12 a.m. come till
13 a.m. okay!! Bye *
ከተኛበት ሶፋ ተነስቶ የመስታወት ግድግዳውን
መጋረጃ(curtain) ገልጦ ቆመ።…የፀሓዩአ ጨረር(ምዕዛር)
መስታዎቱን አለፎ ሰውነቱ ላይ አረፈ።
የውጪው በረዶ ቀልጦ እንደ ወንዝ እየተንኳለለ ሲፈስ
ይታየዋል።…ፈገግ ብሎ ፊቱላይ ያረፉትን የፀሃይ ዛላዎች ዳበሳ
ዐይኑን ጨፍኖ ለማዳመጥ ሞከረ።
45
| ናትናኤል ዳኛው
ለአፍታ አሻግሮ እያየ ከቆየ በኋላ ተንጠራርቶ ወደ ሶፋዋ
ሲመለስ ወረቀቷ ወለል ላይ ወድቃ አይት…እዛው ባለችበት
መልዕክቷን ደግሞ አንብቦ…በሃይል ሳቀ።...ምሳ የምትጋብዘው
እነዛ ሞጃ የት/ቤት ማቲዎች ወላጆቻቼው ጋር የሚቃበጡት
ነው።
~
* ~
በሰዓቱ የተባለው ሆቴል ደርሶ በሩ ላይ ቆመ።ከህንፃው
አናት ላይ የተጻፈውን ስም አንጋጦ ያያል …መልሶ ደግሞ
አንገቱን አስግጎ …ዐይኖቹን ወደ ውስጥ ሰዶ ወንበሮቹን
ያስሣል። ከመግቢያ ቤሩ ፊት ለፊት ያለ…የሚታይ ኮርነር ላይ
የዳበሱት እጆች የተገለጠ መፅሃፍ ይዘው አየ።…የመፅሃፉ
ውጨ ገጽ ለማየት ሞክሮ በማይለያቼው ፊደላት የተጻፈ
መሆኑ ሲያውቅ ምን እንደምታነብ የማወቅ ጉጉቱ ቀዘቀዘ።
ቀድሞ መጥቶ የእሱን መምጣት የሚጠባበቅ ሰው
በማግኜቱ ደስ ብሎታል።…ትንሽ መዘግየት…ትንሽ መጠበቅ
ፈልጎ… ልጋብ አልግባ እያለ እያመነታ ሳላ…እጆቿ
እየተውለበለቡ ሲጠሩት አይቶ ደነገጠና ወደ ዛው መራመድ
ጀመረ።
መጽሃፏን እያጠፈች ከጊኗ እንዲቀመጥ ጋብዛ ጠረፔዛ ላይ
የነበረውን ሜኑ አንስታ ማየት ጀመረች።…አጥፋ ያስቀመ
ጠችውን መጽሃፍ አንስቶ በደመ ነፍስ መገላለጥ ሲጀምር
46
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ውስጡም በማይለያቼው ፊደሎች የተጠቀጠቀ ሆነበት።
ወዲያ “ መን ይባላል?” አላት
“ምኑ?” አለችው ሜኑውን ወደ’ሱ እየገፋች
“መጽሃፉ?”
“እ…መረቅ!” አለችው መጽሃፉን ገልብጣ የደራሲውን ፎቶ
በጣቷ እየዳበሰች
“መረክ!?” ብሎ ደገመላት …በስሱ ፈገግ አለችለት
~
* ~
አድርጓቼው ከማያውቃቼው ነገሮች አንዱ ነው...ሜኑ
(መዘርዝረ ምግብ) አገላብጦ የሚወደውን ማዘዝ።
በዕድሜም… በቆዳ ቀለምም… ክሱ በብዙ የምትርቅ… ቶሎ
የሰዎች ዐይን ውስጥ የምትገባ ሴት ጋር እንዲህ ዓይነት ሆቴል
ገብቶ መመገብ የእስካሁን የህይወት ገድሉ ውስጥ የለም።
ከጎኗ ተቀምጦ ሰወች እየዞሩ የሚያዩትን ዐይኖች
መቋቋም አቃተው።…ተነስቶ ፊት ለፊቷ ተቀመጠ። ዐይኖቹ
ውስጥ እየገባች ስታዋራው አንገቱን ይሰብራል… እሷ ደግሞ
ከዙሪያዋ የሚወረወሩትን እንኳ አምና የተቀበለች መሰለችው።
…ስትረበሽ ባለማየቱ።
47
| ናትናኤል ዳኛው
ያዘዘው ምግብ ፊቱ ቢቀርብም ብዙውን ያጎረሰችው እሷ
ናት። …ዙሪያቸውን የከበቡት ከራሳቼው ክብ ሰሃን ያረፈን
ምግብ ወደራሳቼው እንጂ ወደሌሎች መሰንዘርን አያውቁም።
...ይሄ ፊቷ የተቀመጠውም የዚህ ባህል አካል ነውና ስታጎርሰው
በመደነቅ ያያታል።...ከጉርሻዋ ጋር ጥቅል ፍቅር ወደልቡ
ስትሰድ ታወቀው።
ከምሳ በኋላ ቡና እየጠጡ ስለራሷ በስሱ ነግራው ስለ’ሱ
እንዲያዋራት አነቃቃችው። ቡና ቀምሶ የሚያውቅ አልመስላት
አለ...ፉት ባለ ቁጥር ፊቱን ያኮማትራል…። ቡናው ላይ ደጋግሞ
ስኳር እየዶለ ለመጨረስ ይታገላል።
እያወራላት...ከስሜቷ ጋር እየታገለች…ትሰማዋለች።
ስሚቷ…የቆላ ቀለሟን የሚመስሉ ብርቱ መሆኑን
ላሳየችው…ፍዝ ወጣት…አሁን…ደካማ ሆና ላለመታየት…
ከእንባዋ ጋር ትታገላለች። ሲጨርስ
“ከእናትህ ጋር
እፈልጋለሁ።” አለች
አስተዋውቀኝ።
ቤታችሁ
መሄድ
“እ…እናቴ ከስራ የምትመለሰው ማታ ነው” አላት
.
.
.
ከኤልዛቤል ጋር ስላላሳለፏት ሌሊት እያሰበ ዝም ብለው
ቆዩ። ሆቴሉ ውስጥ ለስላሳ ሳቆች ይሰማሉ። ራቅ ብሎ
ባርቴንደሩ በጥቂት ብሎንድ ሴቶች ተከቦ ትሪዒት መሳይ
48
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ያሳያል።…ሴቶቹ ደጋግመው መዳፎቻቼውን
እያነካኩ
የማጨብጨብ ምልክት እያሳዩ…አየሩን በቀይ ከንፈሮቻቼው
ይስማሉ። ከባልኮኒው የግራ ጠርዝ የተቀመጠ አንድ የራስ
ፀጉሩ የሳሳ ሽማግሌ ጉልበቱ ላይ የተቀመጠች ወጣት እንስት
ጋር ድሪያ ይዟል…ወጣቷ የለበሳትን ቲሽርት እጂጌ እየገለጠች
መደብዘዝ የጀመረች ንቃሱትን ታያለች።…ደጋግማ “ጊንጥ ነች
አይደል!?… ጊንጥ እፈራለሁ…ግን ደስ የሚል አውሬነት አላት…
አይደል?” እያለች ትቅበጠበጣለች። ሽማግሌው ደጋግሞ
ጉንጮቿን ለመንከስ እየሞከር “ልክ እንደዚህ አውሬ” ሊላት
ይሞክራል።
ይችን ሌሊት ይወዳታል።...ከሌሎች ቢያንስ የእናቱን
ዐይኖች ካየባቼው ጋር ግን ማነጻጸር ግን አልፈለገም።
~
* ~
ማታ ቤት ባታገኜው ኤልዛቤል ምን እንደምትሆን
አያውቅም።…በተለያየ ጣራ ያሳለፏት ሌሊት ከዚህ በፊት
የለችም። ቤጡ ውስጥ ካያት መቆየቱን እየታወሰው ዐይኖቹ
እንባ ማቅረር ጀመሩ።…እያሰበ “ማታ እቅፍ አበባ ይዤ
እቀበላታለሁ… ደሞ… ደሞ እቅፍ አድርጌ ‘ስማታለሁ።” አለ
“እ?” ስትለው ከሃሳቡ ነቃ።
~
* ~
49
| ናትናኤል ዳኛው
ከሆቴሉ ወጥተው በዝግታ እየተራመዱ በየመንገዱ ላይ
አልፎ አልፎ የተቋቱ በረዶዎችን እየረገጡ ወደ ሆቴሉ
ከሚያመጣው መንገድ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ታጠፉ። አዲስ ቀለም
የተቀባች አሮጌ መኪና በጊናቼው ስታልፍ ከጎማዋ የተፈናጠሩ
በረዶዎች እግሮቻቼው ስር አረፉ። ወደ ጎን ዙሮ መኪናዋን
ሲያይ የተሸከመችውን ግዙፍ የገና ተመልከተ።…በልቡ”
ከሁለት ቀን በኋላ ገና ነው። ኤልዛቤል ደግሞ ከጊንጥ ፀንሳ
ከክርስቶስ ጋር ወልዳኛለች።” አለ::
50
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
መጠበቅ ስንት ብር ያወጣል?
ጥቁር ካፖርትና ናይለን ሱሪ የለበሰ ወጣት ገብቶ ፊት
ለፊቷ ተቀመጠ። ከዚህ በፊት እንደምታውቃቼው ሃብታም ነን
ለማለት ወይንም ለመምሰል ተሽቀርቅረው በየመጠጥ ቤቱ
ሴት ከሚያሽኮረምሙት ለይታ አላየችውም። ሌሎች
ሲያደርጉት እንደነበረው ...እሱም ዐይኖቿን ከስልኳ ላይ
አንስታ ወደ’ሱ እንደትሳብ የታሰሩ እና ሲነኩ የሚጮሁ የብር
ኖቶች እስኪያወጣ እየጠበቀች ነበር።
እዚህ የተገኘችው የማታውቀውን ገላ ፍለጋ እንደሆነ
ታውቃለች። …ዛሬ ራቁት ገላዋን የሚዳብስ ትናንት
የተዋሰበችው ገላ እንደማይሆን ታውቃለች።
የብር ኖት ቋቋታወችን እየጠበቀች ነበር። እነዛኞቹ ከዚህ
በፊት የምታውቃቼው በኖት ቋቋታ ጠርትው በአልጋ ኡኡታ
የሚሸኟት …ከፊታቸው ሲያገኟት ዐይተው የሚያልፏት ዐይነት
ስለማትሆንባቼው ሞጃ ነኝ ለማለት ይጣደፉ ነበር። …የገላዋ
ጠረን ሩቅ ለሚሆን አይሸትም።…እሷን በዐይኖቹ ጠርቶ
ማባበል የቻለ ባለ ገድል የለም። የሚጠሯትን ዐይኖች
አታያቼውም።... ቀድመው የሚረቱት ጀሮዎቿ ናቸው።…ምሷ
ሽታ ነው…የወረቀት። ጆሮዎቿ የኖት ጩኸትን ያሳድዳሉ።
51
| ናትናኤል ዳኛው
ከ’ሷ ቅርብ ካለች ወንበር ላይ መጥቶ ሲቀመጥ ውልብ
ሲል ባየችው ጥላ ዛለው ያማረ መሆኑ ገብቷታል። የቤቷ
ብርሃን ገጽን ሊደብቅ የሚችል አይደለም…ሁሉም በግልጽ
ይተያያሉ። የተቀመጠችው ግድግዳውን ተጠግታ ፊታቼውን
ወደ ግድግዳው ያዞሩ ሁሉ እንዲያዩአት ሆና ነው። የማር
መለልታ ቀለም ያለው ጭኗ ካደረገቻት ቁምጣ አምልጦ
ተጋልጧል።…ሆድ የላትም…አኗኗሯ በ ‘SUN GAZING’ ነውን
የሚያስብል አይነት። በዳሌዋ ስፋት የተስተጓጎለ ወጥ ቁመናዋ
ሆዷ ላይ በወገቧ ጥበት ተደግሟል። እግዜር ወገብ እና ዳሌዋ
ላይ የውሃ ልክ በሰፊው ስቷል..ከትክሻዋ ልክ ሆኖ መጥቶ ወገቧ
ላይ ሰጥሞ ዳሌዋ ይንዘረጠጥና ተመልሶ በትከሻዋ ልክ
ይወርዳል።.......ይሄን ማየት ለማንም የተፈቀደ ነው።
ከዚህ ገላ ጋር መዋሰብ…የዐይኗን ሸውራራነት
ማስተዋል.…ከሰካችው አርቴ ማዶ የታፈነ ኪንኪ ፀጉሯን
ማወቅ የሚችለው ግን ቅርቧ ሆኖ በትኩስ ኖቶቹ የተጣራው
ነው።
.
.
.
ባለካፖርቱ እና በውልብታው ዛላው ያማረ ነው ብላ
ያሰበችው ሰው የምትወዳቼው ኖቶችን ድምጽ ከማሰማት
ዘገየ።…የዚህን ያህል የጠበቀችበት ጊዜ ሩቅ ነው።
“ማንም ገላየን አይቶ መታገስ አይችልም። ብላ
ከደመደመች ቆይታለች። “የመጣሁት ለፍቅር አይደለም።
52
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
…ያለሁትም በቅንዝር እንጅ በፍቅር መስክ አይደለም።
ያገናኜን የኔ ብር ፈላጊነት እና የ’ነሱ ቅንዝራምነት ብቻ
ነው…every man is prurient::..ስለዚህ በመገበያያ እንጅ
በመግባቢያ ቋንቋችን ማንም እንዲያናግረኝ አልፈቅድም።”
ትላለች
ከጎኗ መጥቶ ይቀመጣል። ኪሱን ዳብሶ የኖት ችብታ
ያወጣል። የኖቶቹን ድምጽ ሰምታ ፈገግ ትልለትና ተነስታ
በቤቷ የኋላ በር ትወጣለች።ይከተላታል…ያወራሉ። ...ሲነጋ
ራሷን የተዛነቀ አንሶላ ስር ታገኜዋለች።
~
* ~
ለራሷ “ሰውየ ካለህ አሰማኝ አልያ ቦታ ልቀቅ?” ልበለው
ትላለች።
ከወትሮዉ
ትንሽ አንገቷን ቀና አድርጋ የእጆቹን
እንቅስቃሴ እየተከታተለች ነበር። ያስከፈተዉን ቢራ አንድ ጊዜ
በረዥሙ ስቦለት በሃይል ተነፈሰ። ወዲያዉ ቀኝ እጁን ወደ
ካፖርቱ ኪስ ሲከት በልቧ"ላያመልጠኝ አሯሯጠኝ" ብላ ፈገግ
አለች።...እጆቹ ከኪሱ ሲመለሱ የያዙት ሰፊ ጥራዝ እንደሆነ
ገብቷታል። ወዲያዉ ከንፈሮቿን ለጥጣ ፈገግ እያለች ቀና ስትል
ያየችዉ ግን ሽፋን የለበሰና ወፍራም ጥራዝ ያለዉ ፖኬት ቡክ'
ነበር። ከንፈሮቿ ተመልሰዉ ቦታቸዉን ሲይዙ ዐይኖቿ አንገቱን
ሰበር አድርጎ
የመፅሃፉን
እልባት ያደረገበት ቦታ
የሚከፍተዉን ቀይ ወጣት በግርምት ያዩታል። መፅሃፍ ከብዙ
53
| ናትናኤል ዳኛው
ብላሽ ሰዎች የተሻለ ወዳጅ ነዉ...ለእሷ...ምናልባት ለዚህ
ወጣት።
ወጣቱን አተኩራ ታየዋለች።...በስህተት እንኳ ሊያያት ቀና
ያለበት ቅፅበት የለም። ከረዥም ጊዜ በኋላ ነዉ... ዐይን
እንዲያያት ስትናፍቅ።... በልኸኝነቷ... ግዴለሽነትን ተለማምዳ
የረሳቻቼዉን እነዛ የመናፈቅ ዘመናት ወደ አእምሯዋ ሊመልስ
ታገላት። ...ከፊቷ መኖሩን እንኳ ረስ ለሰዓታት ያልነካችዉን
ቢራ አንስታ በጉሮሮዋ አንደቅድቃ አወረደችዉ።
ስልኳን ከጠረጴዛዉ ላይ አስቀምጣ አሁንም ወጣቱን
በጥልቅ ታየዋለች። አራተኛዉ አንገተ ረዥም ቢራ በእጇ 'ርቀት
አለ። ወጣቱ እያነበበ ሳይሆን እየሼሼ መሰላት "ለንባብ
ሊመረጥ የሚችል ቦታ አይደለም ያለዉ...እንዲህ ዐይነት
ጫጫታ ዉስጥ መፅሃፍ መግለጥ የደፈረ ለምን ሽፋኑን
መከለል አስፈለገዉ?" ትላለች ለራሷ።
ያ ድንቅ አሰላሳይ ነዉ የምትለዉ ደራሲ 'የታጠፉት ገፆች'
በምትለዉ ተረኩ ዉስጥ "መፅሃፍትን የሚሸፍኑ የንባብ
አሻራቸዉን መደበቅ የሚልጉ ናቸዉ።" ብሎ መፃፉን
አስታወሰች።
መልሳም "የንባብ አሻራ የሚያስስ ትዉልድ በሌለበት
ሀገር አሻራተደበቅ አልተደበቅ ለዉጥ አያመጣም።" አለች
54
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
እየሰከረች መሆኑ አልታወቃትም...በቢራ ጠርሙሶች
የተሸፈነዉን ጠረጴዛ በእጆቿ ተደግፋ በገፆች ጫካ ዉስጥ
የጠፉትን ዐይኖች ትፈልጋለች።
ቤቱ መቀዝቀዝ ጀምሯል።
አልፎ አልፎ እያንጎላጁ ከሚታዩት ሴቶችና ሴት አቅፈዉ
ለመዉጣት ሲታገሉ ከሚታዩት በቀር ሌላዉ አየር ነዉ።
ወጣቱ መፅሃፉን ዘግቶ ቀና ሲል በቅርብ ርቀት ያለችዉ
ሴት በጠርሙሶች ተከባ ታንኮራፋለች።...ራቅ ብሎ ካለዉ
ባንኮኒ ውስጥ ያለች ሴት በአግራሞት እያየችዉ "ልንዘጋ ነዉ"
አለችዉ
ከመዉጫ በሩ ጥበቃ ያሰለቻት የምትመስል ወጣት "!
አበዉ በነፃ እንሂድ" ብላ ሳቋን ለቀቀችዉ።...የእጁን ሰዓት
ሲመለከት ሊነጋ የዶሮ ጩኸት ብቻ ነዉ የቀረዉ...መፅሃፉን
ካፖርቱ ዉስጥ እየከተተ ተጣድፎ ወጣ።
55
| ናትናኤል ዳኛው
አራት ኹለት ኹለት
ቤርሲ
ትንሽ ሱቅ አለችን። መስኮቷ ከአጥራችን ሾልኮ የወጣ።
ከት/ቤት መልስ ያለ ጊዜየን የማሳልፈዉ እዛች
ነዉ...እያጠናኹ...እየሸጥኹ። ት.ቤት የማዉቃቸዉ ሶስት
ጎረምሶች ደብተራቸዉን በእጃቸዉ ጨብጠዉ...አረንጓዴ
ዩኒፎርማቸዉን ለብሰዉ፡ኮቱን እንደ ስካርፍ አንገታቸዉ ላይ
አንጠልጥለዉ ሲመጡ አየኋቸኹ።
...ሊያሳፍረኝ ይሞኮራል... ወጥጦ ሙቶ...እኔ ኮረዳዋን
ሊያሳፍረኝ። አሁን አብረዉ ከሚመጡት ሁለት ጓደኞቹ ጋር
በእረፍት ሰዓት 'ክፍላችን ፊት ለፊት መጥቶ ይቆምና...ስወጣ
ጠብቆ ሊያሳፍረኝ. ..ሊያሽኮረምመኝ ይሞክራል።. ..ማን ነዉ
ቤርሲ ጠይም ወንድ ትወዳለች ያለዉ?...ማነዉ ቤርሲ ደረቱ
ወጣ ያለ...ፍንዴx ፍንዳታ... ታታታ ያለ ትወዳለች
ያለዉ?...ፓንክ
የተቆረጠዉን
ፀጉሩን
አቁሞ
እኔ
ከምቀመጥባት ፊት ለፊት ያለችን የባህር ዛፍ ተደግፎ...ጓደኞቹ
አስሬ እየገለፈጡ፡እግሮቻቸዉን እያወናጨፉ የሚያወሩለትን
ትቶ...ወደ
እኔ
ያፈጣል...
በሚማርክ
ፈገግታዉና
በሚያጥበረብር የጥርስ ንጣቱ የሚማርከኝ መስሎት። ፈገግ
ይላል...ባላየ ዐይኔን ቀልብሼ ላሽ እላለኹ።
56
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ያ አልበቃ ብሎት ዛሬ ደግሞ ይሄዉ በሰፈሬ...ከነ
ዩኒፎርሙ...ከነዛዉ ጓደኞቹ ጋር።...እንዳያየኝ ፈልጌ ነበር ግን
ይሄ ሰካራም አዳሙ ያለወትሮዉ በዚህ በቀትር ሰዓት 'ሰፈሩ
ተገኝቶ "ማነሽ?...ቤርሲ" እያለ መጣ... ለ'ሱ ሲጋራ ስሰጥ...
ፊትለፊት ተጋጨን።
ሲደነግጥ ያስታዉቅበታል...ፓንክ የተቆረጣት ሉጫ ፀጉሩ
ብን ብላ ትቆምና የ'ንትን ፀጉር ትመስላለች... ጠይም ወንድ
ላይ ሉጫ ፀጉር ይሸክከኛ የኾነ መርካቶን ተላምዶ የቀረ የከሰረ
ህንድ ነዉ የሚመስለኝ።
ልቤ ላይ ትንሽ ድንጋጤ ተቋጥራ ብትን ስትል
ታወቆኛል...ድብብቆሽ ለመጫዎት ፈልጌ ስለነበር ይኾናል...አለ
አይደል እስከኾነ ድረስ መዉደዱ ያልገባኝ መስየ oldish 'Prey
and predator' ጨዋታ መጫወት። እንደሱ አይነት ፈርጣማ
ወንድ ሲርበተበት ማየት ያዝናናል።
ትንሽ አልፈዉ ከሄዱ በኋላ...ከእኛ ቤት በስተቀኝ
አራተኛዉ ቤት ፊት ለፊት ያለች ጠላ ቤት ሲገቡ አየኋቸዉ።
የመጣዉ ጠላ ቤት ፍለጋ ነዉ ወይ?...ይኼ ወጠጤ እኔን ፍለጋ
አልነበረም የመጣዉ?
ጠላ ቤቷ አጥር የላትም...እናም እዝች ሱቅ ተቀምጨ ብዙ
ወጣቶች ጀግነዉ ገብተዉ ተልፈስፍሰዉ ሲወጡ አያለኹ።
አቅሙ ይገርመኛል?...የጠላዉና የወንዶች አእምሮ ነገር
ይገርመኛል? ሰክረዉ በመዉደቃቸዉ ግንባራቸዉ በነጭ
57
| ናትናኤል ዳኛው
የቁስል ፕላስተር የታተመ ከነህመማቸዉ ተመልሰዉ ለሌላ
ቁስል የሚመጡበት የጠላ ነገር ያስደንቀኛል።
በግልፅ የማዉቀዉና ያየኹት ሳይንስ ይኼ ነዉ። ሀገሬ
ለትዉልዶች በግልፅ ያስተላለፈችዉ ጥበቧ የጠላና የአረቄ
መቀመምን ይመስለኛል።ከልጅነቴ ጀምሮ አይቻለኹ እናቴ
ጠላ እንዴት እንደምታዘጋጅ ግን ሳይንስ መሆኑን አላዉቅም
ነበር...7ኛ ክፍል ደርሼ Ferme- ntation* የሚባል ነገር
እስካዉቅ ድረስ።
አሁን አልኮል ሲጠጡ ለምን ሚዛን እንደሚስቱ
አዉቃለኹ cerebellum የሚባለዉን የአእምሯቸዉን ክፍል
አልኮሉ ስራ ስለሚያስፈታዉ ነዉ።
ይኼን ልቤ እየለመደዉ የመጣን ጠይም ወጠጤ ግን
እንዲህ አይነት ቦታ አየዋለኹ ብየ አላሰብኩም ነበር።
የምጠላዉን እንዲያደርግ ያለመፍቀድ የሴትነት ቅመም
ዉስጤ አትጠፋም።...የጠላ ኬሚስትሪ የሚደንቀኝን ያህል
ጠላ የሚጠጣ ሰዉ አልወድም... የእናቴን ቦይፍሬንድ ተዘራን
ነዉ የሚመስለኝ። ጠላ የሚጠጣ ሰዉ ተዘራ ነዉ...ተዘራን
ደግሞ አልወደዉም።
...የአረቄ ጠርሙስ እየሸተተ መጥቶ ካጠራቀምኳት የሱቅ
ሳንቲም ካልሰጠሽኝ ብሎ ይጣላኛል... እንደማ ልፈራዉ
ያዉቃል...እናቴ ፊትም ደፍሬ እልደማልቆምም ግን ያዉቃል።
ማታ በአልኮል ትንፋሹ እየጠመቃት...ነገር ያዋሽካላታል።
58
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ከተኛኹበት ቀስቅሳ... "ምንአገባሽ?" ትለኛለች...ላለቅስላት
አልፈልግም እልኼን ጠንቅቃ ታዉቃለች።... ከእንቅልፌ
እየተቀሰቀስኹ መነትርክ ስለሚመረኝ እሰጠዋለኹ።
ሱቋ ቀስበቀስ በአፅሟ መቅረት ጀመረች። "ምን
አድርገሻት ነዉ?... የኔ ኮረዳ... እንደ ጓደኞችሽ...እንደ ሃብታሞች
ለመኾን ስትይ የእኔን ሱቅ ባዶ አስቀረሻት!?" ትለኛለች
ልቧ ግን ያዉቃል...እንደ ጓደኛ የምል እንዳልኾንኩ... ጓደኛ
የሚያጓጓኝ እንዳልኾንኩ... እሷም ይኼ አልኮል ቦይፍሬንዷም
የሚያኖራቸዉ እዛች ሱቅ ግማሽ ቀን ቆሜ የማጠራቅማት
እንደኾነች ያዉቃሉ...ከት/ት ቤት ስመለስ ምግብ አብስላ
እንደማትጠብቀኝ ታዉቃለች...እጥኚ ለሱቋ እኔ አለኹ
እንደማትለኝ ታዉቃለች...ግን ከዉሽማዋ ጋራ እኔንም
ሱቋንም በአልኮል ካማጉን በኋላ...እኔኑን ልትወቅሰኝ
ትሞክራለች...ልፋቷ እቴ።
ሰዎች ሊነግሩኝ ከሚሞክሩት ቁንጅናዬ ይልቅ ትልቁ
መመኪያየ እልኼ ነበር...በቀላሉ የምሰበር አልነበርኹም...
እንቅፋት መትቶ ቢያደማኝ...ደሜን እንኳ ጎንበስ ብየ
አልጠርገዉም። ቀጥ ብየ ምንም እንዳልተፈጠረ መንገዴን
እጓዛለኹ...ሰዎች እነዛዉ ሰዎች እንቅፋቱን መንገዴ ላይ
ያስቀመጡት ጣቶቻቸዉን ወደ እግሬ እየቀሰሩ..."ቤርሲ ጣትሽ
እኮ እየደማ ነዉ!?" ሲሉኝ አልሰማቸዉም።
59
| ናትናኤል ዳኛው
አንድ ቀን ከት/ቤት ስመለስ እናቴን ትንሽዬን ቦርሳ
አንጠልጥላ...ነጠላ ራሷ ላይ ጣል አድርጋ...እንባዋን በነጠላዋ
ጫፍ እየጠረገች ከግቢ ስትወጣ አገኘኋት... የትም ልትኼድ
እንደምትችል ስለማዉቅ ብዙ አልደነቀኝም ነበር...ግን
አለቃቀሷ!?
"ፍቅር የት ነዉ?" አልኋት
እናቴ እንደዛ ቀን ተሰብራ አይቻት...አናግራኝም
አታዉቅም። አቀፈችኝ... እቅፏ ይሞቃል...የማዉቀዉ ድሮ
ነዉ... ፈጥኜ ማቀፍ ቢከብደኝም...እልኼን አሸንፌ አቀፍኳት።
...እንባዋ ትከሻና አንገቴ መኻል ጠብ ሲል ያቃጥለኝና በአጥንቴ
ደርዝ ተንኳሎ...በጡቶቼ መኻል ይወርዳል
"ፍቅር ግን የት ነዉ?" አልኳት ደግሜ
በነጠላዋ ጫፍ እንባዋን እያበሰች...የአፍንጫዋ ጫፍ ላይ
የተቋተዉን እየጠረገች
"ገጠር...አባትሽ አርፏል አሉኝ" አለች
ስለአባቷ እንዲወራባት እንኳ የማትፈቅድ እንዳልነበረች
አዉቃለኹ...ልጅ እያለኹ... "አባቶች ኹሉ ክፉ ናቸዉ... የአንቺ
አባት...የእኔ አባት...የእናቴ አባት...ኹሉም ክፉ ናቸዉ።" ትለኝ
ነበር...እኔም እናቴን አትላስ ናት አባቴ ደግሞ ዜዩስ በእርግማኑ
ዓለምን ያሸከማት ብያለኹ።
60
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
አባቴ ጥያቄ ኾኖብኝ አያዉቅም...በተለይ እናቴ ከተወችኝ
በኋላ።
ኹሉም እናት እና አባቶች ክፉ ናቸዉ...ስለዚህ እናትም፡
አባት አያስፈልገኝም...እኔም እናት አልኾንም... ባልም
አይኖረኝም...እል ነበር።
ሱቅ ተቀምጨ...ሹመት የሚባሉ ጎረቤታችን. ..ህፃን
ልጃቸዉን...ከኬጅ ሲመልሱ አያቸዋለኹ...ቦርሳዋን በእጁ
አንጠልጥሎ...አንድ እጇን በሌላኛዉ እጁ ይዞ...እሷ
አይስክሬሟን እየላሰች..."ሰላም" ብለዉኝ ያልፋሉ... የእሱም
ግን ከማሰመሰል የዘለለ አይደለም እላለኹ... እናቴ እንደዛ
ነበረች...እናትም አባትም...ይኼ ቦይፍሬንዷ ቤታችን ከገባ
በኋላ ደግሞ መኮርደድ ስጀምር...እሷ እያረጀች...እኔ
ወጣትነቷን ስመስል።
ኹሉም ፉርሽ መሆኑ ገባኝ...ይኼ ቦይፍሬንድ ተብየዋ
አይኑ ከ'ሷ ተነስቶ ወደ'ኔ ሲዞር...ቤታችን ግድግዳ ላይ
የተሰቀለዉ በዉብ ወጣትነቷ የተነሳችዉ ፎቶ ሰዉ የእኔ
ሲመስለዉ... ከልጅነት ማዕረጌ አሸቅንጥራ ጣለችኝ።
...መልበስ...መታጠብ...መስታዎት መመልከት ለ'ኔ የአርዮስ
ተግባር ኾኑብኝ።
እኹድ...ከሰኞ እስከ ቅዳሜ የሌለኝ ጊዜ ሲለሚስጠኝ...
ፀጉሬን ለሳምንት እንዲኾነኝ አድርጌ ለመታጠብ እና ለማበጠር
ስቀመጥ "ወይዘሪት...ሳሙናና ቅባቱ አያልቅብሽ...ደግሞ በሌለ
61
| ናትናኤል ዳኛው
ዉኃ" ትለኛለች...ያኔ ነዉ ኹሉም ፉርሽ ነዉ...ማስመሰል ብቻ
ነዉ የምለዉ።...እናም ይኼም ሹመት የሚሉት ሰዉየ ራሱ
ሲያስመስል ነዉ።
ዛሬ ደግሞ አባቴ ሞተ ብላ ስታለቅስ እያየኋት ነዉ።
...ለያዉም የኔ የልጇ ትከሻ ላይ...ለያዉም ለ'ኔ እንኳ ነግራኝ
የማታዉቀዉም ገጠር ልትኼድ ቦርሳዋን አዝላ።
እሷን ሸኝቼ ስገባ...ቦይፍሬንድ ተብየዋ...በረንዳ ላይ
ቆሞ...ስልኩን እየጎረጎረ አገኘኹት።...እርቦኝ ነበር... ማንም
አብስሎ እንደማይጠብቀኝ አዉቃለኹ...እማዬ የምታበስለዉ
ለ'ሷና ለሰዉየዋ ያህል ብቻ እንደኾነ አዉቃለኹ።
...ፈጥኜ ደብተሬን ወርዉሬ...ዩኒፎርም ኮቴን...አሮጌ ሶፋ
ላይ አንጠልጥየ...ወደ ጓዳ ገባኹ።
ትናንት ከት/ቤት ስመለስ የገዛኹት አስቤዛ ኹሉ
ተሟጦ...ጥቂት እንኳ "ለእሷ" ብለዉ ያስተረፉት ነገር አጣኹ።
...ርቦኛል...በጣም። ርሃብ ደግሞ ክፉ የእናት ዉሽማ
ነዉ...ያዋሽካል ለኾድ...ኾድ እየሞረሞረ እረፍት ይነሳል።
...የሽሮ
ዱቄት
ፈልጌ...ደረቁን እንጀራ እያጣቀስኩ
በላኹና...ዉኃ ቸለስኩበት...ዉኃዉ መርጋት አቅቶት እየተንጓጓ
ኼዶ ፊኛየ ላይ ሲቋት ታወቀኝ...ስለራበኝ 'ረስቸዉ እንጅ
ቀድሞዉኑ ሽንቴ ወጥሮኝ ነበርና...ሽንት ቤት ኼድኩ።...እንደ
ሰሚ ብቻ ወዳጅ እቆጥረዋለኹ ሽንት ቤቱን...ብሶቴን ኹሉ
እዘረግፍበታለኹ... ይሰማኛል።...ከሽንት ዉጭ ያሉት ቦታዎች
62
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ለኔ የሚኾን... ለኮረዳነቴ የሚያዝን የፈነደቁ ጡቶቼን
የማይበት ጊዜና ነፃነት የላቸዉም...ያላጉኛል...እያደከሙ
ሊያበርቱኝ።
ሽንት ቤት ቆይቼ ስመለስ...ቦይፍሬንዷ በረንዳ ላይ
ከሰዎች
ጋር
ሲያወራ
ተሰማኝ...ሊሸኛት
እንኳ
አልሞከረም...ቤት ዉስጥ ለያዉም በረንዳ ላይ የመቆየት
ልምድ የለዉም...ዛሬ ግን እሷን ላለመሸኘት...'ርቃ
እስክትኼድለት...እንደ አሮጌ ዉሻ...እንደ አኮረፈ ዉሻ...በረንዳ
ላይ ኾነ ይልመጠመጣል።
...ድምፁ አስቀያሚ ነዉ...የሚገረፍ ሰይጣን ድምፅ እንኳ
የ'ሱን ያህል አይሰቀጥጥም...Well ስለምጠላዉ ሊኾን
ይችላል።
.
በደንብ አላተዋልኩትም እንጅ ግንባሩ ላይ ትኩስ ቁስል
አይቻለኹ...ስንጥቅ ቁስል...በማሰሻ ተግሎ የተተመተመ
ቁስል...መጠየም የጀመረ ቁስል...ማታ ጠንብዞ እየተገላወደ
ሲገባ...እማዬ ስትጮህ ነበር።
"ምን ኾናችኹ?" ብየ አልወጣኹላትም እንጅ...አኹን
ቁስሉን ሳይ ፊቱ ላይ የሚዥረበረብ ደም አይታ ነበር
የጮኸችዉ...እያባበለችዉ ጡቷን አንተርሳዉ (ኹልጊዜ እንደዛ
ነዉ የምታደርገዉ)።
63
| ናትናኤል ዳኛው
ጠራችኝ..."አቤት!"
ዉስጥ እንደኾንኩ)
አልኳት(እዛዉ
የማድርባት
ሱቋ
"ይኼ ምንድን ነዉ የሚባለዉ..እ..ም...እ..."
"ምኑ?"
"ቁስል የሚተኮስበት"
"መተኮሻ ነዋ!"
"ወጠጤ
እንጅ?"
ይተኩስብሽ...ምጣድ
የምትወለዉይበት
"እ የማሰሻ ጨርቅ ነዋ!"
"አዎ...እሱ...የት ነዉ የምታስቀምጭዉ?"
ይች ሴትዮ ከዚህ በፊት እንደዚህ አልነበረችም...ቢያንስ
እንደህ አትጮኽብኝ ነበር... አሳዝናት ነበር አለአባት
በማደጌ...የሚገባኝን ሰጥታኝ በአለማደጌ... ዛሬ ኮርድጄ
አስጠላኋት... ፍቅርተን ሰለቸኋት!?... ማመን የሚከብድ ነዉ...
ለሌላዉ ሰዉ... ለእኔ።
ግን ሳይደግስ አይጣላም እንደምትሉት...ኃሞተ መራራ
አድርጎኝ...ጥላቻ አያስፈራኝ...ጥቁር እይታ አያስደነግጠኝ...
አካሌ ይኮርድድ እንጅ ልቤ ሽማግሌ ነዉ...ኹሉን አዉቆ
የረጋ..ፈገግ የሚል በሞኝ ድርጊትና ሃሳብ።
64
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"ጓዳ ጊቢ ፊትለፊት ታገኝዋለሽ"
ከዚህ በኋላ የፈለገችዉን ያህል ጮክ ብላ ብትጣራ አቤት
አልላትም...አንዳንድ
ቀን
የሱቋን
በር
በድንጋይ
ትደልቃታለች...Of course በዚህ መደንገጤ አይቀርም...
ምንስ አድጊያለኹ ብል ሞሳነት ሩቄ አይደለም።
ጠዋት ወደት/ት ቤት ስኼድ እነሱ ከእንቅልፋቼዉ
አልነቁም ነበር
....እና አኹን ስመለስ...አባቴ ሞተ ብላኝ ገጠር ኼደች።
...ስንብት በሚመስል መልኩ አቅፋኝ...እንባዋን በጡቶቼ ሰርጥ
አርግፋ...ልቤ ዉስጥ አቁራ ኼደች።...ስለዚህ ሰዉየዋ ግን
ያለችኝ ነገር የለም።
እስክትመለስለት
ቤቱን
ለቆልኝ
ቢወጣ
ደስ
ይለኛል...ቢኼድ...ከዛ ደግሞ ባይመለስ። ያዉቃል እሷ ከሌለች
የሳንቲም ቁራጭ እንኳ እንደማልሰጠዉ...ሰክሮ እንደ ሱሪዉ
እየተንጀላጀለ
ቢመጣ...ደንግጦ
በር
የሚከፍትለት
እንደሌለ...ቢደማ ደሙን የሚጠርግለት... ጣቶቹን አንተርሶ
የሚያባብለዉ...በሽሮ ፈትፍቶ የሚያጎርሰዉ እንደሌለ
ያዉቃል።... ይች የኔ ፉርሽ እናት (ዛሬ እንዲህ ታሳዝነኝ)...የ'ሱ
ቅንዝራም ዉሽማ የነበረች እስክትመለስ
ባይመጣ...ባላየዉ ባያየኝ ደስ ይለኛል።
65
| ናትናኤል ዳኛው
ለተወሰኑ ቀት ያህል ጠፍቶ ቆየና አንድ ቀን መጥቶ
አንገቱን ደፍቶ ፊቴ ቆመ...ላየዉ እንኳ እጠየፋለኹ።...ዛሬ ግን
ከሱቋ ፊት ለፊት እንዳየዉ ኾኖ ቆመ... ተበሳቁሏል... ልብሶቹ
ነትበዋል...ቆሞ የሚኼድ የቃሊቲን መንገድ መስሏል...ቡላ
አፈር።..."ፍቅር
ይህን
ነበር
የምታቅፈዉ?"
አልኩ
ለራሴ..."ይኼን ፊት ነበር ጡቶቿን የምታተርሰዉ... ለያዉም
በነዚህ
ከንፈሮቼ
የሳብኩትን
ወለላ
አመንጪ
ጡቷን"...የኮረዳነት ስጦታዬን...የደረቴን ጉልት በምናቤ ላያት
ሞከርኩ...አቅለሸለሸኝ...ወንድ ቀምሼ ቢኾን ኖሮ...አርግዣለኹ
እንዴ? ብየ 'ራሴን እጠርጠጥር ነበር።
...እየቆየኹ ሳየዉ ያሳዝናል...አንገቱን ደፍቶ ቆይቶ ቀና
ሲል...ዐይኖቹ የዋህ ናቸዉ...ልብ ያባባሉ...ፍቅርተን ባይኖቹ
እንዳባበላት ገባኝ።
ኹለት የአስር ብር ኖቶች አዉጥቼ አሳየኹት...እየሳቀ
መጥቶ ተቀበለኝና ሊኼድ ብሎ እንደገና ተመልሶ
"ቤርሲ ርቦኛል" አለ...ስታወክ ታዉቆኛል...ርሃብን
አዉቀዋለኹ...የሚጠሉትም ሰዉ ሲርበዉ ያሳዝናል... ጅብ
እንኳ ሲርበዉ ያሳዝናል...አለ አይደል አንድ ጭኔን በሰጠኹትና
በጠገበ ያስብላል።
...በተለይ እንደዚህ አይነቱ ቅስምጥ...እንኳንስ ተርቦ
እንዲያዉም ንትብ ነዉና...ተራብኹ ሲል ያሳዝናል።
66
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በሰጠኹት ብር ምግብ እንደማይገዛበት ሲነግረኝ
ነዉ...እኔም አዉቃለኹ...ሌላ ራቅ ያለ ቦታ እንኳ አይኼድም
እዝችዉ ፊትለፊቴ ካለች...ያ ወጠጤና ጓደኞቹ ሲገቡባት
ካየኋት ጠላ ቤት ገብቶ ነዉ...ፋሻ ብሎ የሚወጣዉ።...የደሃ
ትልቁ በደሉ ሰክሮ እንኳ ነገረኛ መሆኑ ይመስለኛል...መፅሃፍ
ደሃ የሚጠጣዉ ድህነቱን እንዲረሳ ነዉ ቢልም...ሃቁ ግን ደሃ
አይረሳም...የረሳዉን ኹሉ አስታዉሶ ነገረኛ ይኾናል እንጅ።
...እናም ይኼ ንትብ የእናቴ ዉሽማ...በእናትና ልጅ መኻል
የመራራቅ ግንብ ያቆመ ጣ'ረ ሞት መሳይ ሰዉየ...ብር ወስዶ
እንኳ "ቤርሲ...ርቦኛል!" ይለኛል
"እያወቅሽ ብሩማ የነገረኛነት አልበሜን ልቀዳበት ነዉ!"
በሚል ትርጉም
ቤርሲ
ሲል
ከሰማኹት
ቆይቻለኹ...
በተለይ
እንደማልፈራዉ ካወቀ በኋላ ጠልቶኛል በስሜ አይጠ ራኝም
ነበር።
አበላሉ...እህል የናፈቀዉ አይነት ነበር።
አንድ ከሰዓት የዩኒፎርም ኮቴን ከራሴ በላይ ዘርግቼ
ከት/ቤት ስወጣ ከርቀት ሆኖ ''ቤርሲ..'' የሚል ድምፅ ሰማሁ...
እርግጠኛ ስላልሆንኩ እስኪደገም ድረስ ጠበቅኹ። ደግሞ
''ቤርስ...''አለ
67
| ናትናኤል ዳኛው
የወንድ ድምፅ በመሆኑ ግራ ቢገባኝም ዞርኩ...ልቤ
ስትቀልጥ ታወቀኝ… ያ ጠይም ወጠጤ እንደኔዉ ዩኒፎርሙን
አናቱ ላይ እንደ ዣንጥላ ዘርግቶ ወደኔ ሰከም ሰከም እያለ
ይመጣል።እንዳየሁት...ተንቀሳቃሽ ድንኳን መምሰሉን አስቤ
እኔም ለሚያየኝ እንደሱዉ መሆኔ ገብቶኝ ፊቴ ላይ ፈገግታ
ልትረጭ ታገለችኝ።
በቀስታ እየተራመድኩ... (ላለመቆምም ላለመሄድም
ዓይነት)... ጠበቅኹት።
መጥቶ ከጎኔ ሲቆም ጥላዉ ከበደኝ...ጥላዉ እንደአካሉ
ፈርጣም ሆነብኝ... ፀሃዩን ለመከለል የዘረጋሁት ኮቴ...የእሱን
ፊት ከማየት ከለለኝ።...እሱም ፊቴን የከለለዉን ኮቴን እንጂ
ፊቴን ማየት አይችልም።
ጥቂት ደቂቃዎች በዝምታ ተኩለዉ አለፉ። ከት.ቤት
ወደቤቴ ስሄድ ሁልጊዜ የምትፈትነኝ እጥፋት ዳገት ጋ ስደረስ
ቆሜ ለመረጋጋት ስሞክር እሱ እርምጃዉ ሳይስተጓጎል ቂብ
ብሎባት ሲያልፍ አየሁት።...የባቱ ቁርጥ ከዩኒፎርም ሱሪዉ
በላይ ታየኝ እና ''በዝች ነጥብ ዕድሜ እንዴት የዚህ አካል
ባለቤት ሆነ?''ብየ አሰብኩ
ዳገቷን ከወጣ በኋላ ከጎኑ አለመኖሬ ታዉቆት ወደኋላ ዞሮ
ሲያይ አፌን ገርበብ አድርጌ ትንፋሽ ሰብስቤ ጉርዴን በግራ እጄ
ወደላይ ሸክፌ ስይዝ ደረሰ...ጭኔ በትንሹም ተጋልጣ ስለነበር
ዐይቶ በሃፍረት አይኑን ሰበር አድርጎ እጁን ዘረጋልኝ።
68
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
እጁ ግሏል...ስስ ቆዳየ እንደ ፌስታል ስትኮማተር ታወቀኝ።
ሁልጊዜ የምትፈትነኝን ዳገት ሳትታወቀኝ ተሻገርኳት።...ትንሽ
ከተሻገርን በኋላ ''እ...''አለ
ዘወር ብዬ አየሁት...''ስለ egsece* ምን አሰብሽ?''አለ
''ማለት?'' አልኩት
''ፍሬንዶች
ጋ
እየተገናኜን
አስበናል...ከተመቼሽ ተቀላቀይን?'' አለ
ሽት
ልንፈልጥ
ትንሽ ዝም አልኩ...ከንግግሩ ኋላም እኔን የማጥመድ ሴራ
ነገር ያለች መሰለኝ ለራሴ አሹ አልኩ...''ቤት ሰዉ የለም...ከት.ት
በኋላ ሱቅ እከፍታለሁ'' አልኩት
ፊት ለፊታችን አሮጌ ወፍጮ ቤት አለ...ከቤቱ ዉጭ
ከተቸከለች እንጨት ላይ የታሰረች አህያ አለች... የምታምር
ገብስማ ዉርንጫ ከርቀት እየዘለለች መጥታ አፏን ከጡቷ
ወትፋ ጎሰመቻት...አህያዋ ሆዷን ሳገች...አእምሮየ ላይ የኔዋ
ፍቅር መጥታ ተሰነቀረች...ልቤ ሂጄ የመሸጎጥበት የእናት እቅፍ
አለመኖሩን አስባ በረዳት... ይሄን እያየሁ ፈዝዤ ለጥቂት ደቂቃ
ያለዉን ሳላዳምጠዉ ቀረሁ።
ዐይኔ እንባ አቁሮ ስመለስ...በድንጋጤ እያየኝ ነበር
''ምነዉ...?" አለኝ
69
| ናትናኤል ዳኛው
እንባየን ከዐይን አርግፌ ዝም አልኩት..እስከ ሰፈሬ
መግቢያ ድረስ ሸኝቶኝ ሊመለስ ሲል
"በኋላ ሱቅ ልምጣ?" አለኝ
በአንገቴ እሽ አልኩት...ልቤ በደስታ አለች
አመሻሽ አካባቢ የሱቄን መስኮት ልዘጋ ስዘገጃጅ ከርቀት
አየሁት...ሁለት ጓደኞቹ ጋር ቆሞ እያወራ ነበር። ቶሎ ብየ
መስኮቷን ዘግቼ ቤቴ ገባሁና በግድየለሽነት የተዉኳቼዉን
አንዳንድ ነገሮች ማስተካከል ጀመርኩ።...የወለል ንጣፉን
እየወለወልኩ...የሶፋ እግር ስር የደለቡ ቆሻሻዎች መኖራቼዉን
አስቤ ዝቅ ብየ በመጥረጊያ ስስብ በማሾ የታፈነ የአንድ ጆሮ
ጌጥ አገኜሁ...ትንሽ አፈር በልቶት መጠየም የጀመረ ነጭ የብር
ጌጥ ነዉ...የፍቅር ነበር...የእኔ ጆሮ ጌጥ አንጠልጥሎ
አያዉቅም...አተኩሬ እያየሁት ቆይቼ... ቀና ስል... የእኔን
ኮረዳነት የሚመስ ለዉን የፍቅር የወጣትነት ፎቶ ጋር
ተላተምኩ... ያደረገችዉ ይህንኑ ጌጥ ነዉ...ምን ያህል ትወደዉ
እንደነበረም አዉቃለሁ...አሁን ነዉ ያሰብኩት...ይሄ ንትብ
ፍቅረኛዋ በሌባ ዝናብ ቤታችን ከገባ በኋላ ይህን ጌጥ ጆሮዋ
ላይ አይቼዉ እንደማላዉቅ...ጆሮዋ ላይ ጌጥ አይቼ
አላዉቅም።
...የአባቴ ስጦታ እንደነበረ ባትነግረኝም አዉቃለሁ...
መንታዉን ፈልጌ አጥቤ ለራሴ እንደማደርገዉ እየዛትኩ...
ከመፅሃፍቶቼ አንዱን በደመነፍስ ገልጨ ሻጥኩት።
70
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የግቢዉ በር በተደጋጋሚ በለስላሳዉ ሲንኳኳ ሲሰማኝ
ከዐይኔ የተቋተ እንባየን ጠርጌ ልከፍት ሄድኩ። ፊት ለፊቴ
ሸንቃጣ ሆደስልግ መፅሃፍ በግራ ዕጁ ይዞ አገኜሁት። የግዴን
ፈገግ ልል እየሞከርኩ...ዐይኔን አንሻፍፌ የመፅሃፏን አርዕስት
ለማንበብ እየሞከርሁ ''ግባ'' ብየ የማርያም መንገዱ
ሰጠኹት። የመፅሃፏ ሽፋን ላይ ፊቷ የማይታይ ሴት ስዕል
አለ...ሴቷ ሰዉነተ መልካም ዓይነት ናት። መፅሃፏን ባላነባትም
በስም አዉቃታለሁ... ስለደራሲዉ አንደበተ ርቱዕነትም።
ለምወደዉ አድልቼ ራሴን ያስደሰትኩበት ቀን ጥቂት ቢሆንም
ስነፅሁፍ ለልቤ ቅርብ እንደሆነ ምዚ ''እዚህ ሱቅ ስትዉይ
እንዳይደብርሽ እነዚህን አንብቢ" እያለች ካዋሰችኝ ጥቂት
መፅሃፍትን የማንበብ ልምዴ ተረድቻለሁ። ምዚ በተደጋጋሚ
ካዋሰችኝ በኋላ አንድ ቀን "የትኛዉ ደራሲ ተመቼሽ?" ብላ
ጠየቀችኝ..እኔም ጥቂት ከአመነታሁ በኋላ "እንጃ እስቲ...ግን
የ"ማህሌት" ደራሲ ለነፍሴ ቀርቦልኛል።"አልኳት
ፊቷ በደስታ አበራ..."እሱ ለሁላችንም ነዉ" አለችኝ
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መፅሃፍትን ባላነብ እንኳ ማየት ደስ
ይለኛል...በቻልኩት
መጠንም
ወደ'ነሱ
ለመቅረብ
ሞከርኩ...አልፎ አልፎ ፌስቡክን የማየት ፈንታ ሳገኝም ወደ
ደራሲዎቹ ገፆች ነዉ የማመራዉ።
ቤት ገብተን መፅሃፏን ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠ ሶፋ ላይ
ራሱን አደላድሎ ተቀመጠና ዙሪያዉን አየ። ሌላ ሰዉ
71
| ናትናኤል ዳኛው
አለመኖሩ ገባዉ መሰለኝ ዘና ለማለት ሲሞክር አየሁት
ወዲያዉ "የሆነ ቀን ምዚ ...ቤርሲ ጊዜዉ ስሌላት ገበያ ወጥታ
አትገዛም እንጂ ጥሩ የማንበብ ልምድ አላት ' ብላኛለች...ለዛ
ነዉ 'በፍቅር ስም'ን ያመጣሁልሽ"አለ
"ምዚ!...ምዚ ኩሸት ትወዳለች... ስታዳንቅ ነዉ... አንተን
ግን አመሰግናለሁ።"አልኩት
ወዲያዉ ወሬ ለመቀየር ያህል"ይልቅ ባለፈዉ 'የአሌክስ
ኮፍያ' የምትል አጭር ተረክ ፌቡ ላይ አንብቤ ገረመኝ" አልኩ
"እ...እኔ አላየሁትም...ትንሽ ለየት የሚል ይመስላል.."
አለ...ካመላለሱ ቀልቡን የሰረቀዉ ሌላ ነገር ያለ ይመስላል።
"አዎ...እሱ ዓለማየሁ ኮፍያ ያዘወትራል መሰለኝ...እና
ፀሃፊዋ የሆነ 'fictional intimacy* ለመፍጠር ነዉ
የሞከረችዉ"
"ኦ...የሆነ አርት ያለዉ ይመስላል...ሴት መሆኗ ግን ደስ
ይላል"
"እንዴት?"
"ቅር አይበልሽ...የሴት ደራሲያን ጠኔ አለብን ብየ ነዉ።"
72
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"..ሃሃ..አይገርምም.. ባለፈዉ ምንአለበት... የሴት
ዘፋኞቻችን IOTA ያህል እንኳ ሴት ደራሲዎች ቢኖሩን? እያልን
ስንቆጭ ነበር ምዚ ጋር።
73
| ናትናኤል ዳኛው
ያ ጠይም ወጠጤ
ቤርሲ "ጠይም ወጠጤ" እንደምትለኝ ምዚ ስትነግረኝ...
በጣም ነዉ የሳቅኹት...
ብዙ ሰዉ ምዚን የማፈቅራት ይመስለዋል...ያ አቤል እንኳ
የነጠቅኹት መስሎት ጠልቶኛል። ምዚዬ ዉድ እኽቴ ናት...
ይችን በፍቅር አክሊል የተከበበች ሴት ከጓደኝነት ዘልየ
አላሰብኳትም። የሐሜት ወንጭፍ እንዳጣመረን ግን
ኹለታችንም እናዉቃለን። እኔም እሷም የልባችን ወዳጆች
ከጓደኝነት ሜዳችን ዉጭ እንደመኾናቸዉ ሐሜት ፈርተን
ቢያንስ ት/ቤት አብረን ላለመታየት አቀድን። ቤርሲ ግድ
እንደማይላት አዉቃለኹ። ለብዙ የት/ት ቤት ታሪኮች ሩቅ ናት።
ክላስ አርፍዳ እንደመግባቷ ቀድማ ትወጣለች። ምዚዬ ታዲያ
"ቤርሲ እኮ ትልቅ ሰዉ ናት ሰርታ ቤተሰብ ታስተዳ ድራለች...
ለዛ ነዉ የምትጣደፈዉ እንጂ ልጅነታችን በ'ሷ ጨዋታ
ወዳድነት የታጀበ ነዉ" ትላለች::
ትንሽዬ ሱቅ እንዳለቻቼዉና ቤርሲ እንደምትሸቅ ጥባት
አዉቃለኹ።
ምዚን ሰበብ አድርጌ ቤርሲ ጋር ተዋዉቂያለኹ። እጇ
ሸከራ ነዉ...። የየሰዉ የህይዎት ታሪክ በመዳፉ ሸካራነትና
ልስላሴ የሚታወቅ ይመስለኛል። የቤርሲ መዳፍ ሸካራነት
74
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
አኗኗሯን ተርኮልኛል። ከዛ በኋላ አዝንላታለኹ። በተለየ ግን
ከምዚ የምሰማቼዉ ፉተታወቿ...በተለይ እኔን የሚመለከቱት
ይበልጥ ያስቁኛል...ፀጉሬን ፓንክ ስቆረጥ የእንትን ፀጉር
መሰለች ትለኛለች አሉ...የእንትን ፀጉር ምን እንደደሚመስል
የምታዉቅ እሷዉ ናት።
ጠይም ወንድ ፀጉሩ ሉጫ ሲኾን አልወድም ማለቷ ግን
አስኮርፎኝ ነበር።
ከመተዋወቃችን በፊት ኹለት ጓደኞቼ ጋ ክላሳቸዉ ፊት
ለፊት ኼደን እንቆም ነበር...ግን ስታየን ተነስታ ወደ ዉስጥ
ትገባለች።
ትሸሻለች...ምክንያቷ የኮረዳነት ጫንቃዋ ላይ የወረደዉ
ኃላፊነት ይመስለኛል። ከሩቅ ኾኖ ለሚያያትና የዉንጀላ ዓለም
ዉስጥ ለሚኖር ከንቱ ሰዉ...ተራ አኩራፊ ተፈጥሮ ያላት መስላ
ነዉ የምትታየዉ።...ጫንቃን ገልቦ የሚያይ የለም...ኹሉም
በሃሜት ጌሾ የሰከረ ነዉ።
አንድ ወቅት በተዳጋጋሚ ከት/ት መቅረት አበዛች...በጣም
እራባት ነበር...ጓደኞቼ ትካዜየ ቢበዛባዬዠቼዉ ለምን ሰፈሯ
አንኼድም...እዚኽ ቅር እነምዚ ሰፈር ነዉየምትኖረዉ ብለዉ
አኳሹኝና ከት/ት እንደተለቀቅን ደብተራችንን በጃችን
እንደያዝን የዩኒፎርም ኮችንን እያወናጨፍን ኼድን።
75
| ናትናኤል ዳኛው
በርቀት ትንሽየ ሱቋ ዉስጥ እንዳለች ለየኹኣት።
...እየቀረብን ስንመጣ እግሬ አቅም ሲያጣ ይታወቀኝ
ነበር...እነዛዉ ጓደኞቼ ግን "ሳናስነቃ ጠላ ቤቷ እንገባለን" እያሉ
ወሰዱኝ።
ወደ ሱቃቼዉ ስንደርስ እሷም ለየችን መሰለኝ
እንደለመደችዉ ለመሸሽ ስትሞክር የስካር ልምድ ያለዉ
የሚመስል አንድ ሰዉ እየተጣደፈ ጠርቶ "ሲጋራ" አላት። የዛኔ
ቀናስትል ዐይን ለዐይን ተጋጨን...ፈጥኜ ዐይኔን አሸሸኹ።
ይኼ በሴትና በወንድ መካከል ነበረ የሚሉት የ"Prey and
predator" ዘመን ያለፈ ይመስለኝ ነበር...ይች የኔ ግን አኹንም
እሱን መተወን ያምራታል።
አልፈን ጠላ ቤቷ ገብተን ተቀመጥን። እንዲህ አይነት ቦታ
ስገኝ የመጀመሪያየ ነዉ...።
ጠላ ቤቷ በረንዳ ላይ ተቀምጨ ጓደኞቼ የጀመሩትን ደረቅ
የአልኮል መጠኑ እንኳ የማይታወቅ ጉሽ ነገር እስኪጨርሱ
ተክዤ እጠባበቃለኹ። "ሰዉ ምን ይለኛል?" ብሎ ማሰብ
አልወድም እንጂ ይኼ ያልበሰለ ገላ ይዞ እንዲህ ዓይነት ቦታ
መገኘት በሚወዱት ፊት ምን ትርጉም እንደሚያሰጥ
አይጠፋኝም። ጠላ ቤቷ የትያትር መከወኛ ነዉ
የምትመስለዉ...የሚያስቁት ነገሮች ይበዛሉ። የዘመን
ተጋሪዎቼ ጀግነዉ ገብተዉ ነፍዘዉ ሲወጡ ማየት ግን ጥያቄ
ፈጠረብኝ "የማን ስህተት ነዉ?" እላለኹ
76
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"የዕድሜ?"
"የወላጅ?"
"የሀገር?"
ወይስ"የኛዉ የልጆቹ የራሳችን?"
ቤቷ በሲጋራ ጢስ ትታጠናለች ወፍራም ድር እየሰራ
ከበሯ ሾልኮ ይወጣል። በረንዳ ላይ ከአፍ እንደወጣ አየር
ከሚበትነዉ ስስ የጢስ ድር ተቀላቅሎ ይሸሻል። እኔ ይሄን
በትካዜ እያስተዋልኩ በጢሱ የምናብ አርት እየሰራኹ
እተክዛለኹ። ወዲያዉ ደግሞ ቀልቤ ወደ ቤርሲ ይመለሳል።
አንድ ከሰዓት ድንገት ከክፍል ስወጣ ኮቷን ከአናቷ በላይ
እንደ ድንኳን ዘርግታ እንደ ሰጎን ትሳብ አየኋት።
አላመነታኹም እኔም እንደሷዉ ከፀሃይ ለመጠለል የዩኒፎርም
ኮቴን ከአናቴ በላይ ዘርግቼ ተከተልኳት። ገና በርቀት እንለኹ
"ቤርሲ" ብየ ጠራኹዋት አልሰማችኝም
ለሁለተኛ ጊዜ "ቤርሲ" ስል ዘወር ብላ አይታ ቆማ
ጠበቀችኝ። አቤ...ት የዛኔ ልቤን የሰማ!!...ተንኖ የሚኼድ ያህል
ነበር የከዳኝ።
ሰላም ብያት ወደ ቤቷ እየሸኘኋት ነበር። ጥቂት በዝምታ
ከተጓዝን በኋላ
77
| ናትናኤል ዳኛው
"ስለ egsece ምን አሰብሽ?" ብየ ጠየቅኋት....በሃሳብ
ተጉዛ ነበር መሰለኝ
"እ" አለች
"ስለ egsece ምን አሰብሽ?" ደገምኩላት
"ምንም" አለች
"እየተገናኘን ሽት ልንፈልጥ አስበናል ተቀላቀይን"
"ከሰዓት ሱቅ እከፍታለኹ...ቤት ሰዉ የለም " አለችኝ
ይኼን አዉቅ ነበር...በጊዜዉ እሷን ማጥመጃ ሳስብ
የመጣልኝ ያ ኾኖ ነዉ እንጂ...ከ'ኛ የራቀች ጫንቃዋ ከተማሪነት
እስከ ቤተሰብ አስተዳዳሪነት የተዘረጋ መኾኑን አዉቃለኹ።
ሰዉ ቤት የለም ማለቷን "ቤት መምጣት ትችላለህ"
ማለት ነዉ ብየ ተረጎምኩትና
"ከሰዓት ሱቅ ልምጣ?" አልኳት.
አለችኝ...ልቤ በደስታ ጮቤ ረገጠች
..በራሷ
"እሽ"
የኾነች እጥፋት ጋ ያለች የኾነች ትንሽየ ዳገት ላይ ቂብ ብየ
አልፌ ዘወር ስልጉርዷን በእጇ ይዛ፡አፏን ገርበብ አድርጋ
ትንፋሽ እየሰበሰበች አየኋት። በትንሹ የተጋለጠ ጭኗን ሳይ
ደነገጥኹ...ወዛም ጠይምነት አላት...ልብ ቀጥ የሚያደርግ...
እንደምንም አይኔን አሸሽቼ እጄን ዘረጋኹላት። በእጆቻችን
78
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
መካከል የነበረዉ ግለት በቆሎ የመጥበስ አቅም ይኖረዉ
ይመስለኛል።
በተደጋጋሚ
በሀሳብ
የምትጠፋዉ
ነገር
ግራ
ያጋባኛል...የኾነ አሮጌ ወፍጮ ቤት ደርሰን ልሰናበታት ስል
የወፍጮ ቤቱ ቸሓል ላይ የታሰረች አህያንና ዉርንጫዋን
እያየች አይኑዋ እንባ ሲያቀር አየኹት። ግራ ገባኝና ልሰናበታት
ፈለግኹ።
እሷን ሸኝቼ ቀጥታ እየተጣደፍኩ ወደ ወደ ቤቴ ሄድኩ።
እናቴ ደጅ ላይ የተከካ አተር እያነፈሰች አገኘኋት። ደጋግማ
ታስላለች። አባቴ ሳሎን ላይ ያለ አልጋ ላይ ጋደም ብሎ
ቴሌቪዥን ያያል። እህቴ ቡና ልታፈላ ከጓዳ ሳሎን
ትመላለሳለች።...እኔ በእናቴና በ'ነሱ መሃል የበረንዳዉን ኮለን
ተደግፌ ቆምኩ። ቴሌቪዥኑ ሰርቫንት ሊደርሽፕ ስለሚባል ነገር
እያወራ መስራቹ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ ይላል። እኔ
በዉስጤ "ሊኾን ይችላል...እኔ እማዉቀዉ ግን እናቴን ነዉ"
እላለኹ።...ቲቪዉ
አወራሩን...አባቴ
አሰማሙን...እኔ
ታዛቢነቱን...እናቴ ደግሞ አሰራሩን እናዉቅበታለን።
እናቴ "ግባ እንጂ?" አለችኝ
"እ..እሽ" ብያት ገባኹ።
ምሳ በልቼ...ቡናየን ከጠጣኹ በኋላ ስለቤርሲ ማሰብ
ጀመርኩ። ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ምዚ የነገረችኝን አስታዉሼ
79
| ናትናኤል ዳኛው
አንዲት አነስተኛ መፅሃፍ ይዤ ከጓደኛየ ጋር ወደ ሰፈሯ ሄድን።
ሰፈር ስደርስ ምዚ አባቷ ጋር የግቢያቼዉ በር ላይ ቆማ
አገኘናት። እኛን ስታይ እየሳቀች የኾነ ነገር ብላዉ ወደኛ
መጣች። ትንሽ ንዳወራን ቻዉ ብያቸዉ ወደ ቤርሲ ሄድኩ።
ሱቋ ተዘግታ ነበር። እየፈራኹ በለኾሳሳ በሯን ቆፈቆፍኩ።
በኹለተኛዉ ተከፈተ...ፊት ለፊቴ መጥታ ስትቆም ጥላዋ አካሌ
ላይ አረፈ...ወዲያዉ የማርያም መንገድ የምትመስል ሰጥታ
ግባ አለችኝ። ቤታቸዉ ደብዛዛ ዉበት አላት...አንድ ወቅት
የሞቀች እንደነበረች ታስታዉቃለች። ግድግዳዉ ላይ የቤርሲን
የሚመስል የ'ናቷ የልጅነት ፎቶ ተሰቅሏል።
በ'ጄ የያዝኳትን መፅሃፍ ጠረጴዛዉ ላይ አስቀምጨ አሮጌ
ሶፋዉ ላይ ተቀመጥኩ። እሷ ሻይ ላፍላልህ ብላ ወደ ጓዳ ገባች።
ትንሽ ዙሪያየን ካየኹ በኋላ ዉስጤ መፍታታት ጀመረ።
ከአወራሯ ብስለቷ ይታወቃል። ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ
'fictional intimacy' የሚል ቃል የሰማኹት...ለያዉም ከ'ሷ
አንደበት።
መፅሃፍትን ማንበብ ልዉደድ እንጅ ብዙም የተፃፉበት
ቴክኒክ የሚያሳስበኝ አይነት አይደለኹም። የማነበዉ መሪ
መኾን ስለምፈልግ ነዉ። የማልተገብረዉን ለቃል ዉበት ብየ
ብዙም አላነብም። ምዚየ በትረካ ብቃቷ አፌን ስታስከፍተኝ
የሷን ምርጫዎች አነባለኹ። የምሸሸዉ ድህነት...ማምለጥ
የምፈልገዉ ድንቁርና ቤቴና ከባቢየ ዉስጥ ስለሞላ ንባቤ
80
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ተግባር ተኮር ኾነ እንጂ ህይወት በነዛ በኩል እንዳለች
አዉቃለኹ።..ይችን ዛሬ ለሷ ያመጣኹላትን እንኳ ምዚየ ናት
ያስገዛችኝ።...ይች ቤርሲ ራሱ "ምዚ ኩሸት ትወዳለች"
ያለቻት...አንደበቷ ስለሚጣፍጥ..ቃሏ ስለሚያኳሽ ነዉ።
ፍቅር ታሳምራለች።
.
ሻዩን ከጠጣን በኋላ በመሃላችን ዝምታ ኾነ። ወዲያዉ
"በቃ ነገ እመጣለኹ" ብያት ልወጣ ተነሳኹ።
"ደስ ይለኛል" አለች ልትሸኘኝ እየተነሳች
ቪዛዬን አገኘኹ ማለት ነዉ። የግቢ በር ላይ ስንደርስ
"ለመፅሃፏ አመሰግናለኹ" አለችኝ
"ግዴለም አንብቢ እንጅ ሌላም አመጣለኹ" ብየ
በድፍረት ላቅፋት እጄን ዘረጋኹ...መጥታ ሽጉጥ አለች።
81
| ናትናኤል ዳኛው
ምዕዛር
የስሜ ልዩ መኾን ይገርመኛል። እና አባቴን " አባ!... ግን
ለምን ምዕዛር አልከኝ?" ብየ ብጠይቀዉ
"ልዩ ኾነብሽ አደል የኔ ቃጭል!?...ቃሉ የግዕዝ እንደኾነ
ነግሬሻለኹ አይደል?
እናትሽ ፀሓይ ናት።...አንች ደግሞ የ'ሷ ጨረር... ዘለላዬ...
እንደ መስፍ ልቤን የቦረቦርሽ" አለኝ
እንጀራ አባቴ(እአ) ልለዉ የሚያስችለኝ ነገር ብፈልግም
አላገኝም።...ምናልባት ፅንሰቴ ከሌላ ወንድ መኾኑ ብቻ
ካልኾነ። ግን አንዳንድ ጊዜ የኾነ ነገር ፈልጌ ጠይቄዉ አይኾንም
ካለኝ ብቻ ማኩረፌን ለመግለፅ በልጅነት ክፋት ሺህ ብትወደኝ
የእንጀራ አባቴ ነህ ስለዉ በ "አባ" ፈንታ "እአ" እለዋለኹ።
ፍሱን ከእናቴ አዋህዶ የፈጠረኝ ሌላ አባት (ስነ-ሕይወታዊ
አባት) ስለመኖሩ ያሰብኩበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። የዚህ
አባቴ ስም አወጣጥ ትንሽ ቅኔያዊ ይኾንብኛል..."እኔና አንቺን
ፍቅር እንጂ ጂን አላገናኘንም" ባይ ይኾንብኛል።
ለምለም የፀሓይን ጨረር የሚጠላ እንደሌለ
አዉቃለኹ...ዚሊየን ጊዜ ቢወዱም ግን ጨረሩ የፀሓዯ ብቻ
እንደኾነ ያዉቃሉ። እና ይኼ አባቴ ከፀሓዯ እናት ወደ'ኔ
82
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የተላክሽ 'ምዕዛር' ነሽ ብሎ ስም አወጣልኝ።. ..ስሙን
ብወደዉም ያራቀኝ እየመሰለኝ ቅር ይለኛል። ት/ቤት ቁጭ ብየ
ይኼን ሳስብ ይናፍቀኛል።...ደግሞ ከ'ኔ በጥቂት ርቀቶች
የተቀመጠዉ አቤል የእሱን ልጅነት እየመሰለኝ...ወረቀት
የሚገልጥባቼዉ ረዣዥም ጣቶቹ... ጉንጨን መዋጥ
እስከሚመስል ድረስ በኃይል ስቦ የሚስምበት አፉ...እጄ ላይ
ምራቄን እየተፋኹ "መላጣ ና ቡና ጠጣ" የምተመትመዉ በራ
ራሱ...ይናፍቁኛል። ነገረ ስራየ ኹሉ ጆሮ ኾኖ የመጨረሻዋን
ደወል በቋፍ ተቀምጨ እጠባበቃለኹ።...እንዲህ ብጣደፍም እኔ
ቤት ከደረስኩ በኋላ ከሰዓታት በኋላ እንደሚመጣ ግን
አዉቃለኹ።
ከዚህ በፊት እንደዚህ የመገፋት...የማራቅ...ስሜት
ሲሰማኝ ከት/ቤት እንደወጣኹ ቀጥታ ወደ ቢሮዉ እሮጣለኹ።
ትንሽ ምቾት የሚነሳ እንክብካቤ ያጋጥመኛል...ከቢሮ ቢሮ
ስመላለስ መንገድ ላይ ያጋጠምኳቸዉ ኹሉ ፊቴ በምራቅ
ጎርፍ እስኪታፈን ይስሙኛል።...እሱ የእኔና የእማን 'የ'ሱ
ፀሓይና ምዕዛሮች' ን ፎቶ ፊት ለፊቱ ጠረንፔዛዉ ላይ በፍሬም
አስቀምጦ... ትንሿን ኮምፒዩተሩን ከፊቱ አድርጎ ጣቶቹ
ኪቦርድ ላይ እየተልሞሰሞሱ.... አሻግሮ እንዳየኝ ፊቱ ይፈካል።
ከ'ሱ ጀርባ የሚያምር መጠነኛ የመፅሃፍ መደርደሪያ
አለ።...ከመደርደሪያዉ በላይ...ዉበቱን ከማድነቅ በዘለለ
ትርጉሙን ያልተረዳኹት ስዕል አለ (በመጣኹ ቁጥር ስለዚህ
ስዕል 'ዛሬስ ምን ተገለጠልሽ?' እያለ ይጠይ ቀኛል)።
83
| ናትናኤል ዳኛው
ቢሮዉ ዉበታም ናት። አባቴ የዉበት አድናቂ መኾኑን
ለማወቅ እናቴንና ጊዜ የሚያሳልፍባቼዉን አካባቢዎች ማየት
በቂ ነዉ።...እሱ ባለበት ኹሉ ዉበትና ፍቅር አለ።
አስተዳደጌ ኹሉ እሱን የሚመስል ነዉ። እንደሱ
በመፅሃፍት መከበብን እመርጣለኹ። እንደሱዉ ዉበትና
ፍቅርን አስሳለኹ። ታዲያ በዚህ ምክንያት ይመስለኛል ጓደኞቼ
"አንቺ በፍቅርሽ የተከበብሽ" የሚሉኝ። እንደ ሴት ማህበረሰብ
አስቀድሞ የፈረደብኝን ለመኾን የተዘጋጄኹ አልነበርኩም።
በዚህም ከእናቴ ጋር አንግባባም አንዳንድ ጊዜ "አንቺ ልጅ
ጓዳም እኮ ሙያ አለ" ትለኛለች ከአባቴ ጋር ተያይተን
እንስቃለን።
ስታኮርፍ ጓዳ ገብተን አባቴ ጋር ኮርኩረን አስቀናት
እንመለሳለን።
የዋህ ገፇ ከሚያበራ መልኳ ጋር ልዩ ያደርጋታል።...ከ'ሷ
ዉበትን ብወርስም የዚህ ሰዉየ ፍቅር ግን ያነግሰኛልና ብዙ
ነገሬ ለ'ሱ የቀረበ ነዉ።
ህይወትን ከምማረዉ ሳይንስ ወጥቼ ተራተርታዉ ትንሽ
ተብሎ የተናቀዉ ነገር ላይ መፈለግን የተማርኩት ከ'ሱ ነዉ።
ለነገ የምለዉ ደስታና ፍቅር የለኝም። መንገዴ በሰዉ የተከበበ
ነዉ።...የምነፍገዉ ዕዉቀትና ተሰጥኦ... የምሸሽገዉ ማንነት
የለኝም።
መፅሃፍቶቼን
ማንበብ
ለሚወዱ
እሰጣለኹ...ባገኘኹት አጋጣሚ ኹሉ ደግሞ በልፋትና በዚህ
84
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
እአየ ትግል ያመጣኹትን የትረካ አቅም ተጠቅሜ ለጓደኞቼ
እተርካለኹ።
ግን ምኑም ከ'ኔ የማይገጥም ቀለሜ ወደድኩ። ዕዉቀት
ሌትና ቀን ከሚጨመጭመዉ ሳይንስ ዉጭ ያለ
የማይመስለዉ ዝጋታም አፈቀርኩ። እኔን እያጮለቀ
የሚያይበት ዓይኑ የአባቴን ይመስለኛል። ነገር አመራመሩ
የእሱን ይመስለኛል። ከእጥፋቱ ላይ ከሌሎቻችን የጆሮ ቆዳ
በተለየ የ'ሱ ጆሮ ቀጥ ማለቱ የአባቴን ይመስለኛል። ለዓላማዉ
ትጋቱ የእአን ይመስለኛል።... በ'ሱ መታየትን ለመድኩት።
አስተያየቱ የሚመረምረኝ ይመስለኛል። ተፈጥሮየ ፍፁም
ተቃራኒ የሚኾነዉ ከ'ሱ ተፈጥሮ ጋር ይመስለኛል። እኔ በሰዉ
መከበብን የምወድ extroverted* ሴት ነኝ። እሱ ብቻን
መኾን የማይበርደዉ ስሜቱን አምቆ የሚይዝ Introvert*
ወንድ ነዉ። ባለችኝ የንባብ ልምድ ይመስለኛል በሃሜት ሰክሬ
እሱን ኩራተኛ ከማለት ይልቅ ተፈጥሮዉን ተረድቼ ልቀርበዉ
መሞከሬ።
በኼደበት ኹሉ መሪ መኾንን የማይሰለች...ባገኘዉ
አጋጣሚ ኹሉ በሰዉ ልብ ዉስጥ ድርሻዉን ከመዉሰድ
የማይመለስ ራዕዮ ጓደኛየ ደጋግሞ "ይኼ አቤል ይወድሻል!"
ይለኛል።
"ተዉ ባክህ እሱ ከሳይንስ ዉጭ አይወድም" እለዋለኹ
85
| ናትናኤል ዳኛው
ታዲያ ክፍል ዉስጥ የመጨረሻ ወንበር ላይ ይቀመጥና
ዓይኑ ኹለታችን ላይ ይኾናል። እዛዉ ኾኖ በቁራጭ ወረቀት
"ሰዉየሽ ተሟዞ ሲያሽ ነበር" ብሎ ፅፎ ይልካል
"ቤርሲ እዚህ ብትኾን አንተም ያዉ ነበርክ"ብየ መልሼ
እልክበታለኹ
...ቤርሲየ በልጅነት ጫንቃዋ ላይ ሀገር የተሸከመች ናት።
የልጅነት ትዝታየ ዉስጥ የሷን ያህል የሚጎላ ሰዉ ያለ
አይመስለኝም። ፍቅርተም እንዲህ አልነበረችም።
የቤርሲን ያህል ልጅነትን የሚያዉቅ የጨዋታ ልክፍታም
አላስታዉስም።...ድንገት ነዉ የህይወት መስመሯ ፈሩን ስቶ
ዛሬ እዚህ ላይ ያደረሳት። ማን ነዉ ነገዉን በ'ርግጠኛነት
የሚያዉቅ?
ነፃ ነዉ የምለዉ አቤል ለቧልታ ጊዜ የሌላት ህይወት ላይ
ቂም የያዘች የምትመስል በእልህ የተሞላችን ሴት አይቶ ብቻ
ወደዳት። በጣም ደስ አለኝ። ለምን እንደኹ ባላዉቅም በራዕዮ
ደስታኛ ነኝ። ኋላዉን አዉቃለኹ ደልቶት የሚኖር እንዳልኾነ
ግን ኹሉንም በሳቅ ሊያሸንፍ ይተጋል። ራሱን መሪ አድርጎ
ለመፍጠር ይተጋል። በአገኘዉ አጋጣሚ ኹሉ ተፅኦኖ
ከመፍጠር አይመለስም። ለእንቅስቃሴ የሚቀለጥፍ ፈርጣማ
ሰዉነት አለዉ።
86
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
አንድ ቀን በ'ረፍት ሰዓት የቤርሲ ክላስ ወስጄ
አስተዋወቅኩት። የዛን ጊዜ ነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈሪዉን ራዮ
ያየኹት። ...አስተዋዉቄዉ ስንመለስ "ማን እንደምትልህ ግን
ታዉቃለህ?" አልኩት ለሳቅ የተዘጋጄኹ
በጣም ሰፍ ብሎ "አላዉቅም" አለኝ
ሳልነግረዉ በጣም ሳቅኩ...ፊት ለፊቴ መንገዴን እየገረገረ
በጉጉት ይጠባበቀኛል...ልነግረዉ እልና መልሼ በሃይል
እስቃለኹ።
ሲበዛበት የአኮረፈ መስሎ ጥሎኝ ለመኼድ ሲሞክር
ተከትየ ይዤዉ ሳቄን የተቆጣጠርኩ
"ጠይም ወጠጤ ነዉ የምትልህ" አልኩት
"ዋት?" ብሎ በቆመበት በሳቅ ፈነዳ
ተያይዘን የተሳሳቅን ወደ ክፍላችን ሄድን። ወደ ክፍል
እየገባን ላስተክዘዉ ለፈለግኩ ሉጫ ፀጉሩን እየፈለስኩ
በጆሮዉ "ጠይም ወንድ ፀጉሩ ሉጫ ሲኾን አትወድም" ብየዉ
ዘልየ ወደ መቀመጫ ወንበሬ ኼድኩ
እዛዉ ኾኖ በአግራሞት ወገቡን በእጁ ይዞ ቆሞ እያየኝ
እያለ የፊዚካ መምህርና አቤል ተከታትለዉ ገቡ።
87
| ናትናኤል ዳኛው
እየተማርን በቁራጭ ወረቀት "ምዚ ግን የምርሽን ነዉ?"
ብሎ ላካ...
"አረ እንዲያዉም መርካቶ ከስሮ የቀረ ደቡብ ህንዳዊ ነዉ
የሚመስለኝ ኹላ ትላለች" ብየ ጨመርኩለት
በት/ቤቱ ስማችን በጥንድነት ሲነሳ ብዙ ጊዜዉ ቢኾንም
እንደ አኹን ግን አላሳሰበንም የእሱ ለቤርሲ መብሰልሰል ሲበዛ
እኔም ፍላጎቴ ወደ አቤል ሲሸፍት ቢያንስ ት/ቤት አብሮ
ላለመታየት ወሰንን። ኹለታች ንንም የሚያስከፋ ነበር። እሱ
በረፍት ዘሎ ወደ ቤርሲ ሲሄድ እኔ እዛዉ ክፍል ቀርቼ ለሴት
ጓደኞቼ ታሪክ አነባለኹ። እየቆየ ግን አቤል እንደሚሰማኝ
ሳዉቅ ደስ አለኝ። የሳይንስ መፅሃፉን ገልጦ የሚያነብ
ቢመስልም ቀልቡ ግን ወደ'ኛ ነበር ይኼን ደግሞ በራሴ
መንገድ አረጋገጥኩ።
ፍቅር ድብብቆሽ ሲኾን የሚጥም ነገር እንዳለዉ ማወቅ
ጀመርኩ። በቃ እስከ ጊዜዉ እንዲህ ይኹን አልኩ።
ዓይኑን ከ'ኔ ማሸሽ ሲጀምር የምኾነዉ አጣኹ። ከመቼ
ጀምሮ እንዲህ እንደኾነ አዉቃለኹ ቤርሲ ከት/ት ቤት
የቀረችበት ሰሞን ነበር...ራዕዮ ፀባዩ ሲቀያየርና ቁጡ
ሲኾንባቼዉ ጓደኞቹ የዛሬን እረፍት ሰዓት አብረሽን ኹኝ
ብለዉኝ ነበር ወደ ሜዳ ከ'ነሱ ጋ የኼድኩት። እዛዉ "እዉነት
ድፍረት" በቅጣት እየተጫወትን እያለ ራዮ እጄን እንዲስም
ተቀጣ። አርቄ አላሰብኩም ነበር እንዴትስ ጨዋታ መኃል
88
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ለዛዉም የተከፋ ጓደኛየን ላፅናና በምጥርበት ከርቀት ኾኖ
የምወደዉ ሰዉ ያየኛል ብየ ልጨነቅ?...እንዴትስ እጇን
ተሳመች ብሎ መዉደዱን እንኳ በግልፅ ያልነገራትን ሴት
ይሸሻል ልበል?... ግን ጥያቄዉ ከመሳሜ ብቻም ሳይኾን
ቀድሞም ሳሚዉን ከመጠርጠር የመነጨ ነዉ።
እሱ ይኼ ፍዝ የቤርሲን አልያ የሌላ ሴትን እጂ ሲስም
ባየዉ ተለወጠ ብየ ማድነቅ እጄምራለኹ እንጂ ጠርጥሬዉ
በቅናት ፊቴን አላዞርበትም።
ከርቀት ኾኖ እንዳየኝ እንኳ ያወቅኩት ያለወትሮዉ
ዓይኔን ታመምኩ ብሎ ት/ት ቀጥቶ ሲኼድ ነዉ።
እየፈለጉ መተዉ ለ'ሱ አዲስ ነገር አይመስልም።
በየደቂቃዉ እየዞረ መኖሬን ያረጋግጥ የነበረ ሰዉ አልይሽ ብሎ
መሸሽ ጀመረ። ፊቱ ከወትሮ በባሰ ተኮማትሮ ከሰዉ ሸሼ።
ይበልጥ ሳይንሱ ዉስጥ ተደበቀ። መኾን የሚፈልገዉ የኾነ
ዓይነት ታላቅ የሳይንስ ሰዉ ያለ አይነት ኾነ። መምህራኖቹ ጋር
እንኳ መግባባት አቃተዉ። አንዳንዶቹ መጥተዉ እንደ ተማሪ
አግዳሚ ላይ ተቀምጠዉ እሱን ቾክ አስጨብጠዉ አስተምር
ማለት ጀመሩ። ግን የሚለዉ ኹሉ ከ'ኛ ሩቅ ነበር።
ዓይኑን ከኔ ባሸሽ ቁጥር የእኔ እሱን ማለት ጨመረ...ራዮን
መዉቀስ ጀመርኩ። እሱና ቤርሲ በአዲስ ፍቅር በግቢዉ
ሲደምቁ እኔ መተከዝ ኾነ ስራዬ። ግን ደግሞ ሌላ ላሰብኩት
89
| ናትናኤል ዳኛው
ሃሜት ጆሮየ ገባ "ምዕዛር በራዮና ቤርሲ ደስተኛ አይደለችም"
ተባለ።
...ሃሜትን አልፈራም ግን የዚህ ሰዉ ዓይን መሸሽን
መታገስ አልቻልኩምና ቀጥታ ራዮን ሄጄ "እንዳጣላኸኝ
አስታርቀኝ" ብየ ምክንያቱን ኹሉ ነገርኩት።
ከሰዓት ሶስታችን ተያይዘን ወደ እሚያነብበት ላይብረሪ
ሄድን። ራዮ እኔና ቤርስን አሮጌዉ የላብራቶሪ ህንፃ ዉስጥ
እንድንጠብቀዉ ነግሮን
እሱ አቤልን ሊጠራ ወደ ላይብረሪ ሄደ።
90
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ስለ መሳምና ምዚ
አቤል ድልነህ
መሳም እንዴት ዉብ ነዉ?...የመጮል ዓይነት ህመም
አለዉ። በጣዕም ብቻ የሚገናኝ።...እና ጊዜ ሞገደኛ በሱሎ
ፈረሱ ጭኖ ያሽቀነጥረኝና "እዛ ጋ ነዉ የመጀመሪያየ መሳም"
እላለኹ። ...የመጀመሪያየ መጮልስ? እሱን ልብ ልለዉ
አልቻልኩም። ልቤ ነዉ ወይስ ቆዳዬ የመጮልን ጣዕም
የረሳብኝ?... ማንስ ነበር የመጀመሪያዉን ጥፊ ለጋ ጉንጨ ላይ
ያሳረፈ?... እግዜር?... አዳም?...ወይስ ሰይጣን?...እናቴም
ልትኾን ትችላለች... በለጋ ድዴ የጡቶቿን ወለላ እየማግኹ.
..አወራረዱ ሲንቀራረፍብኝ "ምነዉ ይኼ ዝል ጊሬራ በጉሮሮየ
ላይ ቆመሳ!?" ብየ ነክሻት...በፍቅር ያጮለችኝ።
ያች የእናቴ አዋላጅ ግንባሬ ላይ በተደፋዉ ሉጫ ፀጉሬ
ቀንታ እንደነበር አስታዉሳለኹ።...እሷ ትኾን?
መሳምን ግን አንረሳም!!
ከንፈሮቿ የጎላ እርሳስ መስለዉ ነዉ አፏ ላይ የተኳሉት።
...ኹልጊዜ እርጥበት አያጣቼዉም።
ወፍራም ከንፈሮቼ ቡሐ ያጠቃቼዉ የመሰሉ ናቸዉ።
...እሷን እያየኹ...እንደሷ ከንፈሮች ረጥበዉ ዉበታቼዉ
91
| ናትናኤል ዳኛው
እንዲጎላ በምላሴ ምራቅ እልሳቼዋለኹ። ((ይኼ በሌላዉ አይን
ሲታይ መጎምዤት ሊባል ይችላል...ዕዉነታቼን የሚገባን እኛ
ብቻ ነን ብራዳ!))
በጥቂት 'ርምጃዎች ልኬት ከኔ ርቃ ከተቀመጠችበት.
..ዐይኖቿን በከፊል ልካ ታየኝና ...ከአፏ ብርሃን ይወጣል።
"ይች ከፊቴ የተቀመጠችዉ ደቃቃ መልከመልካም እንስት
ብርሃን አርግዛለች...አሜን ለዘላለም!!" እላለኹ
በከፊል ወደ'ኔ ከላከችዉ ዐይኗ እና ከአፏ መጥና
የላከችዉን ብርሃን መለካት ያምረኛል...የብርሃን መለኪያ
ምንድን ነዉ?
ይች ሞገደኛ ፀሃይ ወደኛ የምትልከዉን ብርሃን ለክታ፡
መትራና ቆጥራ ነዉ ወይንስ እንዲኹ ከማማዉ አሽቀንጥራ
እኛ ላይ የምትደፋዉ?
ብርሃንን ያህል ሃብት ላገኙት አይነዛም።
በሰዉ ልጅና በፀሐይ መሃል የተዘረጋ የፍቅር መሰላል
አለ...በፀሃይና በሌላዉ እንስሳስ?
ይኼ በመስኮት አሻግሬ የማየዉ ወይፈን በሬ የሚበላዉ
ሳር ለመኖሩ የፀሃይ ብርሃንን አይሻምን?
92
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ያ ገመሬ በቆላፋ ጣቶቹ እየተወናጨፈ ከዛፍ ዛፍ
የሚጎንባቼዉ ቅርንጫፎች ፀሐይ ምናቸዉ ናት?
ወደ ት/ቴ ልመጣ ከቤቴ ስወጣ በጫጩቶቿ ብዛት
...መንገዴን ዘግታብኝ ታግሼ ያሳለፍኳት ((ደግሞ ሰልፋቼዉ
ከሰዉ ሰልፍ ይልቅ ያማረ)) ያች ዶሮ... እንቁላሏን ወደ መሰሏ
ለመለወጥ የተጠቀመችዉን ሙቀት ከወዴት አገኜችዉ?... እዛ
ላይስ ፀሐይ ድርሻ የላትም?
ግን በዚህ ኹሉ መኃል...ይህን ያህል ብርቱ ያልናት ፀሐይ
በደመና ትከለልና የሌለች ይመስለናል።
የልጅነት ልቤን በፈገግታዋ ብርሃን ያሞቀች እሷን
በከንፈሮቿ እርጥበት... ከንፈሬን ያወዛች... ጌሻየን... በቅንጣት
ስህተት አቄምኳት...ብርሃኗን ሽሽት ፊቴን አዙሬ ጀርባየን
አሳየኋት።
....ቂም ደመና ኾነና ብርሃኗን ከለለኝ።...ለፊቴም የሌለች
መሰለዉ።
ነርቬ ግን ጀርባየ ላይ በሚያርፈዉ ምዕዛሯ እየተቃጠለ
ነበር። ልቤ አዘዉትሮ ወደ ኋላ ያያል።...አንጎሌ ደግሞ በጠይሙ
ራዕዮ ስለተሳሙት ቀጫጭን ጣቶቿ ያወጣ ያወርዳል።
ራዕዮ የ'ሷን በሚመስሉ ከንፈሮቹ ቢያሳፍረኝ... በሃጫ
ጥርሶቼ እመጣበታለኹ። በH.P.E ክፍለ ጊዜ ለመተጣጠፍ
በሚቀለጥፉ እጅና እግሮቹ ሊያሳንሰኝ ቢዳዳ ትሪጎኖሜትሪን
93
| ናትናኤል ዳኛው
ከተራ ሀ ሁ በሚቆጥሩት የአንጎሌ ጡንቻዎቼ እመጣበታለኹ።
...ግን እንደሱ ደፋር አይደለኹም...በአንድ ጊዜ በኹለት ጓደኛ
ሴቶች ለመታማት የደረሰበት ድፍረቱ እኔ ጋ የለም።
ምላሴ ስልነት ይጎድለዋል።...ለማሰብ እንጂ ለመናገር
የፈጠንኩ አይደለኹም። ማሰብ ደግሞ ካቴና ነዉ... ምላስን...
እጅን... እግርን ይቆልፋል።...ለድርጊቴ ኹሉ ምላሹን የማስላት
አባዜ አለብኝ።...ሂሳብ እወዳለኹ።...ይችን የብርሃን እርጉዝ
ለማናገር ያልፈለግኹበት ጊዜ አልነበረም።...በአንጎሌ ከራዕዮ
የተሻሉ የማግባባትና የማዉራት ነገሮችን ባወጣና
ባወርድም...ምላሴ ግን አልሰለጥን ይለኛል።
ከፊቷ ቀርቤ ለማዉራት አደርገዉ ጥረት በምስል እንጂ
በቃላት አይገለፅም።
~
* ~
94
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የፊዚካ መምህሩ በኹለት ቁሶች መካከል ስለሚኖር
የኃይል መስተጋብር ያወራል። በኹለቱ ቁሶች መካከል ያለዉ
ርቀት ባነሰ ቁጥር የኃይሉ መጠን ይጨምራል ይላል። ጥቁር
ሰሌዳዉ ላይ በክብ መልክ ስሎ ቁ1 ቀ2 ብሎ ፃፈባቼዉ። ከቁ1
እስከ ቁ2 ደግሞ ቀጥያለ አግዳሚ አስምሮ ር አለበት።
ኃ= ከ (ቁ1×ቁ2)/ር
"በኹለቱ መካከል የሚኖረዉ ኃይል በዚህ ይሰላል" አለን።
"ከ አለምዓቀፍ አይለወጥ ናት ስንት እንደኾነች ነግራችኋለኹ"
ብሎ ቀጠለ።
በከፊል ልቦና ነዉ የምከታተለዉ። ደጋግሜ ወደ'ሷ
እዞራለኹ። ቁራጭ ወረቀት እያነበበች ሳቋ እንዳያመ ልጣት
አፏን ስታፍን አየኋት።
ፊቴን አዙሮ መምህሩ የሚያወራዉን ለመረዳት እየጣርኩ
እያለ አእምሮየ ላይ አንድ ሃሳብ ሽዉ ሲል ታወቀኝ። ጠረጴዛ
ላይ
የአስቀመጥኩትን
እስክርቢቶ
አንስቼ
መፃፍ
ጀመርኩ...ሶስት ክቦች አራርቄ ሳልኩ ና
አንደኛዋ ክብ ላይ `አ` ፤ ኹለተኛዋ ክብ ላይ `ም` ፤
ሶስተኛዋ ላይ ደግሞ `ራ` ብየ ፃፍኩባቼዉ። በመካከል ለት
መስመሮች አስምሬ `ር1` እና `ር2` ብየ ፃፍኩ።
"ኃይል" በተባለዉ ቦታ ደግሞ "ፍቅር" አልኩ
95
| ናትናኤል ዳኛው
አ
ር2
ር1
ፍ1=ከ (አ*ም)/ር1
ራ
ም
እና
ፍ2=ከ (ም×ራ)/ር2
በእኔና በ ምዚ መካከል ላለዉ አለመግባባት በመካከላችን
ያለዉ ርቀት ምክንያት እንደኾነ ማሰብ ጀመርኩ። በሴዕሌ
መሰረት እኔ ወደ እኔ ባቀረብኳት ቁጥር ከራዕዮ ትርቃለች።
ሲተረጎም "በርቀት ኾኖ ለብቻን መብሰልሰሉና ሌላን ሰዉ
መዉቀሱ ከንቱነት ነዉ።" ማለት ኾነ
መንገዱ ቀላል እንደማይኾንልኝ ገብቶኛል። በየትኛዉ
ልምዴ ጎትቼ ወደ'ኔ እንደማቅርባት አላዉቅም። ግን ደግሞ
ያስተዋልኩት አንድ ነገር አለ። ከራዕዮ ጋር እንደቀድሟቼዉ
እንዳልኾኑ። እሱ በ'ረፍት ሰዓት ከኹለት ጓደኞቹ ጋር ተያይዞ
ወደ ምዚ ጓደኛ ክላስ ይኼዳል። ከዚህ ቀደም ከምዚ ጋር ነበር
የሚኼዱት። ምዚ. እዘዉ ክላስ በሌሎች ጓደኞቿ ተከብባ
ታወራለች። በቦርሳዉ ከምትይዘዉ መፅሃፍት አዉጥታ
ታነብላቸዋለች። የትረካ ብቃቷና አንደበቷ የትኛዉንም ቀልብ
የመጎተት አቅም አለዉ። በዉበትና በፍቅር የተከበበች ናት።
አንገቴን አቀርቅሬ የት/ት መፅሃፌን የማጠና መስየ ኹሉነገሬ
ግን ከእሷ ጋር ነዉ። እያነበበች ወደ'ኔ ስትዞር በድምፇ አቅጣጫ
አዉቀዋለኹ። እየሰማኋት እንደኾነ ስለምት ጠረጥር
96
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ይመስለኛል ንባቧን ለአፍታ ቀጥ ታደርገዋለች... ስታቆመዉ
አንገቴን ከአቀረቀርኩበት ቀና ስል ዐይን ለዐይን እንጋጫለን።
ወዲያዉ ፈገግ ብላ ዐይኗን ወደጓደኞቿ መልሳ ማንበቧን
ትቀጥላለች።...ሴት ጓደኞቿ አፍ አዉጥተዉ መልከፍን
ስላልደፈሩ እንጂ የኹለታችን ግልፅ የኾነላቼዉ ይመስለኛል።
በተለይ ደግሞ የ'ኔ ከቀን ቀን ግልፅ መሟዘዝ ኾነ።
በሚቀጥለዉ ቀን ይመስለኛል እዛዉ የክላሱን በር
ተደግፌ ቆሜ ከሩቅ ሜዳ ላይ ራዕዮና ምዚ ከጓደኞቻቼዉ ጋር
ኾነዉ ሲጫወቱ አያቸዋለኹ።
"ምንድን ነዉ እንደነዚህ ከመኾን ያገደኝ?" እላለኹ ራሴን
...ጤነኛነት አልመስልህ ይለኛል...መላ አካሌ በሰንሰለት
የተረጠነፈ ያህል ኾኖ ነዉ የሚሰማኝ።
ነፃ መንፈስ ያለኝ አልመስል ይለኛል። ት/ቴን ማለት
እንዲህ አያደርግም...ሜዳዉ ላይ ከተዘሩት ቦራቂዎች ዉስጥ
ከ'ኔ የተሻሉ ተማሪዎችም አሉበት።
ይኼን እያሰብኩ እያለ ግን ድንገት ያስደነገጠኝን ነገር
አየኹ ራዕዮ የምዚን ጣቶች ሲስም... ሰዉነቴ ሲርበተበት
ይታወቀኛል። እንዲህ ስኾን ዓይኔ በጣም ቀልቶ ወጥቼ
ካልበረርኩ ይለኛል። የእኔ ዓይን መኾኑን እስክጠላ አሳክኮኝ
ያብጣል። ጠረጴዛዉ ላይ ተደፍቼ ልረጋጋ ሞከርኩ... በዉስጥ
97
| ናትናኤል ዳኛው
ከእንግዲህ አላያትም እያልኩ እምላለኹ እገዘታለኹ። በኹለት
ካራ የሚበል እምነት የለሽ አልኩት እሱን።
አንድ ከሰዓት የትምህርት ቤቱ ላይብረሪ ዉስጥ
እያነበብኩ እያለ ራዕዮ መጥቶ በጆሮየ እፈልግሃለኹ አለኝ።
መፅሃፉን እዛዉ ጠረጴዛዉ ላይ እንደተከፈተ ትቼዉ ወጣኹ።
ስወጣ በር ላይ ቆሞ አገኘኹት "መፅሃፍህን አስረከብህ?" አለኝ
"አይ" አልኩት
"በጣም እፈልግሃለኹ አስረክብ እና እዛ ና" ብሎ ወደ
አሮጌዉ የላይብራቶሪ ህንፃ ጠቁሞኝ ሄደ።
ወደ ላብራቶሪዉ ስቀርብ የሴት ሳቅ ይሰማኛል...ቤርሳቤህ
እንደምትኾን ገመትኩ። ከእሱ ጋር አብረዉ መታየት ከጀመሩ
በኋላ የቀድሟዋ ከሰዉ የምትሸሸዉ ቤርሳቤህ አይደለችም።
የመግቢያ በሩ ላይ ስቀርብ የምዚን ድምፅ ሰማኹት።
እግሮቼ ወደኋላ መመለስ ፈለጉ። በተገረበበዉ በር አጮልቄ
ለማየት ስሞክር ራዕዮና ቤርሳቤህ ተቃቅፈዉ ይደንሳሉ ምዚ
በስስት ታያቸዋለች። ሳላስብ ነክቼዉ ነዉ መሰለኝ በሩ ቃ ቃ
የሚል ድምፅ ሲያሰማ ሶስቱም ዞሩ። ደንግጨ እዛዉ
እንደቆምኩ ምዚ ተንደርድራ ወደ'ኔ ስትመጣ አየኋት። እጄን
እየሳበች አስገባችኝ። ኹለቱ ተያይዘዉ እንደቆሙ በፈገግታ
ያዩናል።
98
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ዉስጤ ተምታቶብኛል አንገቴን አቀርቅሬ ብቻ ቆምኩ።
ራዕዮ ከጎኔ መጥቶ አቀፈኝና "አቤላ ይቅርታ" አለኝ
ዞሬ አየኹት...
"ባለፈዉ የምዚን እጂ የሳምኩት የጨዋታ ቅጣት ኾኖብኝ
እንጂ አንተ እንዳሰብከዉ አይደለም" አለኝ
ቅያሜየን ማወቃቼዉ ገብቶኛል...እሷን ላለማየት ስሸሽ
መደንገጧን አስተዉያለኹ። ክፍል ዉስጥ እንዳያት
የምትቀመጥበትን ወንበር ቀያይራለች...ግን አላየኋትም።
እሱም ይኼን ስላወቀ ነዉ እንዲህ የሚለኝ። እሷን አየኋት
ትቁነጠነጣለች። ቤርሳቤህ ከጎኗ ኾና አቅፋታለች። ወዲያዉ
ትንሽ እጣቷን ሰጥታ "እንታረቅ" አለችኝ
"እሺ" ብየ እኔም ትንሽ እጣቴን ሰጠኋት
"በናትህ ከዚህ በኋላ አላይሽም እንዳትል?"
በራሴ "እሺ" አልኳት
እዛዉ ተቀምጠን ትንሽ እንደቆየን ቤርሲና ራ እንዉጣ
ብለዉን ተያይዘዉ ወጡ።
ተከትያቼዉ ስነሳ ምዚ እጄን ይዛ አስቀረችኝ። እነሱ በሩን
ከፍተዉ እንደወጡ ተነስታ ቀረበችኝ። ትንሽ ስፈራ ይታወቀኛል
ስትቀርበኝ ስሰሻት የቤቱ ግድግዳ ላይ ኼጄ ተላተምኩ። ሳቀች።
99
| ናትናኤል ዳኛው
ወዲያዉ በዓይኗ ዓይኔን ስትበረብር ቆይታ ሳላስበዉ ከንፈሯ
ከንፈሬ ላይ አረፈ። እነኾ የመጀመሪያየ መሳም እዚህ ላይ ነዉ።
... ትንሽ ሊያጠወለዉለኝ ቢሞክርም ጣዕሙ ግን ዛሬ ድረስ
ልቤ ዉስጥ አለ።
ራዮ ና ቤርሲ ከርቀት ይታዩናል። ተቃቅፈዉ ያዘግማሉ።
እኛ ከኋላ በዝምታ እንከተላለን። ደጋግማ ቀና እያለች ታየኝና
ፈገግ ትላለች።
የት/ቤቱ ትልቅ ዋርካ ስር እንደደረስን "እኛ እዚህ እንኹን"
ብላኝ ተቀመጥን። የዛፉን ግንድ ተደግፌ ከርቀት የሚሯሯጡ
ጥንድ ራዮና ቤርሲን አያለኹ። ተንጋላ ራሷን ጭኔ ላይ አድርጋ
ማዉራት ጀመረች።
"ታዉቃለህ በቤርሲ እንዲህ መኾን ደስተኛ ነኝ"
"ደስ ይላሉ" አልኳት
ትንሽ ዝም ተባባልን...እሷ ዐይኗን ጨፍና የተኛች
መሰለች። በተጋደመችበት ሙሉ አካሏን አየኋትና..
"ቅርፀ መልካም... በዉበትና በፍቅር የተከበበች... በሩቅ
እንደማልደርስበት ልቅ ተምኔት የቆጠርኳት ዛሬ እነኾ ጭኔ ላይ
አምናኝ አንቀላፍታለች!" አልኩ ለራሴ
100
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ጎንበስ ብየ ግንባሯን ስስማት ዐይኗን ገልጣ አየችኝና ፈገግ
አለች። ተረጋግቻ ፈገግ አልኩላት። ፊቷን ወደ'ኔ አዙራ በጎኗ
ገልበጥ ብላ መልሳ ዐይኗን ከደነች።
አሻግሬ ሳይ ራዮና ቤርሲ አንዳንድ እግሮቻቼዉን አጥፈዉ
የ'ሷ ግራ እጂ ከ'ሱ ቀኝ እጂ ተጠላልፈዉ ሲዘሉ አየኋቸዉ።
ኹለት ራስ...ኹለት እጂ...ኹለት እግር...አንድ ፍቅር።
101
| ናትናኤል ዳኛው
ፍዜዉ
አስቱ...አስቱካ..."ጠይም
ታወርደዋለች።
ዘለግ
ያለ..."ን
በስክነት
"ጠይም ዘለግ ያለ"ን እየተስለመለሙ የሚሰሙ...
በዐይናቸዉ ጠይም ዘለግ ያለን ፍለጋ የሚያማትሩ...ዐይነ ጎላ
ጎላ ኮረዶች...እዛ
እዚህ ደግሞ እኔ...ፍዝ...ድባቲያም...መነፅራም... ከዘመኔ
የተፋታኹ (የሚሉኝ… ያሉኝን ያመንኩ) ወጣት።
ስለራሴ የማስበዉ በእንዲህ ዐይነት አጋጣሚ ነዉ። ራሴን
በመስታዎት ሳየዉ...ጠይም ዘለግ ያልኩ...ደረቴ የሰፋ...ሶማ
መሳይ ወጣት ነኝ።...ግን ቆየኹ ይህን ኹሉ ከረሳሁት።
...የዉስጤ መንጣት...መቀንጨር...መጥበብ ሲያብከነክነኝ...
ዘመቻ የዉስጥ "ጠይም ዘለግ ያለ...ደረቱ የሰፋ"ን ፍለጋ
ጀመርኩ።
ድካም አለዉ። ህመማም ነዉ። ዉስጥ ዉጭን
እንደማሳመር አይቀልም...ወይንም እንደ ዉጭ እንዲህ ያለ
ብለዉ አያሞግሱ...አያኮስሱትም።...ይዉሰበሰባል። ሰፋ ሲሉት
እየጠበበ ጉዞዉ ወደ ራሱ ይሆናል። መታከት። ዉስጥ
በርባሮስ* ነዉ።
102
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ያለኹ ቡና ቤት ነዉ። ከአታካች የቢሮ ዉሎየ መልስ (ኦ
ቢሮ!! Too much mischief is there) እና አኹን ከነዚህ ዐይነ
ጎላ ጎላ ኮረዳዎች መሃል አንዷ መጥታም ኾነ እዛዉ ባለችበት
"ስማ...ድባቴዉ!... ብዙ ነገር ስለመሰልቸትህ እርግጠኛ
ነኝ...ግን ምን አምርረህ ትጠላለህ?" ብትለኝ
"ቢሮ ነዋ ጎላጎሊት!" ነበር የምላት።
እንዲህ ፈዛዛ የኾንኩት ፍዝ ህይወት በመጥላቴ ነዉ።
(ፍዝነት ጠልቼ ፈዛዛ የኾንኩ የመጀመሪያ ሳልኾን
እቀራለሁ!?)... የሚያነቃኝ ተጋድሎ ይመስለኛል... የድርጊትም
የሀሳብም ተጋድሎ። መኖርን የሚነግር አኗኗር ያለበት
ተጋድሎ።
በሃሳብ ብዙ በመጓዜ የምወደዉ ጊዜና ቦታ የምረሳበት
እንደኾነ ባዉቅም የድርጊት ተጋድሎ የለኝምና ምን እንደኾነ
ለይቼ አላወቅኹትም።...በሃሳብ ብቻ መራመዴ ደግሞ
ተነጣይ ፍዝ እንጅ ኗሪ አላደረገኝም።
ህይወት ምንድን ናት?...መኖር ምንድን ነዉ? ...ኖርኩ
የሚባለዉ እንዴት ቢኖር ነዉ?...ሞት ምንድን ነዉ?...ሞት እና
አለመኖርስ?
እነዚህን ለመመለስ ጣርኹ...የኖርኩት ዉሸት መሆኑ
ገባኝ።...የሌሎችንም አኗኗር ለመፈተሽ ሞከርኩ። መኖራችን
ከአለመሞት የተዋረሰሰ ሆኖ አገኘሁት።...ይኼ ኹሉ
103
| ናትናኤል ዳኛው
ያሰለቸኛል...እናም ከመሰልቸቴ ለማምለጥ የቡና ቤት ጨለማ
ስር እደበቃለኹ...አሻግሬ ደግሞ በድባቴዬ የደበቅኹት
ወጣትነቴ ርሃብ የኾኑት ዉብ ኮረዳዎች እያየኹ
እብሰለሰላለኹ።
የቡና ቤቱ ተለዋዋጭ ብርሃን እየተጥመለመለ ሄዶ
የኮረዲት ጭን ላይ እያረፈ የአሰል* እዥ የመሰለ ጭን
ያሳየኛል...ወዲያዉ
በጭኖቼ
መሃል
ቀዝቃዛ
ፍስ
ይሰማኛል...ርስሐት።
ለአስቱ እንጉርጉሮ የማይመጥኑ...የራሳቼዉን ሙዚቃ
እንደ ኩላሊታቸዉ. ..ሳንባቸዉ... ጨበሪያቸዉ... ብልታቼዉ...
ይዘዉ የሚዞሩ ለዲኣ*ዉ ሰጥተዉ ክፈትልን የሚሉ...ታናሞ
ካሻሞዎች...በዕድሚያቸዉ ልክ መሆንን የተነጠቁ ዓለም
የፈጠነችባቼዉ ፈጠኔዎች...ከሞሳ'ነት ያመለጡ...ቡና ቤቷን
መዉረር ጀምረዋል።
ይኽን ጊዜ ነፍሴን ይጨንቃት ይጀምራል..."ተነስ ዉጣ"
የሚል ደዎል... ከበርባኖሴ ይመጣል። ያለ ዕድሚያቸዉ አጥር
ኾነዉ አሻግሬ ከማየዉ ዉበት ያናጥቡኛል።
በተደጋጋሚ እየዞረ ያየኛል "ምናባቱ የመጣበትን አረቄ
አይጋትም" እላለኹ...ለራሴ።
ከተደገፈበት ባንኮኒ ማዶ ያለች ባርቴንደር* እየጎነተለች
ታዋራዋለች። የሰማት እየመሰለ ፈገግ ይልላትና ወዲያዉ
104
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ወደ'ኔ ፊቱን ያዞራል...በመነፅሬ አሻግሬ አየዋለኹ። በመሃላች
ታናሞዎች ይተራመሳሉ።
ከመቼዉ ጎኔ መጥቶ እንደተቀመጠ አላዉቅም... አረቄ
በሞላዉ ብርጭቆዉ ጠረጴዛዉን ሲመታ ዞር ስል ከጎኔ
አገኘኹት። ወደ ባንኮኒዉ ዐይኔን ስመልስ አጣኹት።
አልተረጋጋኹም...ኪሱን በርብሮ እስክርቢቶና ወረቀት አዉጥቶ
"ታዉቃለህ.." ብሎ ወሬ ሲጀምር
መልኩን ለመለየት እንኳ የዐይን ጥራት አጣሁ...።
ከኪሱ ያወጣት ወረቀት የቅጥል ቅርፅ ያላትን መሰለችኝ...
በጣቶቹ መሃል የያዛት እስክርቢቶ ደግሞ ላቫ።...ዐይኔን
በልጠጨ ለማየት ሞከርኩ...ቤቱን ለቆ የመዉጣት ፍላጎት
ሲንጠኝም ታወቀኝ...ግን መነሳት ራቀኝ።
"ታዉቃለህ...ሰዉ ከዕድሜዉ ሲሸሽ አልወድም" አለ
እይታዉ ወደ ታናሞዎች ይመስላል። "እንደዚህ ዘመናችኹ
ሞሳነታቸዉን ያላጣጣሙ ጎረምሳነትን ሲቀላዉጡ ወይንም
በስኹት ተምኔት ተመርቶ ሰማይን ሊጎርስ ሲንጠራራ
ረፍዶበት...ማምሻዉ ላይ የነቃ ሽማግሌ ተመልሼ ልወጥጥ
ሲል እበሽቃለሁ።" ...ንግግሩ እየተጎተተ...እየተንሳፈፈ በልቤ
ሲያልፍ ይታወቀኛል።
ቅጠል መሳይ ወረቀቱን ጠረጴዛዉ ላይ አስተኝቶ
እንደሚፅፍ ሰዉ ላቫ ብዕሩ ጣቱ ዉስጥ እያመቻቼ
105
| ናትናኤል ዳኛው
"...አየህ ንቃት ይጠይቃል። ዕድሜየን ማወቅ በዕድሜ
የሚከዉኑትን መጠንቀቅ ጠንካራ አንጎልና ተራማጅ ልብ
ይጠይቃል።"
"ጨቅላት ለጨቅላ ብቻ ነዉ።. ..ለኹሉም ጊዜ አለዉና
ጉርምስናም ለጎረምሳ ብቻ።
አንዳንድ ጊዜ አንዳንዱ ከወጣትነት ተስፈንጥሮ ልቡ
ሲሸመግል ታስተዉላለህ...እንደ አንተ።"
...እንዴት እንደኾነ ባይገባኝም...የማላዉቀዉ ብሶት
እየተጫነኝ መጣ...ስሜቴ ለማልቀስ ሲናጥ ተሰማኝ።
"...ደግ ነገር ነዉ ሊባል ይችላል። እኔ ግን የእንዲህ አይነት
ሰዉ ቁጣ ያስፈራኛል።. ..ዓለም ላይ እንዲህ አይነት ሰዉ
ሲቆጣባት ሲኦልነቷ ይጎላል።"
ይኼን ስሜቴን አላውቀዉም...ወይንም እንዲህ እንድኾን
አልፈቀድኩም...ግን ከፍቃዴና ከዕዉቅናየ ዉጭ እንባየ
እየፈሰሰ እንደኾነ ያወቅኹት ጉንጨ በጋለ ፈሳሽ ሲለመጠጥ
ነዉ።
አቀርቅሮ በላቫ መሳይ ብዕሩ የኾነ ነገር ይጭራል። ግራ
በገባዉ አኳሃን እስኪጨርስ እጠባበቀዋለኹ
106
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"እይ የዕድሜ ጉዞ እንደዚህ ነዉ።" ቅጠል ወረቀቷን ወደ
ፊቴ እያቀረበ
ሞት
ህይወት
እጄ መልካሙ ልብስ ሰፊ...የሚያዛጋ
ልደት
መቀሱን በጣቶቹ መሃል ሰክቶ በኹለት
ጨርቆች መሃል ቆሟል። ኹለቱም ላይ
ዉበት አየ። በተቃራኒ ቀለሞች የተዋቡ
ናቸዉ።...ከኹለቱም ኹለት ቅዶችን ወስዶ
አንድ አዲስ ልብስ ሰፋ...ሰዉነት የሚባል።
"ኹልጊዜም በዕድሜ ከፍ ባልክ ቁጥር ከአእምሮና
ከልብህም ከፍ ማለትህን ማረጋገጥ አለብህ።" የምትል ግርጌ
አክሎባት በእጄ እንድይዛት ሰጠኝ።
ያስጨበጠኝን አስተዉየ ቀና ስል ከጎኔ አጣኹት። ትንሽ
ዘወር ስል ከበር ሲወጣ ጥላዉ ታየኝ። ጥላዉ የእኔ ይመስላል::
107
| ናትናኤል ዳኛው
108
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ጠይም ድልድይ
ጤነኛ እንዳልሆንኩ አስባለኹ። ሁሉንም ነገር አምርሬ
የምጠላበት
ደረጃ
ላይ
እንዴት
እንደደረስኹ
ባላዉቀዉም...የመሆን ማማዉ ላይ ነኝ...አዎ ምንም
የሚያሰኘኝ...ምንም የምወደዉ ነገር የለም...ሞትም ቢሆን
እንኳ። ያለጊዜየ የሞትኹ ያህል ነዉ የሚሰማኝ... ማን ነዉ
የገደለኝ?... ህልሜን የቀማ ገደለኝ። ከዚህ በፊት ሰዉ
የሚሞተዉ በሚወደዉ ነዉ ሲባል ሰምቼ ከእቁብ
አልቆጠርኹትም ነበር...አሁን ግን እነሆኝ የሞትኹ እኔ። ወፈፌ
ነዉ ብለዉ ባያዉጁም "ትንሽ ነካ ያደርገዋል መሰለኝ!" ግን
ይላሉ። አጥብቀዉ እና ለይተዉ የወደዱት የላቸዉምና እንደ'ኔ
አልገደላቸዉም።
ተስፋ መቁረጥ የዕለት ምግባችን ሆኗል...የእኔና የትዉልዴ
ምልክት በሽንፈት ያንቀላፋ አንበሳ ነዉ።
የአስፋልቱን ጠርዝ ይዤ እየተራመድኩ ነበር፡፡ ብዙ
ዘባተሎ ሃሳብ በዉስጥ እያንገላታኛ ቢሆንም ያዉ
የተለመደዉን በወፈፌነት መጠርጠር ፍራቻ አፌ
እንዳይንቀሳቀስ ከንፈሮቼን ጠበቅ፣ ጥርሴን ነከስ
አድርጊያለኹ። አስፋልቱ የተኛ ጥቁር እባብ አንዳንድ ጊዜ
ደግሞ ከርቀት የተኛ ዉሃ እየመሰለ ይታየኛል። ሃሳቦቼን ደርዝ
109
| ናትናኤል ዳኛው
ለማሲያዝ እየታገልኩ ቢሆንም በጎኔ የሚያልፈዉ መኪናና ሰዉ
ለዐይኔ እንደ ህልም እንደ ዉልብታ ይታየኛል። የኾነ ዓይነት
መንሳፈፍ ዉስጥ ያለኹ ነዉ የሚመስለኝ፡ የምረግጠዉ
አስፋልቱ ለእግሬ ይርቀዋል። አፉ ሞጥሙጦ የወጣዉ ጫማየ
እንደ ዝልግልግ ዘርጋ ኮምተር የሚል ዓይነት ይኾናል ለዓይኔ።
ሃሳቤ አእምሮየ ዉስጥ ዉቅያኖሴ ሆኖ ተዘርግቶ ሲዉጠኝ፡
ስፖንጅ ሆኖ መላ አካሌን ከታች ጀምሮ ምጥጥጥ እያደረገ
ሲምገዉ ይታወቀኛል።
የስንት ሰዉ ትከሻ እየገጨኝ እንዳለፈ ያወቅኹት በድንገቴ
የመኪና ትላክስ ጩኸት ነቅቸ ወደ እዉነቱ ስመለስ በተሰማኝ
የቀኝ ትከሻየ ህመም ነዉ። መላ አካሌ ዝሎ ነበር፡ርቄ ተጉዤ
ከሰላሙ ሰፈሬ ወጥቼ የህዝብ ትርምስ ወዳለበት መሃል ከተማ
ደርሻለኹ። የፀሃዩኣን ግባት ታክኬ ነበር ከቤቴ ጉዞ የጀመርኩት
እዚህ ትርምስ ስደርስ ግን ጨለምለም ብሎ የከተማዋ
መብራት ተንቦግቡጎ፡ የሆቴሎች እና ግሮሰሪዎች ደብዛዛ
ብርሃን ከርቀት የሚጣራ ዓይነት ሆኖ ተለኩሶ ነዉ። የባሚስ*
መዓት ከተማዋን ይንጣታል። የመሸበት ወይም መሸብኝ ብሎ
ያሰበን አዝለዉ ይራወጣሉ። ከነዚህ ባሚሶች አንዱ ነዉ
እጥፋት መንገድ ላይ ሲደርስ እኔ ተራምጀ ወደ መሻገሪያዋ
ስገባ በጥሩንባ ጩኸቱ ያባነነኝ።
"ኼይ ነካ ያረግኻል ልበል?" የባሚሷ ዘዋሪ አንባረቀብኝ፡
ነካ ያረግኻል ሲለኝ የሚያዉቀኝ እኔን ወፈፌ ብሎ ለመሳደብ
ተፈጥሮ ኹነት ያመቻቸችለት ወጠጤ መሆኑን ለመለየት የቀላ
110
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ዓይኔን ወደ ድምፁ አቅጣጫ ላኩ። የማዉቀዉ ፊት
አልታየኝም፡ ምንአልባት እሱ ያዉቀኝ ይሆናል...ወፈፌ
አይደለኹ...ነዉ ባይሉ ነክ ያረገኝ የለ!?።
ፈጠን ብየ አለፍኩለት እሱም ሰዎቹን አዝሎ ሽቅብ
ተሻግሮ ሄደ።
አንዳንድ ወቅት አለ ለሳምንታት ከታፈንኩበት እንድወጣ
የሚያደርገኝ የምሽት ናፍቆት...ልክ እንዳኹኑ ከምጠላዉ
የከተማ መሃል አምጥቶ የሚጥለኝ... የግሮሰሪዎችን ደብዛዛ
ብርሃን
የሚያስናፍቀኝ...የሴቶችን
የተጋለጥ
ጭን
የሚያስመኘኝ።
ስካር የምወደዉ ስሜት ባይሆንም ጠንከር ያለ አልኮል
ግን እወዳለኹ። አእምሮየን ጨምዶ ከሚዝ ጠንካራ ሃሳብ
የምላቀቀዉ ወደ አፌ አንድ ስኒ አረቄ ልኬ ነዉ። ምግብ በልቼ
አፌን
የምጉመጠመጠዉ
በወይን
ነዉ።...ግን
አልሰክርም...በአልኮል ማለቴ ነዉ። እንጅ የሃሳቡማ ግዞቱ ነኝ።
ነፃ መዉጣት እስኪያቅተኝ ይዞኛል። አስባለኹ እሰክራለኹ
እሰበራለኹ። ሁልጊዜም ያዉ ነኝ...ታዲያ ምን አተረፍኹ? ተስፋ
ማጣት።
ስለሀገሬ ሳስብ እደክማለኹ...ስለትዉልዴ ሳስብ
ይጨንቀኛል...ስለአሁን ሳስብ እሞታለኹ....ስለነገ ደግሞ
እፈራለኹ።...እኔ እንደ ገብርዬ* "ሀገሬ ገነት ነዉ።" ብየ
111
| ናትናኤል ዳኛው
መግጠም አልችልም።...ሀገሬ የገነት ቁራጭ ብትኾንም ዜጎቿ
የሲኦል ቀሳዉስት ኾነናል።...እንዲ ሲሰማኝ እፀልለኹ
አእምሮ ሳይፈራ ራስ ቀና ወደሚልበት
እዉቀት ነፃ ወደሆነበት
ዓለም በጠባብ የከባቢ ግድግዳዎች ወደ ቁርጥራጮች
ወዳልተለወጠችበት
ቃላት ከጥልቁ ሀቅ ወደሚፈልቅበት
እዉነተኛ መሻት ክንዶቹን ወደ ፍፁምነት ወደሚዘረጋበት
ንፁህ የአመክንዮ ምንጭ መንገዱን ወደ የሟች ልምድ
ንጡፍ በርሃ ወዳልሳተበት
አእምሮ ወደተሻለ ሃሳብና ልምድ ወደሚተጋበት
አባት ሆይ ወደዛ የነፃነት ገነት ሀገሬን አንቃት።*(ጊታንጃሊ
1913፤?)
ትንሽ እንደተራመድኹ ከመስቀለኛዉ መንገድ ወዲህ
ያለች አንዲት የመብራት ፖል አየኹና ወደሷዉ አመራኹ።
እሷኑ ተደግፌ ዙሪያየን ለማስተዋል ሞከርኩ። ወጣቶች ታዩኝ።
112
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የባሚስ ዉርዉር አለ። የመንገዱን ጠርዝ ይዘዉ የተሰለፉ
ረዣዥም የጭነት መኪኖች...በመኪኖቹ ዙሪያ የእጅ ባትሪ እና
ከዘራ የያዙ ጋወን ለባሾች... የመኪኖቹን ጎማ ታክኮ ብልቱን
የመዠረጠ ጀብራሬ ወጣት።
የተጣደፈ ዓይነት ነዉ...ቁመዉ የሚሄዱ ነፍሳት መከተቻ
ፍለጋ ይራወጣሉ። መንገዴን ወደ ማዉቀዉ ግሮሰሪ
አደረግኹ...ቀለል ያለ የማይረብሽ ቤት ነዉ። ደብዛዛ
ብርቱካናማ ብርሃን የሚዘንብበት...ለስ ያለ ሙዚቃዉ
የሚያባብል ቤት። የአስተናጋጆቹ ስክነት ከቤተ መቅደስነት
የሚያስተካክለዉ ግሮሰሪ።
ለእኔ
ጥርሳቸዉን
የሚገልጡ
ሰዎችን
ካየኹ
ከርሚያለኹ...እዚህ ቤት ግን ይች አስተናጋጂ(ደግሞ
በመጣኹባቸዉ ጊዚያት ኹሉ እሷ ብቻ ነች ያስተናገጀችኝ)
ከንፈሮቿ ተበልጥጠዉ ነዉ የምትቀበለኝ። ደብዛዛዉን ብርሃን
ታክኬ አካሏን አስሳለኹ...ሞንዳላ ናት። የሞላ ሰዉነት
አላት...ጠይም ናት።
ጠይምነት ድልድይ ይመስለኛል። በነጭና በጥቁር መኀል
የተዘረጋ...በ'ኔና በዓለም መሃል የተዘነጠፈ።
ጥርሷን ፈልቀቅ አድርጋልኝ ምን ልታዘዝ ብላኝ
እስክመልስላት አትጠብቅም ሄዳ የለመድኩትን...አንድ ኹለቴ
ካዘዝኳት በኋላ ምርጫየ ያ ብቻ መስሏት እሷ ያስለመደችኝን
ይዛ ትመጣና ጥርሷን ብልጭ አድርጋልኝ ትሄዳለች።
113
| ናትናኤል ዳኛው
ባይተዋርነቴ ጎልቶ ይታወቃል... ብቸኜነት መጎናፀ ፊያየ።
የምቀወመጠዉ ሰዉ የማይበዛባት ጨለምላማ ቦታ ነዉ። ይች
ጠይም ግን ድልድይ ልኹን ባይ ትመስላለች... ወደ ተዉኩት
ዓለም መላሽ። ላወራት ፈልጌ የተዉኩበት ጊዜ
ይበዛል...በፀጥታ ሂሳቤን ከፍየ ስወጣ በቀስታ "ደህና እደር"
ብቻ ትለኛለች።
ስገባ ቦታየ ላይ ሌላ ሰዉ ተቀምጦባት አየኹ። ወዲያዉ
ዘወር ብየ ልወጣ ስል ከክንዴ ላይ እጂ ሲያርፍ ታወቀኝ። ዞሬ
ሳይ ጠይሟ ናት...ጥርሷን ብልጭ አድርጋ እየጎተተች
በግሮሰሪዋ የኋላ በር በኩል ይዛኝ ሄደች።
ጥራት ያላት ክፍል ናት። ጥንቁቅ ሰዉ እንደሚኖርባት አፍ
አዉጥታ ትናገራለች። ነጭ መብራት እንደማልወድ የራሷን
ግምት ወስዳለች መሰለኝ አምፖሉን አጥፍታ ሻማ ለኮሰች።
የምታደርገዉን ኹሉ በድንዛዜ አያለኹ...መደንገጤ
ታዉቋታል...ታዉቆኛል። እሷ ትልቅ እንግዳ እንደመጣበት ሰዉ
ከክፍሏ ግሮሰሪ ትሯሯጣለች። የክፍሏ ድባብ ሲቀየር
ይታወቀኛል። ዐይኔ ያስሳል...ከተቀመጥኩበት ወንበር ጀርባ
ድንክ መደርደሪያ ላይ ጥቂት የማይባሉ መፅሃፍት ዐይቼ
ቀልቤን አሳረፈልኝ መሰለኝ ራሴን ዘና አድርጌ አንዱን ሳብኩት።
እሷና አንዲት ሌላ ሴት እንጀራና ወጥ ይዘዉ ወደ ክፍሏ ገቡ።
ከሰሃኗ የሚወጣዉ የወጥ መዓዛ 'ርቦኝ እንደነበረ
አስታወሰኝና ኾዴ መጮህ ጀመረ። መፅሃፏን ቅርቤ ከነበረዉ
114
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
አልጋ ጫፍ ላይ አስቀምጨ ለመብላት ስዘጋጂ አብራት
የመጣችዉ ሴት ወጥታ ሄደች። ጠይሟ ዉሃ አቅርባ ታጠብ
አለችኝ...አላመነታኹም...እንደነገሩ እጄን ተላቃለቅኩ። እሷም
ታጥባ ከአልጋዋ ስር ትንሽየ የፕላስቲክ ወንበር ስባ
ተቀመጥቸ። እየበላን አላወራንም ደጋግማ ግን ታጎርሰኛለች።
ዐይኗ ላይ ረቂቅ ደስታ አያለኹ። ምግቡ ጣፋጭ ነዉ...። ከበላን
በኋላ ስልኳን አዉጥታ ቁጥር ነካክታ ደወለችና አንድ ጊዜ
እንደጠራ መልሳ ዘጋችዉ። ወዲያዉ ምግቡን አብራት
ያመጣችዉ ሴት ነጭ ወይንና ኹለት ብርጭቆ ይዛ መጣች።
"አመሰግናለኹ" አልኳት፤ ደብዛዛ ፈገግታዋን አሳየችኝ
ዐይኗ ላይ ረቂቅ ፍቅር አየኹ። ደስ ሲለኝ ታዉቆኛል።
ሴቷ ወይኑንና ብርጭቆዉን አስቀምጣ የበላንበትን ሰሃን
ይዛ በዐይኗ ጠቅሳት ወጣች።
~
* ~
ረፋድ ከእንቅልፌ ስነሳ...ራሴን ቤቴ አገኘኹት። ብዙ ነገሩ
ግን ተለወጠብኝ...ከርቀት እየሳቀች ስልክ የምታወራ ሴት
እሰማለኹ። በየቦታዉ አዝረክርኬ የተዉኳቸዉ እቃዎች
የሉም። መስታዉቱን አልፎ ወለሉ ላይ የተዘረጋዉ የፀሃይ
ጨረር ያጥበረብራል። የሳሎኑ መሃል ላይ የሚያምር ረከቦት
በቡና ስኒዎች(ፍንጃል) ተሞልቶ ተቀምጧል። ሳሎኑ ዙሪያዉን
በሳር ጨፌ ተሸፍኗል።
115
| ናትናኤል ዳኛው
የሚሰማኝን ዉብ ተቅጨልጫይ ድምፅ ተከትየ ስሄድ
በረንዳ ላይ ጠይሟን አገኘኋት። ኹሉም ነገር ትዝ ይለኝ
ጀመር። ከወይኑ በኋላ የኾነዉ ኹሉ።
ያለገደብ ያሳየኋት ገመናየ ኹሉ፡ካይኗ ይፈስ የነበረዉ
እንባ ኹሉ እንደ ተዓምር ትዝ ለኝ ጀመር።
ጥቂት ከኋላዋ ኾኜ ካየኋት በኋላ የተጫነኝ የመሰለኝን
ስሜት ለመለቃለቅ ተመልሼ ከዚህ በፊት ወደ ረሳኹት ሻወር
ቤት አመራኹ።
ይረብሸኝ ነበር...የሻወሩ ድምፅ...ከፀጥታ የተጋባኹ
ነበርኩና። ያ ስሜቴ ወዴት ሄደ?... ይኼ ነዉ የማልለዉም እንደ
ተዓምር ያለ ነገር ግን ዉስጤ እንደተከወነ ገባኝ።
ዛሬ እንደትናንት አለመኾኑ ገብቶኛል...። ትናንትን
የሚመስል ዛሬ እንዳልመጣ ቀን ቁጠረዉ ይለኛል እንግዳ ልቤ...
ብዙ ያልኖርኳቸዉ ዛሬዎች ማለፋቸዉ እንደ እንግዳ ዕዉቀት
ይገለፅልኝ ጀመር።
ከሻወር ቤት ስወጣ...መዓዛዉ የሚጎትት ምስላል* ወጥ
ሸተተኝ።
ምስላል ጠይም ወጥ ነዉ። በእኔና እናቴ መሃል ያለ።
ልጅነቴ በእናቴ ና በምስላል ወጥ መዓዛ የታጀበ ነዉ።
ከዘነጋኹት ግን ቆይቼ ነበር...የረሳኹት መሰለኝ እንጂ ተደብቆ
ነበር። ዛሬ ከቤቴ ኾኖ ጠራኝ...ጠይሟ ደግሞ ትሪ ላይ እንጀራ
116
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
እየዘረጋች አየኋት። ኹሉም ነገር ከ'ሷ መኾኑን አዉቃለኹ...
እዚህ ቤት ሳሎን ላይ እንደሚኾነዉ ነዉ ዉስጤ እየኾነ ያለዉ።
ሳሎኑ ላይ የማያት ሴት ልቤ ላይም እንዲኹ እንደኾነች
ይገባኛል። እዚህ ሳሎኑ ላይ የማየዉ ኹሉ ልቤ ላይ እያደረገችዉ
ያለዉ እንደኾነ አዉቃለኹ።
እንጀራዉን በትሪ አድርጋ ጠረጴዛዉ ላይ አስቀምጣ ቀና
ስትል አየችኝና...ጥርሷን በደማቁ ፈለቀቅችዉ... ለመጀመሪያ
ጊዜ ፈገግታዋን በፈገግታ መለስኩላት። ጉንጨን ስማ እጀን
ይዛ ወደ ምግቡ ጠረጴዛ ወሰደችኝ። በደስታ ተከተልኳት።
...ማን ነበር "መኖር ቀስ እያሉ መወለድ ነዉ።"* ያለዉ።
117
| ናትናኤል ዳኛው
ቅፅበቴ
ጀርባየን በሚጠዘጥዘኝ የዕኩለ ቀን ፀሃይ ጨረር
እየተማረርኩ ማረፊያ ጥላ ፍለጋ እራመዳለሁ።...ፊት ለፊቴ
ያገኘሁትን ሁሉ በእግሬ እየለጋሁ ግለቱን ለመርሳት
እየሞከርኩ።
...ከፊቴ የነበረችን ጠጠር በግራ እግሬ ስጠልዛት...
ከአስፋልቱ ግራ ጠርዝ ላይ ቆማ የነበረች ቶዮታ መኪና ጎማ ስር
ሄዳ ተወሸቀች። እንዲህ እያልኩ
ቤቴ ደርሼ በምን ያህል ፍጥነት ልብሴን አወላልቄ ወደ
ሻወር እንደገባሁ የማዉቀዉ ነገር የለም።
አመሻሹ ላይ በእንቅልፍ ብዛት የዛለ ገላየን ላፍታታ
በቀስታ እየተራመድኩ ነበር።...ዘወር እያልኩ ለመጥለቅ
የምታዘግመዉን ፀሃይ ዉበት አደንቃለሁ...ደማቅ ሃምራዊ
ሆናለች።
በቅርብ 'ርቀት ሰዎች ሲሯሯጡ ይታየኛል።...በዛ ያሉ
ወጣቶች ደግሞ የሆነ ነገር ከበዉ ቆመዋል።...ነጠላ ዘቅዝቀዉ
የለበሱ ሴቶች እኔን እያለፉ ይጣደፋሉ። ወደ ቦታዉ ስቀርብ
የብዙ ሰዎች የለቅሶ ድምፅ ይቀርበኛል።
118
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ትንሽ ፍጥነት ጨምሬ ተራምጄ ወጣቶቹ ወደቆሙበት
ሄጄ እየሆነ ያለዉን ለማወቅ ሞከርኩ።...ዝብርቅርቅ ያለ ነገር
አለዉ።
ወጣቶቹ እኩለቀን ላይ ሳልፍ ቆማ ያየኋትን መኪና ነዉ
ከበዉ የቆሙት። ሁለት ወጣቶች የመኪናዋን ግራና ቀኝ በር
ለመክፈት ይታገላሉ።...ከዉስጥ በድንጋጤ መሪዉ ላይ የተደፋ
ፈርጣማ ወጣት ይታየኛል።
ድንኳን ወደተከለበት ዙሬ ሳይ አምስት ዓመት
የማይሞላዉ ህፃን ፎቶ ከፍ አድርጋ ይዛ የምትርገበገብ ሴት
በሰወች ተከብባ አየሁ።
የመኪናዋን ጎማና ያረፈችበትን ቦታ ዝቅ ብየ አይቼ
ምንም ዓይነት የደም ጠብታ አልታይ ሲለኝ...ዳር ላይ ሆኖ
በተደጋጋሚ 'ምፅ' ሲል ወደ ሰማሁት ወጣት ተጠግቼ
"ምን ኾነዉ ነዉ?" አልኩት ቃላቱን ግራ በገባዉ ፊት
አጅቤ
አዘቅዝቆ በአዘነ ፊት ካየኝ በኋላ ትንሽ እኔ ወደ አለኹበት
ቀርቦ
"ምን ባክህ...የገጠመኝ ነገር!.. ምፅ!...እሱ ተልኮ
ሲወጣ(ድንኳኑ ዉስጥ ሴቷ ከፍ አድርጋ ወደያዘችዉ የልጅ ፎቶ
አፉን
አሞጥሙጦ
እየጠቆመኝ
)..ይች
መኪና
ስትንቀሳቀስ(ዓይኑን ወደ መኪናዋ መልሶ)... ምፅ!.. አይይ!...
119
| ናትናኤል ዳኛው
ከጎማዋ የተፈናጠረ ጠጠር ነዉ አሉ...ሄዶ ይችን ሰረሰሩን ብሎ
ፀጥ አደረገዉ አሉ።...ሰዉ ከንቱ!!...ምፅ!" አለኝ
እያላበኝ ነበር...እንዲህ የሚያጥወለዉል መስፍ ልቤ ላይ
የሰካዉ ማን ነዉ?
120
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ሳሊል
"ወፍ ዘራሽ!!" ብላ ሰደበችኝ. ..በኔዉ ቁጥብነት ዘር
ማንዘሬን ታካኪ ባለመሆኔ...ሽማት ምንጅላቴን ቆጥሬ
ባለመናገሬ እንደሆነ እንዲህ ያለችኝ ገብቶኛል።...ምናልባት
የደበቅኋት(ኋቸዉ)... ስለመሰላት(ላቸዉ)... በብሶት አፅም
ልታስቆጥረኝ ይሆናል!?
....አደባባይ ወጥቼ...አልያ ትንሽ የቡና አደባባይ ቤቴ
ዘርግቼ...እኔ ሳሊል ሙሃመድ...መልኬ ፀሃይ...በአባቴ የወሎ
ክርስቲያን...በእናቴ የሸዋ ሙስሊም...በሁለት ታላላቅ
ሃይማኖቶች
መሃል
ተፈጥሬ...ሀይማኖት
ግድ
የማይለኝ...በተሰናሰለ የዘር ሃረግ የከበበኝን ጋሻ ያላረግኹ...
ብቻየን የቆምኩ ግን በሀገሬ ወፍ ዘራሽ ተባልኩ...ብየ እርር
እንድል።...አሰብኩት ከዐይኖቼ እየወረደ የሚፈርጠዉን የእንባ
መለልታ።
አዉቃለሁ ግድ የለሽ ነኝ...ግን ሰዉ አክባሪ
አይደለሁምን?...ጥፋት ታክኬ እጣላለሁን?...አፌን ቀላል
ስድብ እንኳ አላለማመድኩትም። ተክል ስሩ ከረዘመ ዉሃ
አጥሮታል ማለት ነዉ። ህልዉናዉን ለማቆየት ርቆ ይጓዛል።
121
| ናትናኤል ዳኛው
ከስምህ ቀጥሎ ዘር ማንዝርህን የመጥራት አባዜ ካለብህ
በ'ራስ' የሚያቆም ነገር ጎድሎኃል ማለት ነዉ።...እኔ ኩሩ
ነኝ...እግዜር ከሰጠኝ የጀርባ አጥንት ሌላ መቆሚያ ያላሻሁ።
በኹለት የእንቁላል ቅርፊቶች መሃል ያለን....ትንፋሽ
ተለዋዉጠን የምንኖር ፍጡራን አይደለንምን?....መኖሬ
ያጎደለዉ ሰዉ የለ!...ግን ነገር ይመርብኛል!!...ጥፋት
ይገንብኛል...ልፋቴ ይደበቅብኛል።
ይች ያለአባት ያሳደኳት ሶለል ልጄ እንኳ የሆንኩላት በዝቶ
ያጎደልኩባት ቢጠፋት "እስቲ ምን አድርገሽልኛል?" ብላ
ትጠይቀኛለች።
በርግጥ እሷን ማሳደግ ከብዶኝ አልከሳሁ አልጠቆርኩ
ይሆናል ግን ያለወግ ያለደንብ አራት ዓመታት አጥብቻታለሁ...
በወጣትነቷ እንደወለደች የጡቴ መላላት ሳያሳስበኝ።
...የአራስነት ጨርቋ ይመስክር በአፌ አልሳምኩት...በአፍንጫዬ
አልማግኹት እንደሆን። ግን ፍቅር ቁልቁል እንደሚሄድ
እረዳለኹ። ከልጅ ወላጅ ያፈቅራል።
ዉብነቴን፣ ሚስትነቴን የናፈቁ... ወልጄ እንኳ ልመናቸዉ
አላባራም ነበር...እኔስ አቃፊ ትከሻ ከመናፈቅ ነጥፌ ነበርን?
122
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
...ግን በልጄ ለስላሳ ገላ ቀይሬ...የከረረ ከንፈሬን በለጋ
ከንፈሯ መሳም እያወዛሁ...ሆነ ብዬ ከፍትወት ለመራቅ አልጫ
ብቻ እየተመገብሁ ነበር ያሳደግኋት።
አባቴ ሳሊል ሲለኝ በከንቱ አልነበረም...የፊቴን ብርሃን
መሳይ ጸዳል አይቶ እንጅ...ያ ዉበት በቆዳ መሸብሸብ ሲተካ
እኔዉ ቋሚ ምስክር ነበርኩ...ቢሮ ስገባና ስወጣ እየጠበቁ
የቂጤን
እንቅስቃሴ
ይመለከቱ
የነበሩ...ዐይናቸዉን
ወደአለማየት ሲያሸሹ ህያዉ ምስክር ሆኜ አይቻለሁ። ግን
ልጅት የዋዛ አይደለሁም... በከፈልኩት መስዋዕትነት መዋጥን፣
መሰልቀጥን አልፈቅድምና በዕድሜዬ እንደ ዕድሜዬ ማወቁን
ተካንሁበት። በዚህ በጉልምስና(?) ዘመኔ እንኳ ስለአለባበሴና
አልባሳቶቼ ጥራት ተገባብዘዉ የሚመ ለከቱኝ ብዙ ናቸዉ።
ልጄን ወደ ዩንቨርስቲዋ ሸኝቼ ወደ ቢሮዬ አመራሁ።...ስገባ
ከወትሮ ዘግይቼ እንደነበር የታወቀኝ ለወትሮዉ እኔ ከገባሁ
በኋላ ስልክ ተደዉሎላቸዉ የሚገቡ ሰራተኞች እንኳ ገብተዉ
ሳገኝ ነዉ።...ግን አንዳቸዉም እንኳ ስራ አልጀመሩም
ነበር...ሁለት ሶስት ሆነዉ ያወራሉ።እነዚህ ሴቶች የሚረጩት
ፌርሞን* አላቸዉ። እንደ ንብ የወንድ ሰራዊት በዙሪያቸዉ
ለመሰብሰብ። ዉበታቸዉን የሚለኩት በከበባቸዉ የወንድ
ብዛት ነዉ።
እንደገባሁ አለቃዬ ከፀሃፊዉ ጋር ቆሞ እያወራ ነበርና
እንዳየኝ ባለበት "ሳሊል እንዴት አደርሽ. ..ቢሮ እፈልግሻለሁ."
123
| ናትናኤል ዳኛው
አለኝ...ጮክ ብሎ ነዉ ደግሞ...ሴቶቹ በዐይኖቻቸዉ
ሲጠቋቆሙ አስተዋልኩ...እንዳረፈደች ሰራተኛ ለምን ቆጣ
ብሎ
አልተናገራትም
ይመስለኛል
ምክንያታቸዉ።
...የጠረጴዛዬን መሳቢያ ስቤ ቦርሳዬን አስቀምጨ ወደ ኃላፊዉ
ቢሮ ስሄድ "ወፍ ዘራሽ..." የሚል ስሌት የወጣለት ቃል ከኋላየ
ተወርዉሮ ጆሮየ ዉስጥ ገባ።...የተላከዉ ወደ እኔ እንደሆነ
ከላኪዋ አዉቃለሁ ግን ግድ የለኝምና...ቀጥ ብየ (ባልሰማ ነዉ
የሚባለዉ?)...ቀጥ ብየ ወደ ኃላፊየ ቢሮ አመራሁ። አንዲት
የጽጌሬዳ እንቡጥ ከሌላ የጽጌሬዳ እንቡጥ ጋር ፉክክር ዉስጥ
ገብታ አላየኹም...ተፈጥሮና ጊዜዋን ጠብቃ ስታብብ እንጂ።
...እነዚህ በአበባነት ያሉ ሴቶች በጊዜየ ፍሬ ካየኹ ታላቅ
እህታቼዉ ከምኾን ሴት ጋር ራሳቼዉን እያፎካከሩ ለመርገፍ
ሲፈጥኑ ማየት ያሳቅቀኛል።
ፀሃፊዋ ከኃላፊዉ ጋር ባላት ቅርበት በነዛዉ ሴቶች
እንደምትጠላ አዉቃለሁ...ቢያንስ ለስድቤ ምላሽ የሚሆነዉ
እዝች ሴት ጋር የሚደረግ ሞቅ ያለ መሳሳም መሆኑን አዉቄ
ያለወትሮ በደማቁ ሳምኳት...ቆም ብየ አወራኋት...ፊቷ ላይ
ግርታ ባይባትም የገባት መስሎኛል።
ቢሮ ስገባ ሰዉየዉ(ሰዉየዉ ልበል እንጂ) ለጠጥ ብሎ
ወንበሩ (አልጋዉ ብል ይቀላል) ላይ አገኘኹት። ዉጭ ላይ
ከሴቶች መሃል ስለሚያሳየኝ አክብሮት ቢሮዉ ዉስጥ ብቻየን
ጠርቶ እንድክሰዉ የሚፈልግ አይነት ሆኖ ይጠብቀኛል። ልጅት
ይገባኛል(ምናልባት ሴትነትም ያደለኝ ይሆናል)፡ ዉለታ
124
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
እንደተዋለላት ሳይሆን የሚገባትን እንዳገኘች ቁልቁል በሙሉ
አይኔ አየዋለኹ። ይርበተበታል በዐይኖ ወዲያዉ ራሱን
ሊያረጋጋ (ዐይኑን ከዐይኔ ሊያሸሽ) ቆሞ እጁን በኪሱ ከቶ
ሊንጎማለል ይሞክራል...ወደሜዳዉ አምጥቶኛልና ንጉሱ እሱ
ነዉ። ቢንጎማለል አይደንቀኝም ደልዳላ ሰዉነቱ ያኳራል
(በሚስቱ የቀናኹባቸዉ ቀናት የሉምና ይህን ልካድ?)። ወንድ
ልጅ ትከሻዉ ካልሰፋ ጠባብ ኪስ ማለት ነዉ...ፍቅር ያፈሳል።
ማሜ ይሙት!!
በቁመቱ ሊለካኝ ይሞክራል፡ ግን የኛስ መች አንሶ!! ከጎኔ
ቢቆምም ሊጠጋኝ አይችልም... ዳሌየ በሴ.ሜ ያርቀዋል። አፍሮ
ይመለሳል።
እንዲህ አይነቱ ኹኔታ በመደጋገሙ ወደ ቢሮዉ ሲጠራኝ
የቻልኹትን ያህል እልህ ጎርሼ ነዉ የምገባዉ።
"ምነዉ?" ይለኛል
"እንዴት?" እለዋለኹ
ዝም ብሎ ቀብራራነቱን ሊያሳየኝ ይሞክራል...።
እየቆየ ግን እኔም ለመድኩትና በቀን ዉስጥ ወደ ቢሮዉ
ካልጠራኝ ማንጋጠጥ እጀምራለኹ። ፀሓፊዉ ታዲያ ዐይታ
ፈገግ ትላለች(እሷም ሴትናትና የገባት ነገር ይኖራል)።
125
| ናትናኤል ዳኛው
አንዳንድ ጊዜ "ፀሓፊዋ ጋር ግንኙነት ይኖረዉ ይሆን?"
እያልኩ ሳስብ አገኘዋለኹ ራሴን። በተለይ ወጣ ገባ ስታበዛ።
በ;ሷ ወጣትነቴን እያሰብኹ እተክዛለኹ። ከቆዳችን ቀለም
ዉጭ ብዙ ነገራችን ይመሳሰልብኛል። ስክነቷ እንደኔዉ
ሌሎችን የሚያበሽቅ ነዉ።
ስብሰለሰል አደርኹ... ይኼ ሰዉየ ፓብሎቭ እኔ ደግሞ
ዉሻዉን የኾንኩ ያህል ነዉ የሚሰማኝ። መስሪያ ቤት ሄጄ ከ'ሱ
ቢሮ ሳይገቡ መመለስ ድብርት ይለቅብኛል። ቤቴ እንኳ ገብቼ
ረፍት የለኝም። ስልኬን አነሳለኹ...ቁጥሩን አዉጥቼ ልደዉል
እልና መልሼ እተወዋለኹ። ከዚህ ኹኔታ ለመዉጣት የማልይዝ
የማልጨብጠዉ የለም። ምግብ አበስላለኹ፡ቡና አፈላለኹ:፡
ፊልም አያለኹ፡መፅሓፍ እገልጣለኹ...ኹሉም ግን አእምሮየ
ዉስጥ ከ'ሱ ቀጥለዉ የተመዘገቡ ናቸዉ። ልጄ ዩኒቨርሲቲ
ከገባች በተለይ ደግሞ ድመቴ ከሞተች በኋላ ስፋቱ ሊዉጥኝ
ነዉ እያልኩ አማርረዉ የነበረ ቤት ይጠበኝ ጀመረ። ...ከሳሎን
እስከ አልጋ ቤቴ አመሰቃ ቅለዋለኹ።
ትዳር ላለዉ ወንድ እንዲህ መኾኔ ነዉ የሚያበ ሳጨኝ...
በሞራል ህግ የታጠርኩ ሴት ነኝ...ራሴን፡ሴትነቴን የማከብር
ግን ሲሰራበት የማይለምድ የማይለመድ የለም... ስልጣኑንና
ብልሃቱን ተጠቅሞ እንደላብራቶሪ አይጥ እሱን መናፈቅ
አለማመደኝ... ቀድሞዉን ባዶ ልብ መያዝ ይኾናል ያጋለጠኝ።
ከትዳሩ እንደማላስኮበልለዉ እኔም ከቁንጅና ይልቅ ለማረጥ
126
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በረቀበ ዕድሜዬ ወደ ትዳር እንደማልገባ አዉቀዋለኹ... ግን
የተሰራብኝን ማንፀባረቀ አለብኝ እና ነዉ እንዲህ መኾኔ።
ጠዋት ወደ ቢሮ ልሄድ ስነሳ
እንዳለብኝ ወሰንኩ።
መስሪያ ቤት መቀየር
ቢሮ የገባኹት የመጨረሻ ቀኔ እንደኾነ በማሰብ ነዉ።
የጀመርኩትን ሳልጨርስ በዉዝፍ ትቶ መዉጣቱን
ስላልመረጥኩ ያለ ዕረፍት ተያያዝኩት። በመኃሌ ፀሃፊዋ
መጥታ አለቅየዉ ቢሮ ነይ ብሏል አለችኝ። በጣም
አመነታኹ...አልሄድም ብየ ወሰንኩ...ከእሱ ይልቅ ስለሷ ማሰብ
ጀመርኩ። የሻይ ረፍት ላይ እፈልግሻለኹ ብየ ወደ ሻይ ቤቷ
አብረን ሄደን። በርቀቴ ኹለት ቡና አዘን ተቀመጥን።
መስሪያ ቤት ልቀየር መኾኔን ባልነግራትም ስለራሴና
የህይዎት ልምዴ እተርክላት ጀመር። ሴቶቹ በጎናችን የፌርሞን
ስልቦቻቼዉን አስከትለዉ እያስካኩ ያልፋሉ።
"በልጅነቴ ነዉ የወለድኩ...ሴት ልጅ አለችኝ" አልኳት
"ታድለሽ" አለች...ፊቷ በመሻት ሲበራ አየኹት
"አዎ...ብታያት ደግሞ የምታሳሳ ልጅ ናት"
"አታስተዋዉቂኝም?"
"ደስ እያለኝ...
127
| ናትናኤል ዳኛው
...እሷን ሳረግዝ አስራ ሰባት አመቴ ነበር፡ ጎበዝ ተማሪ
ስለነበርኹ መምህራኖቼ በጣም ያቀርቡኝ ነበር...እኔም አንቺ
እንደምታውቂኝ ቁጥብ አልነበርኩም።"
ፊቷ በግርታ ሲለዋወጥ አስተዋልኩት
"ኹሉም ወዳጄ...ኹሉም ዘመዴ ነበር። በዚህም
መምህራኖቼን እንኳ እንደ እኩያ ነበር የምቀርባቼዉ።
እንግዲህ በዚህ መሃል ነዉ ልጄ የተረገዘችዉ።
"ማ...ለት? ከማን?"
"ባዮሎጅ መምህሬ ነበር።...ባዮሎጅ እወድ ነበር። ህልሜ
ኹሉ ባዮሎጅስት መኾን ነበር።...የሚታየኝ ኹሉ ነጭ ጋወን
ለብሼ...መነፅር አድርጌ ስመራመር ነበር። ማካበዴም ሳይኾን
ባዮሎጅን በርብሬ ነበር የማዉቀዉ"
"እ...ሽ"
"ብቻ ቀረቤታችንን እንጂ ብልግናዉን ያላወቅኹበት
መምህሬ ስሜቱ ከህልሜ በልጦበት ሰበረኝ። አኹን ልጄን ሳይ
ግን እፅናናለኹ።"
በመደንገጥና በመገረም ታየኛለች...የመጣዉ ቡና
ረስተነዉ ቀዝቅዞ ስለነበር አስተናጋጇን ጠርቼ እንድትቀ
ይርልን ነግሪያት ወደ ጀመርኩላት ተመለስኩ
128
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"ት.ቴ ተቋርጦ...እንደ ገና እሷን ለ'ናቴ ሰጥቼ ነዉ
የቀጠልኩት...ግን አቋራጭ መንገድ ፈልጌ ልጄን ራሴ ማሳደጌ
ስለነበረብኝ አካዉንቲንግ በዲፕሎማ ተምሬ ነዉ የመጀመሪያ
ስራየን የተቀጠርኩት።"
"ይገርማል ... ለኛ ግን ዉበትና ኩራትሽ እንጂ ይኼን የቻለ
ልብሽ አይታየንም።"
"አዎ...በፈተና በርትቼ ነዉ። ግን የማንበብ ልምዴም
የጠቀመኝ ይመስለኛል።"
"እንዴት?"
"ማለቴ በዛ ፈተና ዉስጥ ኾኜ እንኳ ለልጄ ስል ነገን
ስለማስብ በአገኘኹት አጋጣሚ ለማንበብ እሞክራለኹ...
...እህ ታዉቂያለሽ መልኣክ የኾነ አፍቃሪ ነበረኝ
የየእርምጃየ ኹሉ ደጋፊ ግን አንድም ቀን አፍቅሬዉ አላዉቅም
የዚህ አኹን አለሽ የምባለዉን ጥይካሬና ብልሃት ምንጭ እንኳ
እሱ የሰጠኝ ማረከስ ኦረሊየስ የሚባል ከማደጎነት ተነስቶ ንጉስ
መኾን ላይ የደረሰ ሮማዊ ፈላስፋ መፅሓፍ "ሜዲቴሽንስ"
ነዉ።"
"አንቺ ሴት ግን የማዉቅሽ ሳሊል ነሽ?"
129
| ናትናኤል ዳኛው
"ሃሃ አይዞሽ ነኝ...ልጅነቴን ስላየኹብሽ እና መስሪያ ቤትም
ልቀይር ስለኾነ ነዉ… ኦፍ ኮርስ ቤተሰብ እንድትኾ ኝኝም
ስለምፈልግ ነዉ።"
"እሽ ግን መስሪያ ቤት ለምን?...የተሻለ ክፍያ አግኝተሽ
ነዉ?"
"አረ ገና ልፈልግ ነዉ...ግን መቀየር ስላለባት ብለሽ
እለፊዉና...ቡናሽን ጨርሽ አረፈድን መሰለኝ።"
" ያ አፍቃሪሽስ የት ደረሰ?"
" ህልሜን እየኖረልኝ፡ አሜሪካ ነዉ የሚኖረዉ ግን
አላገባም...ብታይ ልጄ ስትወደዉ።"
"ዛሬም ትገናኛለችኹ?"
"ልጄን የሚያስተምራት እሱ ነዉ ማለት ትችያለሽ።"
"እዉነትም መልዓክ"
"በበነገርሽ ላይ ስሙ መላክ ነዉ።"
"ይገባዋል በእዉነት"
"ግን አኹን መጥቶ ላግባሽ ቢልሽስ?"
"ልጄ ለፍታ ነበር...ፈቃደኞች አልኾንላትም...እኔ እምቢ
ያልኳት እሱን ጠንቅቄ ስለማዉቀዉ ነዉ።"
130
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"እንዴት?"
"ይሉኝታና ዉለት መመላለስ አይወድም...
እሺ ብልሽ እናጠዋለን...ብየ አሳመንኳት።"
ከቀጣዩ ቀን ጀምሮ ለዛ መስሪያ ቤት እንግዳ ኾንኩ። እሱን
የመልቀቂያ ደብዳቤየን አልቀበልም ብሎ ለሳምንት ያህል
አመላለሰኝ። አምርሬ መልቀቄን ሲያዉቅ ግን ጥሩ የስራ ልምድ
ፅፎ ከቦነስ ደመወዝ ጋር ሰጠኝ። ለትጋትሽ ምስጋና የሚኾን
መሸኛ ካለዘጋጄን ያለዉን ግን እምቢ አልኩት።በኹለተኛዉ
ሳምንት ሙሉ በሙሉ ክሊር አድርጌ ወጣኹ።
131
| ናትናኤል ዳኛው
እንደምትወደዉ
በጠቢብነት
ያደገ
ረቂቅ
መንፈስ
እንዳላት
አልጠራጠርም። "እብድ ናት" ቢሏትም ስለማይመስሏት ነዉ።
እኔ የሰዉን ልጅ የመኾን ጥግ ያየኹት በሷ ነዉ። ስትፈራና
ስትሸሽ አላዉቃትም። "መኾንም መኖርም ካለብኝ ሰዉ ፈርቼ
አልቀርም። ተግዳሮች ሸሽቼ አልመለስም።" ትለኛለች
እሷን ከመረዳት ይልቅ መስማት ነዉ የምፈልገዉ።
ሳያትም ሳዳምጣትም ዘባተሎየ ኹሉ ተንኖ ሰላም
ያረብብኛል። የምወደዉ ይህን የሚጋባብኝን ፀጥታ እንጂ
የምትናገረዉን ተረድቼ አዋቂ ምናምን መኾን አሰኝቶኝ
አይደለም።
"ማህበራዊዉን ህግ አልጠላዉም፡አልቃወመዉም። ግን
ይተዉኝ ቀለሜን ጨፍልቀዉ ባዶ እንዲያደርጉኝ አልሻምና።"
ስትል የምሰማበት ጊዜም አለ።
የምትለዉ
አያቅተኝም።
ባይገባኝም
ቢያንስ
ማስታወስ
ግን
በረንዳ ላይ በጣቶቿ መኃል የያዘችዉን ሲጋራ በፍቅር ወደ
ከንፈሯ አስጠግታ እየማገችና የማገችዉ ጪስም መልሳ
በቀስታ እየተፋች ሩቅ ተጉዛ ትመለሳለች።... ባላጨስም ከአፏ
የሚወጣዉ ጪስ ግን አይረብሸኝም።
132
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ሌላዉ ተንጨባረረ የሚለዉ ፀጉሯን ሳይ የምትቦርቅ
ጥቁር ነፍስ ትታየኛለች። ...ሰፊ ቲሸርቷንና ቅድ ቁምጣዋን
ሳስተዉል ነፃነት እየፈለገች ግን በልኳ ያላገኘች ትጉህ ነፍስ
አስባለኹ።...አንድም ቀን ግን ከአልባሷ ሾልኮ ለሚታየዉ
ቅንዝር ወጣሪ ገላዋ አልተጨነቅኹም።
ማለዳ ከምትቀመጥበት የቤቷ ደረጃ ፊት ለፊት የመሳያ
ሸራዋን ወጥራ ለረዥም ሰዓታት ስታፈጥበት ነዉ የማያት። እኔ
ይሰለቸኛል፡ ከሷ ባዶ ሸራ ላይ አንስቼ እግዜር ምን ለማለት
ፈልጎ እንደሳላት ወዳልተረዳኋት እሷ እሸሻለኹ።... ባዶ ነገር
ማየት ይረብሸኛል...አርት የለኝም ካለመኖር መኖርን
የሚያስገኝ።
አንድ ቀን "ዝምታህንና አፍጣጭነትህን እወደ ዋለኹ"
አለችኝ... ፈገግ ማለቴን አስታዉሳለኹ።
"ጠልቀህ የምታነበኝ ይመስለኛል። አንዳንድ ጊዜ
ምስጢሬን ኹሉ አዉቀኽ ጥለኸኝ ትሄድ ይኾን? እያልኩ
እጨነቃለኹ።" ትላለች በዝምታ እሰማታለኹ
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ "ዛሬ ሙድ ላይ ነኝ።" ትልና እጄን
ይዛ ወደ ሳሎን ትወስደኝና ሙዚቃ ከፍታ እየሾረች ለዳንስ
ትጋብዘኛለች።
እጆቿን ትከሻየ ላይ አድርጋ የኔን ደግሞ ዳሌዋ ላይ
ታሳርፋቸዋለች።
133
| ናትናኤል ዳኛው
ከደቂቃዎች በኋላ ከሰመመን እንደ ነቃ ሰዉ ስባንን ራቁት
ገላችንን ሳሎን ላይ አገኘዋለኹ።
ራሷ ደረቴ ላይ አንድ ጭኗ በጭኖቼ መኃል ኾኖ ፊቷ ላይ
እርካታ እየተነበበ ተኝታ ሳያት የሃፍረት ሳቅ ይታገለኛል፡
እንዳልቀሰቅሳት አፌን በእጄ አፍናለኹ።
"ለምንድን ነዉ እንደምወደዉ አድርጎ የሰራህ?" ትለኛለች
"አንቺን እንደምወድሽ አድርጎ ስለሰራሽ።" እላታለኹ
"ጮሌ" ብላኝ ትፍለቀለቃለች...ፈገግ ብየ አያታለኹ።
134
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የሰዉ ኑግ
ሲወለድ ያች ደሳሳ ቁናሳም የሳር ክዳን ያላት ጎጇቸዉ
በጭስ ታፍናና ጠቋቁራ ልጥልጥ ኑግ መስላ ስለነበረ ነዉ
መሰለኝ እሱም ፉንጋ ጥቁር ኾነ።
የወላጆቹ መልከኛነት የሚያዉቅ ያገር ሰዉ "የፈረንጅ
ግልገል የመሰለ ጨቅላ ተገላገለች" ሊል አፉን አሞጥሙጦ
ሲመጣ ያገኜዉ ከደመና በነጣ ጨርቅ የተጠቀለለና ጥንጤ
ዐይኑ ብቻ የምትታይ ሰዉ የኾነ ጥቁር ቀለም ነዉ።
"የምን 'ርግማን ወረደባቼዉ" ተባለ
እናቱ ነገሩ እንግዳ ቢኾንባትም ልጄ አይደለም ብላ
መግፋት ግን አልኾነላትም።
አባት ብልኮ ፎጣዉን ተከናንቦ ከጎጆዉ በር ላይ ያለ ሰፌድ
አይነ በጎ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ ንቃቃት በአጠቃዉ እግሩ
መሬቱን ይተመትማል። በቀየዉ ጥቁር ወንድ እየፈለገ ነዉ፡
ሚስቴን ወሸመ፡ የሱ ፍስ የኔን ፍስ በልጦ መሳይ ልጁ
ተወለደለት የሚለዉ። ሊያገኝ አልቻለም፡ እግዜር ከ'ሱ ጋር
ቁማር የጀመረም መሰለዉ...ዉጤቱን ሰጥቶ ሰበቡን የነሳዉ።
"ዘመኔን ሙሉ ተቃጠል ቢለኝ እንጂ ጭሱን አሳይቶ
እሳቱን የሸሸገብኝ!" ይላል ለራሱ
135
| ናትናኤል ዳኛው
እንዲያ ማሰብ፡ እንዲያ ማለት ባይፈልግም ሃሳቡ ሽዉ
ብሎ አንድ ቦታ ላይ ሲወተፍ ታወቀዉ
"ምናምንቴዉ፡ምናምንቴዉ..." አለ እየፈራ...እሱን አገኜና
ክፍት ሰበብና ክፍት እሳት
ወዲያዉ ያችን የሚወዳትን ባሻዉ ሰዓት የሚተኛትን ገር
ወዛም ሚስቱን አሳልፎ መስጠቱ አመመዉና "የኔዉ እዳ
ነዉ...ማን ያዉቃል በ'ሷ ወይ በ'ኔ የዘር መስመር ኑግነት
ቢኖር...አልያ የመሸበት የእንትን ሀገር ነጋዴ የእግዜር እንግዳ
ብሎ ከምንጅላቴ ተጣብቶ እንደኹ!?" ተፅናና
ጥርጣሬዉን ትቶ ሃሳቡን አራስ ሚስቱን እና የሰዉ ኑግ
ጨቅላውን መንከባከቡ ላይ አደረገ።
ሚስቱ ህፃኑን ስትወልድ ካወጣችዉ የሲቃ ድምፅ በኋላ
አንደበቷ ተዘግቷል። ይኼም አዲስ መርዶ፡እንግዳ ዜና ነበር።
አንድ ቀን ይኼ ኑግ መሳይ ጥላሸት ጨቅላ ዓመት እንኳ
አልሞላዉም...በሰዉ አፍ ሲታኜክ ከርሞ መረሳት ሲጀምር
ከዛችዉ የሳር ጎጆ ኡኡታ ፈነዳ። ለወሬ የፈጠነች የእጇን ሊጥ
ሳትታጠብ...ልታስር
የጀመረችዉን
ሻሽ
ሳትቋጭ
እያንዘላዘለች...አንድ እግር በረባሶ የለበሰ...በ'ጁ ካዝና የሌለዉ
መሳሪያ ያንጠለጠለ ገበሬ...ቤቷን ሞሏት።
-ምን ኾነ? ሲባል
136
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
-የሰዉ ኑግ ደርሶ ክርትም አለ!
-እንዲያዉ ደርሶ
-ሳጠባዉ ቆይቼ (ይኼን ልጄ ብላ ታጥባዉ? መባልን
ስለምትፈራ በፊት ስታጠባዉ ከሰዉ ተደብቃ ነበር) ወዲያዉ
አባቱ (እንደማትታመን ብታዉቅም) ከመም ጣቱ በፊት ግብር
ዉሃ ልዉጣ ብየ ሄድኩ
-እ..ሺ...(ልጁ
አሰፍስፏል)
ተረስቶ
ኹሉም
ሰበቡን
ለማወቅ
-ከዛ ተመልሼ ቅሌን(ፎሌየን) አኑሬ ዘወር ስል በአፉ ምራቅ
ሞልቶ ክርትም ብሏል...ኡ ኡ ((የረሳችዉ ትዝ ብሏት
አቀለጠችዉ))
አባቱ እሾህ በወጋዉ እግሩ እያነከሰ ደረሰ።
እናቱና ቀየኛዉ የሰዉ ኑግ የተኛባትን አልጋ ከበዉ
አገኛቼዉ። የእሱን መምጣት አይተዉ መገነዣ ክርና ጨርቅ
ሊያመጡ ይሯሯጣሉ የቀየዉ አንዳንድ ወንዶች። እሱ እጁን
ወደ ልጁ አንገት እጁን ሲሰድ ትር ትር የምትል ትንፋሹን ሰምቶ
"ነፍሱ አልወጣችም" አለ
ኹሉም ተደናገጡ...አንድኛዉን
አልቀብርም" አላቼዉ፡፡
"ነፍሱ
ሳትወጣ
137
| ናትናኤል ዳኛው
በዚህ ጊዜ ነዉ...የእናት ዲዳ አንደበት መፈታቱን
ማስተዋል የጀመሩት...ጉድ ተባለ።
አንድ...ኹለት....ሶስት...አራት ሳምንታት አለፉ። ሌላ ወሬ
ሌላ ርዕስ ኾነ የሰዉ ኑግ ነገር።
በተኛበት የቆዳዉ ቀለምና ቅርፅ ሲለወጥ ሲያስተዉሉ
"በሽታዉ ንጣታም አደረገዉ" አሉ እንጂ አንዳች መለኮታዊ
አልያም ዝግመተ ለዉጣዊ ሂደት ግን ሲካሄድበት ነበር።
ያለምንም ምግብ ትርትር በምትል የአለሁ ምልክቱ ብቻ
ለሰባት ወራት በእንቅልፍ አሳልፎ ብርሃናማ የቆዳ ቀለም...ቦግ
ያሉ ዐይኖች..ስልክክ አፍንጫ...ዞማ ፀጉር እና ዘለግ ያሉ
ቅልጥሞች ያሉት ኾኖ ከእንቅልፉ ነቃ።
ሌላ ኡ ኡ ታም ኾነ።
138
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
መክቱብ
ዕድሜን የመቁጠር ቁማር ዉስጥ መግባት ባልፈልግም...
የዉስጥ ናፍቆቴን መደበቅ ያለብኝ አይመስለኝም። ፍቅረኛ
መያዝ የፈለግኹት ዕድሜየን ፈርቼ አልያ በስልክ የሚላላሱ
ጓደኞቼ ተፅዕኖ ኖሮብኝ አይደለም። በቃ አፈቀርኩ...ከፍቅር
የራቀ ሰዉ አፈቀርኩ። ቀላል በማይባል ማፍቀር አፈቀርኩት።
ከእኔ መኾኑን የምጠራጠረዉን ዜማ ማፍለቅ ጀመርኩ። ነገሬ
ኹሉ ጥንድነት ላይ ኾነ...ጥንድ መኾን በቻሉ አእዋፋት እንኳ
እቀናለኹ... የጓደኞቸን ስጠራጠር የእነሱን ግን አምነዋ ለኹና
አብዝቼ እቀናለኹ። ለእሱ በግልፅ ያለመንገሬ ምክንያት አንዱ
ይኼ ይመስለኛል። ኹልጊዜ በ'ሱ ደደብነት ማሳበብም ሌላ
ድድብና ነዉ። ፍቅር ላይ ደደብ ነዉ።... የአእምሮዉ ጂኒየስነት
የልብ ጨዋታ ላይ አሸናፊ አያደርገዉም። ግን ለምን
አፈቀርኩት?...እንዴት አፈቀ ርኩት?... አፍቅሬዉ ነዉ
ያገኘኹት...ድንገት ልቤን ስፈትሽ ጠበበኝ። በቃ ሰዉ መኖሩን
አወቅኹ።
የ'ሱ
ወቅትን
ጠብቆ
የሚወረወር
እወድሻለኹ...ወጥመዴ ኾኖ እንደኹ እንጃ!?
የሚያናድድ ልበሙለነት አለዉ...እዛ ተማሪ ቤት እያለን
ፀጥታዉ ደስ ይለኝ ነበር። ተነጥሎ የራሱን መንገድ ተላሚ
መኾኑ እንዲኹ ደስ ይለን ነበር...እኔ ብቻ ሳልኾን ጓደኞቼም
ጭምር።
139
| ናትናኤል ዳኛው
ያላሰብኹት...አንጋጦ እንጂ ፊትለፊት አያይም የምለዉ
ሰዉ...ድንገት አስቁሞ "እወድሻለኹ!" አለኝ
የታባቴ ተንጠልጥየ ታየኹት ይኼ ጀብራራ!!
ዐይኔ ሰፋ...የማወጣዉ ቃል አጣኹ እና የዩኒፎርም ጉርዴን
ሰብስቤ ጥየዉ ወደ ክፍል ሮጥኩ።
ለጓደኞቼ ራሱ ምን ብየ እንደምነግራቸዉ አላዉቅም
ነበር።ጌታን!!
አኹን ስለዚህ ልጅ የፍቅር ጥያቄ ምን ተብሎ ይወራል...
ግን ከዛ በኋላ እንደተቀየርኩ አዉቃለኹ... አንገቴ ቀና ብሎ
መራመዴን አስታዉያለኹ።...
"ለካ እታያለኹ" ብያለኹ ለራሴ
የሴት ልጅ ልቦና ከመጀመሪያ የፍቅር ጥያቄ በፊትና በኋላ
የሚል መልክ እንዳለዉ የዛንጊዜ ነዉ ያወቅኹት።
ከዛ በኋላ ያየኛል ብየ የተሽቆጠቆጥኩባቸዉ ግን ዐይኑ
ሩቅ የኾነብኝ ጊዜ ብዙ ነዉ። ገድሉ እስከዚች የኔን አንገት ቀና
እስከማድረግ ነዉን? ብየ ራሴን ከ'ሱ ለማሸሽ በጣርኩባቸዉ
ጊዚያት ደግሞ መጥቷል።
የዛን ጊዜም ምንም አላልኩትም...ቢያንስ ግን የጉንጩን
ፍሬ እስኪጨርስ ሰምቼዋለኹ።....ሲያወራ ደስ ይላል ግን ቃላቱ
140
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ጠጥረዉ ነዉ የሚሰሙኝ። "ለፍቅር ቀላል አይደለም ይኼ
ሰዉ" ብያለኹ...በየት በኩል ቢኼድ እንኳ እዚህ ላይ
እንደሚደረስ አላዉቅም።
አንዲት የፕሪፓራቶሪ ኮረዳ ከጎረምሳ ጋር ከሚያላፋት
ጨዋታ በቀር ሳይንስ ወላ ስነ-ፅሁፍ ምኗ ነዉ?
እሱ ግን እነዛን ይወዳል። ላስለምደዉ ሞክሬ ነበር....
ሒሳብ አስረዳኝ ስለዉ... እሱ የእዉነት ሒሳብ የአሳሰበኝ
ይመስለዉ ነበር... የእኔ ሒሳብ ግን ያ አልነበረም...
የምንቀራረብበትን መንገድ እያሰላኹ ነበር።
ትንፋሹን ለመልመድ መጣሬ ነበር።...እሱ ግን ቀን
እየቆጠረ ከሚልልኝ እወድሻለኹ በላይ መኼድ አልቻለም።
ራቅኹት...የምንተያይበት ጊዜ እንኳ ጥቂት ነበር።
የዛንጊዜ ነዉ የሚያበሽቅ ልበሙሉነት አለበት ማለት
የጀመርኩት። ለፍቅር ደደብ ነዉ ያልኩት ሰዉ...ፍቅር
ይከብደዋል ብየ የራቅኩት ሰዉ...እንዴት ሳይለምደኝ ብየ
ተከፋኹ።
ዩኒቨርስቲ ገብተንም እንኳ ኹልጊዜ ይገርመኛል። ሰዉ
እንዴት ፈዞ ይደምቃል?...ሩቅ ኾኖ ይቀርባል?
እንዲህ ነዉ የምለዉ የፍቅረኛነት ገድል አይኑረኝ እንጅ
ለወንድ ጥያቄ ባይተዋር አይደለኹም። ለልብ የሚደርሱ
የአፍቃሪ ነን ባይ ገድሎችን አይቻለኹ...ግን ደደብ ነዉ ያልኩት
141
| ናትናኤል ዳኛው
እሱ ጎልቶ ይታወሰኛል።..ከ'ሱ የተማርኩ ይመስለኛል ነገር
አለስልሶ መያዝን...ሰልጥኖ ገዥ...ኮስሶ ተገዥ እንዳይኾን
ማድረግን። ወዳጆቼ "እሷ እቴ አይሞቃት አይበርዳት" ሲሉ
...እኔ "እሰራዋለኹ ያልኹት ሰርቶኝ ኼዷል ለካ" እላለኹ
...አንዳንድ ጊዜም ''እሱ ጠየቀ እንጂ የአፈቀርኹት እኮ እኔ ነኝ''
እላለኹ ስለሚገርመኝ። ማፍቀር ቀላል ኾኖ ከልብ ፍቆ መጣል
ቢቻል...እንዳፈቀርኩት የማወቅ ዕድል ሳይኖረዉ እንኳ ነዉ
አሽቀንጥሬ እጥለዉ የነበረ።
ከኹለት ዓመት በኋላ ይመስለኛል...ትናንት ሲደዉልልኝ።
ስሙን የስልኬ ሰሌዳ ላይ ሳይ በድንጋጤ ከጠቀመትኹበት
ተነሳኹ... የመመረቂያ ፕሮጀክት አብረዉኝ ከሚሰሩ ጓደኞቼ
ጋር የመማሪያ ክፍል ዉስጥ ነበርኹ።
ኹሉም ደንግጠዉ ወደ'ኔ ዞሩ። እጄ ስልኩን መያዝ
እስኪከብደኝ ድረስ ይንቀጠቀጣል። ጎኔ የነበሩ ዐይናቸዉን ወደ
ስልኬ ሲልኩ...ስሙ እንዳይታየቼዉ አድርጌ ዘቀዘቅኹትና ቀስ
እያልኩ ወጣኹ። ከክፍል እስክወጣ ስልኩ ጥሪዉን ጨርሶ
ተዘጋ።
የኮሪደሩን
አግዳሚ
ይዤ
ለመረጋጋት
እየሞከርኹ...ለምን እንዲህ መኾን አስፈለገኝ በሚልም ራሴን
ላይ ተበሳጨኹ።... ዝም ስላለ የረሳኹት መስሎኝ ነበር
እንዴ?... ምናልባት እሱም እንዲህ ይኾናል የሚያደርገዉ...
የዘነጋኝ የመሰለዉን እኔ ምን እንደሚያስታዉሰዉ
ባላዉቅም...ሲያስታዉሰኝ
ግን
እንደዚህ
ይኾናል
የሚያደርገዉ።
ይኼ
ግን
ለ'ኔ
የሱን
ያህል
142
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
አይቀለኝም...እወድሻለኹ የሚል ወንድ እንደሚዘነጋኝ ማሰብ
ህመም ነዉ።.... ይበልጥ የሚያመኝ ግን ይኼን ሰዉ ማፍቀሬ
ነዉ።.... ማፍቀሬን ደዌ የሚያደርግብኝ ደግሞ ሴት ስታፈቅር
ማምለጫ እንደማትሻ ማወቄ ነዉ።
እንደ እኩዮቼ ከመኾን ያገተኝ ማፍቀሬን ማመኔ ነዉ።
ዛሬ በተረሳች የስልክ ጥሪዉ በጥንካሬየ በሚያዉቁኝ
ጓደኞቼ ፊት አርበትብቶኛል። ነገ ፊቴ ባገኘዉ ምን እንደምኾን
አላዉቅም።
ለ'ሱ ይች ጥሪ እንደለመደዉ "ዛሬ እንዴት ትዝ አልኩህ?"
ስለዉ "እንደረሳኹሽ እርግጠኛ ነሽ" ብሎ ከመመለስ የዘለለ
ዓላማ አይኖራት ይኾናል...ወይንም "እህ... እንዴት ይዞሻል
ግቢ... ላይፍ...ፍቅር?" ብሎ ከጥንድነት መድረሴን መፈልፈያ
ጉጡ ልትኾን ትችላለች... ለ'ኔ ግን ወደ ሸሸኹት ህመም
መመለሻ ናት።...በሚወደኝ የምዘነጋ… እሱኑ የማፈቅር ተራና
ቂል መኾኔን ማስታወሻ...በድብቅነቴ የገነባኹትን ጥንካሬ
በእኩዮቼ ፊት የምትንድ ደማሚት ናት።
እንዲህ ስብሰለሰል ስልኬ መልስ እዝዝ ብሎ አስደነገጠኝ...
እሱዉ መልሶ መደወሉ ነዉ።...አመነታኹ ...በጣም
አመነታኹ...ግን በሚደንቅ ኹኔታ የረሳኹት ድምፁ ይናፍቀኝ
ጀመር...ሲያወራ ድምፁ ዜማ አለዉ...ከርቀት እንደሚሰማ
የቤተስኪያን ደወል ነዉ... እወድለት ነበር። አስታዉሳለኹ በዛ
143
| ናትናኤል ዳኛው
ሰሞን "እርግጠኛ ነህ ለሙዚቃ ድምፅ የለህም?" ብየዉ
ነበር...ያ ድምፁ ናፈቀኝ።
አነሳኹትና ተቅጨልጫይ ድምፁ ለጆሮየ ሲደርስ ልቤን
ሞቃት...ዐይኔን ጨፍኜ "ሃሎ" ከማለቱ "ማን ልበል?" አልኩት
እንዲያዉ ከዚህ በፊት ለማላዉቃቼዉ ቁጥሮች እንኳ
እያዋራኹ በድምፃቼዉ አዉቃቸዉ እንደኾነ ለመለየት
እጥራለኹ እንጂ"ማን ልበል እል ነበር?"...ፈፅሞ አልልም...ጌታን
አልልም...ብልግና ነበር የሚመስለኝ... ቁጥራቸዉን ማወቅ
ሲገባኝ ባለማወቄ የማስቀይማቼዉ ይመስለኝ ነበር...ደግሞስ
ወጣት ሴት አይደለኹ...ማንም ሊደዉል ይችላል።
ታዲያ አኹን ረስቸሃለኹ ለማለት ነዉ ዘልየ "ማን ልበል?"
ማለቴ....አቤት የመረሳት ፍርሃት!!
ብዙ አላደነቀዉም መጀመሪያ ሳቀ ቀጥሎ ለሰስ ባለ
ድምፅ "ይገባሻል" ሲል ሰማኹት....ቀጥሎ "ዞላ ነኝ ማሂዬ" አለ
ማሂዬ! ሲል ነዉ የሰማኹት...አረ ስሙ ማህሌት እንኳ
ብሎ ለመጥራት ይሰስት የነበረ ሰዉ አቆላምጦ ጠራኝ
"ዘ ላ ለ ም ኦ! ዛሬ ከየት ተገኘህ ባክህ?"
"ካለኹበት...እንዴት ነሽ?"
"ደህና ነኝ...አንቺ እንዴት ነሽ?"
144
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"በጣም ደህና...ታዲያስ ምን ላግዝህ?"
አረ ተይ በሉኝ ምን ማለቴ ነዉ አኹን ደርሼ እንዲህ
ጋጠወጥ መኾኔ?... ይኼዉ ፈለገኸኝ መጣህ...ባንተ የመፈለግ
ርሃብ ነበረብኝ ማለቴ ነዉ...?
"እ...ወደ ግቢያችኹ መጣን እና"
"የት...ሰላመ-በር?"
"አወ ኤስቢ ለትሪፕ መጥተን... ሃይ ልበልሽ ብየ ነዉ"
"አረ..."
"አወ ምነዉ?
"አረ ምንም" ተምታታብኝ የማስበዉ ነዉ ግራ
የገባኝ...ከዚህ ኹሉ ጊዜ በኋላ እንዴት ነዉ የማገኘዉ?...ፍላጎቴ
እዛዉ ሲሞት ታወቀኝ።
"እደዉልልሃኹ" ብየ ምላሹን ሳልሰማ ፈጥኜ ዘጋኹት
በቃ አልኩ ለራሴ...ድንገት እንዴት እንዲህ እንዳልኩ
እንጃ...ግን ልቤ እንደዛ አለኝ። ለራሴ እንግዳ የኾንኩ ያህል
ተሰማኝ። ማየት አለመፈለጌ የፍርሃት ይኹን የጥላቻ አልገባሽ
አለኝ...ደርሼ ልጠላዉ አልችልም...ቅያሜዉ ይኖር ይኾናል።
ደግሞስ እንግድነት መጥቶ ላግኝሽ ሲለኝ ምን ፈርቼ እንደዛ
አልኩት?
145
| ናትናኤል ዳኛው
አኹንም ስሜቴ ለ'ኔ እንኳ ግልፅ አይደለም... ምናልባት
ለትሪፕ ከማለት ይልቅ አንቺን ላገኝ መጣኹ ቢለኝ እንዲህ
እለዉ ነበር??
እንዲህ መኾኔ እንደ ቁጥሩ የሴት ልጅ ልቦና ላይ
ብልጣብልጥ ዕዉቀት ካለችዉ ክንፍ ያልኩ አፍቃሪዉ መኾኔን
አይነግረዉም??
መልሼ ደወልኩለት ስልኩ ግን አልተነሳም።...ደረጃዉን
ቁልቁል ወርጄ ወደ መኪኖች መናኸሪያ አመራኹ። ከተለያየ
ዩኒቨርስቲ በመጡ መኪኖች ተሞልቷል... ተማሪዎቹ
ሻንጣቸዉን በጀርባቸዉ አዝለዉ ... ፍራሽ በትከሻቼዉ
አንግበዉ ወደ ማደሪያ ህንፃዎች ይሄዳሉ።...እዛዉ እንደቆምኩ
መልሼ ደወልኩለት... አኹንም አይነሳም። ማልቀስ አማረኝ...
እዚኹ በቆም ኩበት በጩኸት ምድር ሰማዩን ማንቀጥቀጥ።...
ሰማያዊዉን የማርዓምባ ዩኒቨርሲቲ መኪና ተደግፌ ራሴን
ላረጋጋ ሞከረኩ። የቀለለኝ ሲመስለኝ...ወደ መጣኹበት
መራመድ ጀመርኩ።...ትንሽ እንደሄድኩ ለስላሳ እጂ ከኋላየ
መጥቶ ትከሻየን ነካኝ። አልዞርኩም ግን ቆምኩ "ማሂ" አለኝ
በልቤ "ራሱ ነዉ፡ራሱ ነዉ" አልኩ
ካሰብኩት በላይ ተቀይሯል...እንደዚህ ዓይነት ቁንጅና
ይኖረዋል ብየ አስቤ አላዉቅም ነበር። የቆዳዉ ጥራት
ያስደነግጣል።...
146
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"ስልኩን ጆሮየ ላይ ስትዘጊብኝ ደነገጥኩ"
"ይቅርታ...እደዉልልሃለኹ ነበር ያልኩህ...መልሼ ስደዉል
አታነሳም።"
".አወ ወደ ማደሪያችን ሻንጣና ፍራሽ ለማድረስ እየሄድን
ነበር
...አኹን እኮ አይቼዉ ልደዉልልሼ ስል የኛን ባስ ተደግፈሽ
አየኹሽ" በዝምታ አደምጠዋለኹ
"ግን ደህና ነሽ አይደል?"
"እ ህ አዎ...እንደምታየኝ ነዉ"
"በጣም አምሮብሻል...ያዉ ድሮም ዉብ ነሽ"
በልቤ "ይኼ ሰዉ ማኳሸት ተምሯል" እያልኩ ለ'ሱ
"አመሰግናለኹ" አልኩት
በርቀት ኹለት ሴትና ኹለት ወንድ ኾነዉ የቆሙ ጓደኞቹን
አሳይቶ ላስተዋዉቅሽ ብሎ ወሰደኝ።
ወዲያዉ ነበር የጓደኝነት ኬሚስትሪያቸዉ የገባኝ...
እንዳሰብኩት ሌሎች ጥንድ ኾነዉ...እሱ ብቸኛ ጆከር ነበር።
የገረመኝ ግን ጠንቅቀዉ እንደሚያዉቁኝ ነበር ነገረ ስራቸዉ
ኹሉ... አስተቃቀፋቼዉ እንኳ ያስደነግጥ ነበር። ኹሉም እሱን
በስሙ ሳይኾን "ዘማህ" ነዉ የሚሉት... ኮይንድ* ቃል እንደኾነ
147
| ናትናኤል ዳኛው
ጠርጥሬ ነበር...እርስ በርስ የሚጠራሩበት የፍቅር ጓኞችን ስም
እያጣመሩ እንደኾነ ሲገባኝ ያሰብኩት እንዳይኾን ብየ
ጨነቀኝ።
እዛዉ እንደቆምን ወደ ባህላዊ ጭፈራ ቤት ካልሄድን
የሚል ሃሳብ አመጡ...እኔን ደግሞ "የምሽቱ አጋፋሪ" ብለዉ
ሰየሙኝ። ምሽት የመዉደዴን ያህል ሰ/በርን በማታ
አለማወቄን መናገር ከበደኝ...በደፈናዉ "እሺ" ብያቼዉ
በቅድሚያ ግን "ወደ ዶርም መሄድ አለብኝ" አልኳቸዉ...ኹለቱ
ሴቶች ዶርሜን ለማየት ተከተሉኝ... ነፃነት አልሰማሽ
አለኝ...አንዳንድ ጊዜ እየተሳሳቱም ይኹን ኾነ ብለዉ በነሱዉ
ልማድ "ዘማህ" ብለዉ ይጠሩኛል... እንዳልገባኝ ዝም
እላለኹ...መልሰዉ "ማሂ" ሲሉ "ወይዬ" እላቸዋለኹ።
.
ጠዋት ስነሳ ራሴን ያላሰብኩት ቦታ አገኘኹት...ከጎኔ
ደግሞ እሱ ተኝቶ ነበር...የአልጋ ልብሱን ገልቤ ሰዉነቴን
አየኹት...ራቁቴን ነኝ...በደም ዳክሪያለኹ። ወለሉ ላይ
ልብሶቻችን ተዝረክርከዋል...በወንድ ፍስ የተሞሉ ኮንደሞች
ታዩኝ...ወደ እሱ ዞሬ አየኹ... በእርካታ ተዘርሯል።
ቅር አላለኝም...እሱን ግን ማቀፍ ፈለግኩ። ግን በእንዲህ
ዓይነት የኾነዉን ኹሉ በማላስታዉስበት መልኩ ክብሬ
መኼዱ አስከፋኝ። ወዲያዉ በተኛበት ጉንጩን ስሜዉ ሻወር
148
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ቤት ሄጄ አለቀስኩ...ጭኖቼ ላይ የደረቀ ደሜን በሙቅ ሻወር
ፈትጌ አስለቀቅኩት።
በሩ በኃይል ይንኳኳል...ጓደኞቹ "ዘማህ ተነሱ" ይላሉ
እሱ በተኛበት "አቦ ተዉና... ምድረ የተሰለቻቼሽ ኹላ"
ይላል
እኔ የሱን
ተቀምጫለኹ።
መነሳት
እየተጠባበቅኹ
ወንበር
ላይ
149
| ናትናኤል ዳኛው
የእግዜር ቀጭን ክር
ተያያዥነት ከየት ወዴት?
መላክ ዓለም(ረ/ፕሮፌሰር)
ከአሜሪካ፣ ማንሃተን ዩኒቨርሲቲ
ዓላማየ ኹለት ነበር ተሳክቶልኝ እሷን የማገባ ከኾነ አሪፍ
አባወራ ለመኾን ካልተሳካልኝ ግን ሙልጭ ብየ በህልሜ
ለመጥፋት። አልተሳካም... ዛሬ ይኼዉ በባዕድ ሀገር ከዝንጀሮ
ልጆች ጋር በማላምንበት ቋንቋ ስግባባ እኖራኹ።
ፊዚስት መኾን ነበር ህልሜ...የእሷ የባዮሎጅ ፍቅር ግን
ባዮሎጅን እንደመረምር አደረገኝ... ነፍሱን ይማረዉና ዛሬ
ድረስ ባልገባኝ ኹኔታ ባልጎ እስኪገኝ ድረስ ጋሽ ዲበ ባዮሎጅን
ሲያስተምር ያጓጓ ነበር። የዛን ጊዜ ጥቁር ሰሌዳ ላይ ሲፅፈዉ
ባይገባንም ልቤ ላይ ገልብጭ ይዤዉ ዩኒቨርስቲ ከገባን በኋላ
የተረዳኹት... በየአንዳንዱ የህይወት ነጠላ ሰበብና ዉጤት ሳጣ
የገባኝ..."ኹሉም ነገር የተያያዘ ነዉ" ...ፍልስፍናዉ ...ዛሬ ድረስ
ለኔ የስነ-ህይወት ምርምሮች መነሻ ይኼዉ የ'ሱ ሃሳብ ነዉ።
ፍፁም የተለያዩ የሚመስሉት ባዮሎጅና ፊዚክስ በተፈጥሮ
150
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በኩል እንደሚገናኙ ያሳየኝ ድንቅ መምህሬ ነበር። ኹልጊዜ
ከጥናት ፅሁፎቼ መግቢያ ላይ የማስቀምጠዉ በቅርቡም
ሊወጣም የህትመት ወረፋዉን እየጠበቀ ያለ መፅሃፌ
"የተፈጥሮ ስነ ህይወታዊና ፊዚካዊ የተያያዥነት ምስጢር"
መነሻ ሀሳብና መግቢያ ጥቅስ ያደረኩትም የእሱን አባባል
ነዉ።
"እንዲህ ገዝፈን ብንታይም መሰረታችን ግን ዶት* ናት።
የሚያኮራ የተለየ ነገር የለንም። በዶት ችብታ እንደቆምን
በቅንጣጢት ዶት መታወክ እንወድቃለን። እንኳን ሰዉና ሰዉ
ዩኒቨርሱም በመያያዝ አዙሪት የቆመ ነዉ።"
ይች ሳሊሌን ደፈረ ተብሎ ከመታሰሩ አንድ ቀን በፊት
ጥቁር ሰሌዳ ላይ አስፍሯት የወጣ ፅሁፉ ለዓመታት እንቆቅልሽ
ኾነችብኝ። ልጠይቀዉ እፈልግ ነበር..."ዶቷ ምንድን ናት?"
ብየ... "ክርስትናችንስ የሰዉ ልጅ ከአፈር ነዉ የተበጀዉ የሚለን
ሀሰት ነዉን?" ልለዉ እፈልግ ነበር።
ባልተጠበቀ ድርጊቱ ያዘነ ተማሪና መምህር ኹሉ
ለሳምንት ት/ቤቱን አኮረፈ... የሳሊሌን መሰበር ያየኹ እኔ
ለኹሉም ነገር ተስፋ አጣኹ። ሳሊል ጋር ለአንድ ወር
አልተያየንም... የፍቅሬ ፅናት የተገለጠልኝ በዛ ጊዜ
ነዉ...የደበቁኝ ቤተሰቦቿ ጋር እየኼድኩ ማልቀስ ኾነ
ስራየ...በኋላ ነዉ አያቷ "ልጄ ያንተ አይነት ጓደኛ ስላላት
ፈጣሪየን አመሰገንኩት። ላንተ ያለችበትን ብደብቅ ይቅር
151
| ናትናኤል ዳኛው
አልባልምና ሳሌ ትንሽ ዘወር ትበል ብለን አክስቷ ዘንድ
ማርዓምባ ልከናት ነዉ" አሉኝ
"መቼ ትመለሳለች እመ ዉዳሴ?"
"እንጃ ፅናቷን አይተን ነዉ እንጂ ልጄ??"
በዚህ ኹኔታ የእሷን መምጣት እየተጠባበኩ እያለ ጋሽ
ዲበ እስር ቤት እያለ ራሱን ገደለ። ት/ቤቱ እንደ ገና ተረበሼ።
...የሳሊሌን ህልም መቀማቱ ያበሳጨኝ ሰዉየ ባገኘዉ ልገለዉ
የተመኘኹት መምህሬ የሞቱን ዜና ስሰማ አመመኝ። ብዙ
የሚተርፈዉ ዕዉቀት የነበረዉ ተራተርታ ስለሚከፈለዉና
ወረቀት ስላለዉ ብቻ ላስተምር የሚል አልነበረም. ..ጥንቅቅ
ያለ ነበር። ፊዚኦሎጅየን ጠንቅቄ ያወቅኩና የተረዳኹት በ'ሱ
ግፊት ነበር።..በሃይስኩል አእምሮ የተራራቁ የሚመስሉንን ስነህይዎትና ፊዚካ ቀጭን መስመር ፈጥሮ ዉህደታቼዉን ያሳየኝ
የዕዉቀት መሪየ ነበር ጋሽ ዲበ... ሳሊሌ በነበራት የባዮሎጅ
ፍቅር ይወዳት ነበር...ታላቅ ወንድሟ ነበር የሚመስለዉ...
ሌላዉ ጋር አበዛሽዉ የምላት ግልፅነቷ እሱ ጋር ልክ ይመስለኝ
ነበር...ግን ምክንያቱን ባላዉቅም ተሳስቶ አገኘኹት። ዛሬ ድረስ
ለምን? የሚለዉ አልተመለሰልኝም ሳሊሌም "በቃ እርሳዉ"
ከማለት ያለፈ ምንም አልነገረችኝም።
...የጋሽ ዲበን ሬሳ ከእስር ቤት ተቀብለን ቤቱ ልናደርስ
ተማሪዎች ኹሉ ተሰልፈን ሄድን ወዲያዉ ፖሊሶቹ በእሱ እጂ
የተፃፉ ኹለት ወረቀቶች አግኝተናል ብለዉ "አንዱን
152
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ለቤተሰቦቹ፡አንዱ ደግሞ ለተማሪየ መላክ" ነዉ የሚለዉ
ብለዉ ሰጡን።
ቀኑ ረዝሞብኝ ነበር...ለ'ኔ ሊፅፍልኝ የሚችልበት ምክንያት
አልገለጥልህ ቢለኝ ደብዳቤዉን ለማንበብ ጓጓኹ። ምን
ያደርጋል ነገሩ ኹሉ ተረጋግቶ እኛም መደበኛ ት/ታችንን
በጀመርንበት ወቅት ራሱን ገድሎ ተገኜ። እስር ቤቱ ራሱን
ከተጠያቂነት ለማዳን ወይንም እሱ ማድረግ ችሎ ባላዉቅም
"በጥርሱ የደም ስሩን በጥሶ ነዉ ራሱን ያጠፋዉ" አሉ።
ሬሳዉን ከወላጆቹ ቤት እንዳደረስን በሰልፍ የመጣዉ
ተማሪ ወደ ቤቱ መበተን ሲጀምር እኔም ተቀላቅየ ሄድኩ።
ችኮላየ ደብዳቤዉን ገልጦ ለማንበብ ነበር...ቤት ስሄድ እትና
አባቴ ወደ ለቅሶዉ ሂደዉ ታናሽ እህቴን ከሰራተኛዋ ጋር በረንዳ
ላይ አገኘኋቸዉ። እነሱ እዛዉ በረንዳ ላይ ትቼ ቀጥታ ወደ
ክፍሌ አመራኹ። ቦርሳየን አልጋየ ላይ ወርዉሬ፡ አጣጥፌ ኪሴ
ዉስጥ ያስቀመጥኳትን ደብዳቤ አዉጥቼ የጥናት ወንበሬ ላይ
ዘፍ ብየ ተቀምጨ ማንበብ ጀመርኩ
ከዲበጊዜ ድልነሳ
እስር ቤት
ለተማሪዬ መላክ
መቼስ ያንተ ዓይነት ተማሪ ከስንት አንድ እንደሚገኝ
እንጃ?
153
| ናትናኤል ዳኛው
ምን ይኾናል እኔ ከንቱ ያንተን ጉዞ ለማየት አልታደልኩ።
ጥሩ መምህር ለመኾን የመጣሬ ምክንያቴ ያንተና የሳሊል
ዓይነት ተማሪዎች ናችኹ። ነጋችኹ ያሳሳኝ ነበር። የሳሊል
የባዮሎጅ ፍቅር ያንተ ፊዚክስን ጠልቆ የማወቅ ጉጉት ነበር
ያለረፍት አዲስ ነገር እንዳስስ ምክንያቴ ይኼ አንተ ደጋግመህ
በጥልቅ እንዳስረዳህ የምትጠይቀኝ የ "ተያያዥነት" ፅንሰ ሃሳብ
አንዱ ማሳያ ነዉ። 'ርቄ ልሄድበት ዝግጅት ላይ ነበርኩ። አንድ
ኹለት ወረቀቶችም ቤቴ አሉ መነሻ ሀሳብ እንዲኾኑኝ
የፃፍኳቸዉ። ዛሬ ከሞቴ አንድ ቀን ቀደም ብየ ይህን
የምፅፍልህ በኹለት ምክንያት ነዉ።
1ኛ፡የሳሊልን ህልም ብቻ አላጨለምኩም። የአንተንና
የራሴንም ጭምር እንጂ። ሳሊልን ምን ያህል እንደምትወዳት
አዉቃለኹ የአስተማሪነት መስመሬ ስለማይፈቅድ እንጂ
ያልጠየቅኳችኹ። እሷን ስሰብር ሀገሬ ሰብሪያለኹ።...ገለባ
ስሜቴን መገዳደር አቅቶኝ እሷን ስደፍር እናቴን እህቶቼን
ደፍሪያለኹ። እሷ ላይ ስባልግ ተምሬ ያስተማርኩበት ት/ቤቴን
ጥላሸት ቀብቻለኹ። ለ'ኔ ከሞት የተሻለ ቅጣት የለም።
ከሳምንት በፊት ብልቴን ልቀጠቅጥ ስታገል ሌሎች እስረኞችና
ፖሊሶቹ ታግለዉ አስተዉኝ ሃኪም ቤት ወስደዉኝም "ቫን ጎህ
ሲንድረም" ነዉ የሚባለዉ የእንዲህ ዓይነቱ ገጠመኝ ብለዉ
የክኒን መዓት አሸክመዉ መለሱኝ። በደህና ጊዜዉ ቢኾን
ስለቫን ጎህ ብዙ ባወራዉህ ነበር። ግን አዉቃለኹ ጥቂት
154
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ከአቀበሉህ ብዙ እንደምትቆፍርና አላስብም።...በራሴ
ማፈሬን...ከራሴም መቃቃሬን እወቅ ስልህ ነዉ።
2ኛ፡ለሳሊል ((ስሟን ስጠራዉ እንኳ አፌ በደም ይሞላል))
ብፅፍላት ልታነበዉ ቀርቶ ከእጇ እንኳ እንደማይደርስ
ይገባኛል። "ይቅር በይኝ" ልላት አይደለም... ያፋፋኹትን
ህልሟን በመርፌ እንደቀላል ያፈነዳኹ እኔን በየት በኩል ይቅር
ትለኛለች?... ድፍረቱም የለኝም። ለአንተ ግን ለእኔ እንጥፍጣፊ
ክብር ከቀረችህ አደራ የምልህ ነገሮች አሉኝ። ከሳሊል ምላሽ
ሳትጠብቅ የቻልከዉን ኹሉ እንድትሰጣት ልለምንህ ነዉ።...
ጥፋቴን እንድታርምልኝ ተስፋ እማደርገዉ አንተን ነዉ።
እርግጠኛ ባልኾንም ኹሉም በማላዉቀዉ ምክንያት በቅፅበት
የኾነ ነዉና አርግዛ ሊኾን እንደሚችል እጠረጥራለኹ...
አጣርተህ እስክትነግረኝ የምጠብቅበት ጊዜ የለም...ከዚህ በኋላ
ምድር ላይ የመቆየት መብትም የለኝም። ከኾነ ግን ፅንሰቷ ከኔ
ሳይኾን ካንተ ነዉ። ከስጋ ሞቴ በኋላ አንተ ዉስጥ ነዉ
የምኖረዉ።
ልጄ ባንተ ስም እንዲጠራ/እንድትጠራ ነዉ የምፈልገዉ።
ከዚህ ከኔ ቅሌት በኋላ ለ'ሷ ያለህ ነገር እንደማይቀንስ
አዉቃለኹ... የልብህ ክብደት ይገባኛል።
በተረፈ የአንተ መምህር
የጀመርኩትን የተሻለ ቦታ
መኾኔ ያኮራኛል። እኔ
ላይ ኾነህ ጠልቀህ
155
| ናትናኤል ዳኛው
እንደምታጠናዉና ለፍሬ እንደምታበቃዉ አምናለኹ። የመነሻ
ሀሳብ እንዲኾንህ ያልኩህን ወረቀቶች እህቴ ትሰጥሃለች።
ሳሊልን አበርታት... "ለሰባሪሽ አትሸነፊለት" ብለህ
አፅናት...ሳወራልህ የነበረዉን ፈላስፋ ንጉስ ታስታዉሰዋለህ?
ኦረሊየስ የምልህ? መፅሃፉን ከወረቀቱ ጋር እህቴ ትሰጥሃለች
ከፍ እያልክ ስትሄድ በደንብ ታነበዋለህ ብየ አስባለኹ።
...በመጨረሻ ከቻልክ የሶስታችንንም አልያ የአንተን ህልም
እዳር ማድረስን ችላ እንዳትል።
ሰላም ለምድርና ምድራውያን።
አክባሪህ
ፊርማ
ደጋግሜ አነበበኩት... ማልቀስ አምሮኝ ነበር። ተነስቼ
እንጎራደድና ተመልሼ ተቀምጨ ደግሞ አነበዋለኹ... ሳሊልን
ካየኋት ኹለት ወር ሊኾን ነዉ። ብዙ ተስፋ ያደረኩበት
መምህሬ...ከፊቴ አስቀምጨ ልደርስበት የምጓጓ መምህሬ
ሞተ። አንዲት ቅፅበት በህይወታችን ይህን ግዙፍ ልዩነት
ስትፈጥር አየኹ። ተከዝኩ...ሽርፍራፊ ስህተት የካበዉን
የናደችበት... ህልሙ፡ተስፋዉ በቅንጣት ስህተት እንደ ኩይሳ
የተናደበት ብዙ ሰዉ መኖሩን አስቤ ተከዝኩ።
156
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ዩኒፎርሜን እንዳደረኩ ምግብ እንኳ ሳያምረኝ አልጋየ ላይ
እግሬን አጥፌ ጥቅልል ብየ ተኛኹ።
ቀን 7:00 የክፍሌ አልጋ ላይ የተኛኹ ሰዉ በሚቀጥለዉ
ቀን 10:00 ሰዓት ራሴን በሰዎች ተከብቤ የሆስፒታል አልጋ ላይ
ተኝቼ አገኘኹት። ከጎኔ ወላጆቼ ነበሩ። ታናሽ እህቴ መሃላቼዉ
ላይ እንባ በእንባ ኾና አየኋት። የሃዘን ልብስ የለበሱ
መምህራኖቼ በዙሪያቸዉ አሉ... ዓይኔን ማመን ያቃተዉ ግን
ሳሊልን ከእናቷና አያቷ ጋር ከጎኔ ቆማ ሳገኛት ነዉ። አንገቱ ላይ
ስቴቶስኮፕ ያንጠለጠል ነጭ ጋወን የለበሰ መላጣ ዶክተር
በመገረም እያየኝ አገኘኹት። መንቃቴን እየተጠባበቁ እንደኾነ
ገብቶኛል...እናቴ በጉጉት ታየኛለች ወዲያዉ አንገቴ ስር ገብታ
ማልቀስ ጀመረች...ትንፋሿ ያቃጥላል...ምግብ እንዳልበላችና
እንደደከማት ታስታዉቃለች። አባቴ እጄን ጨብጦ ጉንጨን
ሳመኝ...እህቴ ታለቅሳለች...ሳሊል ሮጣ ሄዳ ስታባብላት አየኹ።
ሀኪሙ ለአባቴ "ትንሽ ይረፍ...ግሉኮሱን ስለጨረሰ አባብላችኹ
የሚበላ ስጡት" ሲለዉ ሰማኹት...ወደ'ኔ ዙሮ "ጎረምሳዉ
እንዳታስቸግር እሽ" ብሎኝ ወጣ ።...ምን እንደኾንኩ
አላስታዉስም ስለደከመኝና ስለከፋኝ መተኛቴ ብቻ ነዉ ትዝ
የሚለኝ።
እናቴ ትቅበጠበጣለች... መምህራኖቼ በየተራ እየቀረቡ
አይዞህ አሉኝ። ሴቶቹ ግንባሬን ሳሙኝ።
157
| ናትናኤል ዳኛው
የሳሊል እናት ኹሉም ከተረጋጋ በኋላ ቀርበዉ "ምነዉ
ልጄ?...አስደነገጥከን እኮ" አሉኝ
እመ ዉዳሴ ከርቀት ኾነዉ በስስት ያዩኛል። ሳሊል ግን
ልትቀርበኝም ኾነ ዐይኔን ልታይ አልፈቀደችም ሳያት
ትሸሸኛለች።
ከእናቴ ጋር የኾነ ነገር ከተነጋገሩ በኋላ ከእናትና አያቷ ጋር
ተያይዘዉ ወጡ...እያየኋት አነባ ነበር...ወዲያዉ እናቴ በጆሮየ
ቀርባ "አንተ ጅል አፍቃሪ ትመለሳለች እኮ" አለችኝ በሃፍረት
አይኔን ጨፈንኩ።
ኹለት ቀን እዛዉ ሆስፒታል ቆየኹ...አባቴና ሳሊሌ ማታ
እናቴና እህቴ ደግሞ ቀን በፈረቃ አብረዉኝ ይኾናሉ። ሳሊሌ
ቶሎ ቶሎ ሲደክማት አያት ነበር...አባቴ "እኔ እበቃለኹ"
ቢላትም እሽ አልል አለች። እያስገደደች ትመግበኛለች።
ቤቴ ስመለስ ከምትሰማኝ ድካም በቀር ደህና ነበርኩ።
ቤት ከገባኹ በኋላ ስለኾንኩት ነገር እናቴን ስጠይቃት "ከለቅሶ
ስንመለስ ተኝተህ ነበር። ደክሞት ነዉ ይረፍ ብለን ተዉንህ...
ማታ ግን ራት እንድትበላ ሰራተኛዋ ልትቀሰቅስህ ብትመጣ
በላብ ተዘፍቅህ አገኜችህ 'አረ እትየ አሞታል መሰለኝ
ይንቀጠቀጣል' አለችን መጥታ ተደናግጠን ስንመጣ ራስክን
ስተህ አገኘንህ" አለችኝ
"ታዲያ ዶክተሩ ምን አለ?"
158
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"ድካምና ጭንቀት ነዉ ብሎ በአንድ ቀን ስንት ግሉኮስ
እንደወስድክ እኮ!!"
"እሽ ሳሊልስ?"
"ተደብቃ ነዉ እንጂ ከመጣች ሰንብታለች አሉ...አቤት
ታመመ ሲባል የኾነችዉ...የኔ ቆንጆ"
...የኾነባት... የኾነብን ቢከብድም ከእኔ እንኳ ለመደበቅ
መሞከሯ አሳዘነኝ። ይህን ፍራቻ ይመስለኛል... እንድናወራ
አትፈልግም። ላዋራት ስጀምር "ይደክምሃል፤ ስትድን
እናወራለን" ትለኛለች
እየተሻለኝ መንቃትና መንቀሳቀስ ስጀምር መጥፋት
ጀመረች። ከሳምንት በኋላ ጭራሽ "ተመልሳ ወደ ማርዓምባ
ሄዳለች" አለችኝ እናቴ..."እርግጠኛ ነሽ ቤቷ አልተደበቀችም"
ብላትም
"እኔ ነኝ የሸኜኋት ይልቅ ይህን ወረቀት ስጭልኝ ብላለች"
ብላ በእጂ የታሸች ወረቀት አቀበለችኝ
"ብዙ ጥያቄ እንዳለህ አዉቃለኹ፡እኔም ብዙ ላወራህ
የምፈልገዉ ነገር አለኝ። ጊዜዉ ግን አልፈቀደልንም።"
እህትህ ሳሊል
159
| ናትናኤል ዳኛው
እናቴ ፊት ላይ ወረቀቷን ቆራርጨ ጣልኳት። ለረዥም
ሰዓት እዛዉ ሶፋ ላይ ተቀምጨ ተከዝኩ...ማርዓምባ መሄድ
አለብኝ አልኩ። ቀጥታ ወደ ክፍሌም ሂጄ የሳንቲም
ማጠራቀሚያ ሳጥኔን በርብሬ ሂሳብ ማስላት ጀመርኩ። ከዚህ
ማርዓምባ ምን ያህል እንደሚርቅ አላዉቅም። የእሷ አክስት
የት ቀበሌ ምን ሰፈር እንደምትኖር አላዉቅም። በቅድሚያ
እነዚህን ማጣራት እንዳለብኝ ወሰንኩ።
ይኼን ላጣራ በምሞክርበት ጊዜ ግን ሳሊል አርግዛለች
የሚል ወሬ በሰፈሩ ተዘርቶ እኔም ጋ ደረሰ። እንደሰማኹ ቀጥታ
የሮጥኩት ወደ'ናቴ ነዉ። ቤት ስገባ ግን ቡና ተፈልቶ የሳሊል
እናትንም ከናቴ ጎን ተቀምጣ አገኘኋቸዉ። ፊትለፊታቸዉ
ተቀምጨ እማየን ጥያቄ በተሞላ ፊት አየኋት። ደንግጣ
"ምነዉ?" አለችኝ
"እዉነት ነዉ?“ አልኳቸዉ ኹለቱን እያፈራረቅኩ እያየኹ
የሳሊል እናት ጥያቄ ገብቷቸዉ አንገታቸዉ ሰበሩ። እማየ
ተነስታ እጄን ይዛ ወደ ክፍሌ ወሰደችኝ... እንደገባንም "ቀስ
በል...እስከምትሰማ እየጠበቅን ነበር። እሷንም ከኹሉ
ያስጨነቃት ያንተ ነገር ነበር። ተመካክረን ነዉ አክስቷ
የእርግዘና ጊዜዋን ጨርሳ እንድትመጣ የላክናት"
"ያረገዘችዉ ለ'ኔ ነዉ" አልኳት
"ምን?" ብላ ደነገጠች
160
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ተነስቼ መሳቢያ ዉስጥ ያስቀመጥኩትን የጋሽ ዲበን
ደብዳቤ አዉጥቼ ሰጠኋት
ራሷን እየነቀነቀች አንዳንድ ጊዜም ምፅ እያለች አንብባ
ከጨረሰች በኋላ
"ገባኝ" አለችኝ
ቀጥላም "በጣም ጥሩ...ስለዚህ ታግዘናለህ ማለት ነዉ?"
"ምኑን?"
"ስንጨነቀ የነበረዉ እኮ አንተስ ማርገዟን ስትሰማ
ምንትኾንብን የሚለዉ ነዉ... አንተ አንድ ነገር ብትኾንብኝ
ደግሞ እኔ አልተርፍም... ምን መዓት ወረደብን እያልኩ ነዉ
የማነባዉ እኮ...እግዚአብሔር ይስጠዉ ይችን ደብዳቤ ፅፎ
ከሌላ ጥፋት ታድጎናል።...ሳሊልን ወደ አቅሟ መመለስ ካለብን
አንተ ጠንክረህ ወደ ት/ትህ መመለስ አለብህ። ከዛ ልጇን
ከወለደች በኋላ ደግሞ እኔና እናቷ እናሳድግላታለን... እሷ
ት/ቷን ትቀጥላለች።"
እዛዉ የኔንም የሳሊልን እና የጋሽ ዲበን ህልም እንደምኖር
ቃል ገብቼ አቀፍኳት። እያለቀሰች ጭምቅምቅ አድርጋ አቅፋ
አንገቴ እስኪረጥብ ሳመችኝ። እኔ እዛዉ ክፍሌ ኾኜ ቀጥሎ
ለማደርገዉ ነገር ያሰብኩ የሳሊል እናት ደጋግመዉ "ተመስገን!
ተመስገን!” ሲሉ እሰማቼዋለኹ
161
| ናትናኤል ዳኛው
የጋሽ ዲበን ወረቀት ከእህቱ ተቀብየ ላጠናዉ ሞከርኩ።
እንዳለዉ መነሻ ብሎ እሱ በሚገባዉ መልኩ ስላሰፈረዉ ቀላል
አልኾንልህ አለኝ። አንድ የተረዳኋት ነጥብ ግን የመጨረሻ
የጥቁር ሰሌዳ ፅሁፉ ላይ ዶት ያላት አቶም መኾኗ ነዉ። ከዚች
ነጥብ ተነስቼ ስለ ሰዉ...ስለ ከዋክብት... ስለእፅዋት...
ስለአፈር። ስለዩኒቨርስ አፈጣ ጠርም ከሃይማኖትና ከሳይንስ
አንፃናር ማጥናት እንደሚኖርብኝ ገባኝ። ነገር ግን በአለኝ
የግንዛቤ አቅምና የማጣቀሻ ምንጭ አናሳ መኾን በዛ ላይ
ደግሞ ሙሉ ትኩረቴን ወደ ዚህ ካደረኩ ት/ቴ እንደሚጎዳ
ገባኝ። ስለዚህ ብየ ኹሉንም ነገር በጊዜ ሂደት ለማጥናት
አስቀመጥኩት። በየአጋጣሚዉ ወደ'ሱ የሚመሩኝን
ከማንኛዉም ምንጭ ሳገኝ ግን ለማሰላሰያነት እየመዘ ገብኩ
አስቀምጣቸዉ ነበር።1
ኹሉም ነገር ከዶት ክምችት የተሰራ ነዉ ብለን መጀመር እንችላለን።
እያንዳንዷ ዶት ደግሞ በብዙ ክፍልፋይ ዩኒቶች የተዋቀረች ናት።
1
ይች ዶት አቶም ናት ብለን ብንነሳ። እያንዳንዱ አቶም ደግሞ በዉስጥ ፕሮቶን፡
ኒዉትሮንና ኤሌክትሮን ከሚሉ ቅንጣጢቶች የተዋቀረ ነዉ። እነዚህ
ቅንጣጢቶች ደግሞ ከነሱ ወዳነሱ ክፍሎች ይከፋፈላሉ። ኳንተም ፊዚክስ
ዩኒቨርሳችን ስለምትፈጥራት እጅግ አናሳ ነገር የሚያጠና ሳይንስ ነዉ።
ስነ-ህይወት የሰዉ ልጅ የተዋቀረባት ትንሿ ክፍል ሴል እንደምትባል ይነግረናል።
የእያንዳንዱ ሰዉ አካል ዉስጥ ትሪሊየን ያህል ሴሎች አሉ። እያንዳንዷ ሴል
ዉስጥ ደግሞ ቢሊየን ያህል አቶሞች ይገኛሉ።
162
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የጥናታችን ዋና ትኩረት ወደ እነዚህ አቶሞች ያደላ ነዉ። የኹሉም ነገር
መሰረትና መያያዝ ምክንያት እነሱ ናቸዉና::
አቶም
አቶም ከሶስት መሰረታዊ ነገሮች የተዋቀረ ነዉ። ኒዉትሮን (0), ፕሮቶን (+) እና
ኤሌክትሮን (-)…
እነዚህ ሶስት ነገሮች ደግሞ በተለያየ መጠን እያንዳንዱ ኤለመንት ዉስጥ
ይገኛሉ። ከእንስሳት እና እፅዋት ሴል ጀምሮ አፅናፍ ላይ እስከተዘሩት ከዋክብት
ድረስ።
ልብ
ልብ ሄሞግሎቢን አለዉ።ሄሞግሎቢን በዉስጡ ብረት (Fe) ይይዛል። ይኼ
ብረት ደግሞ በሱፐር ኖቫ መሰረት ከሞቱ ኮከቦች የተገኘ ነዉ። ይህ ብረት
በዉስጡ ኤሌክትሮን፣ ኒዉትሮንና ፕሮቶን አለዉ። እነዚህ ራሳቼዉ ወደ
ጥቃቅን ኳርክስ ይከፋፈላሉ።
ስርዓተ ትንፈሳ
163
| ናትናኤል ዳኛው
ህይወት ያለዉ ነገር በህይወት ለመቆየት መተንፈስ አለበት። ሲተነፍስ
የተቃጠለ አየር CO2 ወደ ዉጭ ያስወጣል። ያን co2 እፅዋት ለምግብ
መስሪያነት ይጠቀሙታል። መልሰዉ ግን በፎቶ ሴንቴሲስ ተረፈ ምርት (by
product) ብለዉ የሚለቁትን ዐ2 የሰዉ ልጅ ህልዉናዉን ለማቆየት
ይጠቀመዋል። ፉድ ቼይን የምግብ ሰንሰለት ነዉ። አንዱ ሌላዉን የመመገብ
ሂደት የሚያሳይ። የሞራል ጥያቄ ዉስጥ ገብቼ ለምን? አልልም። ተፈጥሮ ሂደት
ናትና...ቁምነገሬ ሂደቷን እንዴት? ብሎ ማጥናት ነዉ። እንስሳት እፅዋት በል፣
ስጋ በልና ኹለበል ተብለዉ ይከፈላሉ። አንዱ ሌላዉን ይመገባል።
እፅዋት->እ እፅዋት በል እንስሳ->ሰዉ የሚመገበዉ እንስሳ ማለት ወይም
እፅዋት-> እፅዋት በል እንስሳ
እፅዋት-> ሰዉ
ለስርዓተ ትንፈሳ መሰረቱ ኦክስጅን ነዉ። ኦክስጅን መሰረታዊ መገኛዉ የት
ነዉ? ጥያቄ
ከእፅዋት በፊት አፈር አለ...አፈር ከእፅዋትና እንስሳት ብስባሽ አልያ ከሞቱ
ከዋክብት ይገኛል። ይኼ ማለት እነዚህ የነበራቸዉን ኤለመንቶች ይዟል ማለት
ነዉ።
የኹሉም ኤለመንቶች መሰረት አቶሞች ከኾኑ ኹሉም ፍጥረታት እዛች
ነጥብ/ዶት ላይ ይገናኛሉ።...ለዚህ ነዉ በዶት ችብታ የቆምን ነን የምለዉ። ለዚህ
መፅሃፋችንንም አስቀድሞ ዶት ነበረ። ያም ዶት አቶም ነበረ። ብለን
እንጀምራለን።
ለሰዉ ልጅ ህመም የአንዲት ሴል መታወክ በቂ ናት። ለአንዲት ሴል መመረዝ
ደግሞ የአንዲት አቶም ስርዓት መሳት ይበቃል።
164
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ስለ ስጋ ዘላለማዊነት
ሰዉ ሲሞት ይቀበራል አልያ ይቃጠላል። ስለሚቀበረዉ እናዉራ...የተፈጥሮ
ሂደቱን የጠበቀ እሱ ነዉና። ብስበሳ(decomposition) በአጋፋሪ ምስጥ
አማካይነት የሚካሄድ ነዉ። የሂደቱን ዉጤቱ መሰረት አድርገን
metamorphosis ልንለዉ እንችላለን። የቅርፅ ልዉጠት ነዉና የሚያካሂደዉ።
ከእንስሳነት ወደ እፅዋትነት መልሶ ወደ እንስሳነት አልያም ወደ ሌላ። የዚህ ሂደት
ዋና ባለቤት ምስጥ ናት። አካሉን ዲኮምፖዝ ታደርገዋለች። ያ ዲኮምፖዝድ
አካል ጊዜዉን ጠብቆ ወደ አፈርነት ይቀየራል። ያ አፈር ለእፅዋት ምግብነት
ይዉላል...በሌላ ሂደት አልፎ እፅዋት ኾኖ ይወለዳል። ቀደም ብለን ባወራነዉ
የፉድ ቼይን መሰረት ይኼ እፅዋት የተበይነት ተግባሩን ፈፅሞ ሌላ አካል ኾኖ
ያድጋል በዚህ የሞትና የትንሳኤ ሂደት እያለፈ ዘላለማዊ ይኾናል ማለት ነዉ።
አንድ ነገር ቅርፁን ለዉጧል ማለት የለም ማለት ላይኾን ይችላል።
(...)
በአቶም በሞለኪዩል ታንፆ ተሰርቶ
በተበተነ አካል ህይወት ተመስርቶ
ህይወት ተጎናፅፎ ሞለኪዩል ተሰራ
አልፋ ኦሜጋ ነዉ ፍጥረት ያንች ስራ
ለብዙ አይነት ህያዉት ግባት አበርክቶ
የአልፋ ኦሜጋነት ድርሻዉን ተወጥቶ
ይከሰት ይኾናል?
ማን ያዉቃል?
165
| ናትናኤል ዳኛው
~
* ~
ከሰባት ወር በኋላ ሳሊል ሴት ልጅ ወለደች።... እንደ
አባወራ ጠብ'ርግፍ ብየ አገለገልኳት። እንደሷዉ የምታበራ
የሶረኔ ላባ፡የመስቀል አበባ
ወይም ቅማል፡ትኋን፡ወይም ግዙፍ ዱባ።
<<ህይወት>> <<አልባ ህይወት>> ያንድ አካል ገፅታ
ኹሌም መፈራረቅ አንዱ ባንዱ ቦታ።
ዘላለም በተርታ
ያለምንም ፋታ
ምንም ሳይገታ።
...
ሞተ ማለት ይቅር፡ይባል ተቀየረ፡
ከወዲያ የመጣ፡እዚህ የነበረ፡
ከአንዱ አካል ሌላ አካል የተመነዘረ
ምንግዜም የሚኖር፡ ኹሌም የነበረ። *
*ሽብሩ ተድላ/ ከስንኝ ማሰሮ
166
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በዉበት የተከበበች ልጅ ነበረች። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ልጄ እላት
ጀመር።
ዩኒቨርስቲ እየተማርኩ እያለ ሳሊል በአካዉንቲንግ
ዲፕሎማ ተመርቃ ስራ ያዘች። ልጇንም ራሴ አሳድጋለኹ ብላ
ከእናቷ ወደ ራሷ ቤት ወሰደቻት።
ተመርቄ እንደወጣኹ ላገባት ብፈልግም እሷ "አይኾንም"
አለች...እናቴ አዘነችባት። በመኃል አስታራቂ ኾኜ ልገባ
ብፈልግም የእናቴን ቅያሜ ማሸነፍ አቃተኝ። በወሬ ወሬ
"መላኬን ከወንድሜ ዉጭ ባዳ አድርጌ አስቤ ላርቀዉ
አልፈልግም። ለልጄ አባት ለ'ኔ ወንድሜ ነዉ" አለች ተብሎ
እጆሮየ ደረሰ
የእማዬን ቅያሜ ላስተርፍላት ብሞክርም እኔ ግን ተጎድቼ
ነበር። የተጎደኹት አላገባህም
ስላለችኝ ሳይኾን "እጮኛ አለኝ ብየ የገፋኋት ሌላ ሴት
መኖሯ ነበር።"
ከእሷ ጋር እየኖርኩ በሀገሬ እማራለኹ ብየ የተዉኩትን
የዉጭ ት/ት እንደገና ማፈላለግ ጀመርኩ። እየደወለች
ታለቅሳለች..."ለምን
ትኼዳለህ?...ለምን
እዚህ
አትማርም?...እትየስ?...እኔን ብትተወኝ ልጅህስ?" ትለኛለች
አስቀድሞ የነበረኝ ኹለት ምርጫ
ማግባት...አልያ ት/ቴን እጫፍ ማድረስ።
ነዉ...አንቺን
167
| ናትናኤል ዳኛው
ያንችና የኔ ጉዳዬ አብቅቷል...አልኾነም ከእንግዲህም
አይኾንም...ለልጄና ለእናቴ የትም ብኾን አያጡኝም...ልባቸዉ
ዉስጥ አለኹ።" ብየ በህይወቷ ለሚገጥማት ዉጣ ዉረድ
አጋዥ ይኾታል በሚል የምወደዉን መፅሃፌን ሜዲቴሽንስ
ሰጥቼ ተሰናበትኳት።
ልጄ ዛሬ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ናት። በመኃል የእማየን ሞት
ተረድቼ የሄድኩ ጊዜ ተገናኝተናል። አንድ ነገር እንዳይጎድልባት
አድርጌ ነዉ ያሳደኳት። ሳሊል ከሰዉ የምትጠብቅ ሴት
አይደለችም...ለመቆም ደጋፊ አልሻም ትላለች...ረስተዋለች
የጋሽ ዲበ የቅፅበት ስህተት በተያያዥነታችን ስንታችንን
ልታፈርሰን እንደነበር። እህቴ "እማዬን እንዳስቀየምኳት ይቅር
ሳትለኝ" እያለች እንደምታዝን እህቴ በስልክ ደጋግማ
ነግራኛለች።
ልጄ የተረሳ ፍቅር አግላ ድልድይ በመኾን እኔና ሳሊልን
ለማገናኜት ትጥራለች። ግን "ተይ" አልኳት "ከንግዲህ እሽ
ብትል ላንቺ ብላ ነዉ...እሱ ደግሞ ለ'ኔ ቁስል ነዉ...እንዳታጭኝ
ከፈለግሽ ተይ" አልኳት...ሳግ እየተናነቃት እሺ አለች።
የሶስታችንንም ህልም ኖሬ እንዳሳካኹ ይሰማኛል። የጋሽ
ዲበ "መሰረታችን ዶት ናት" ፅንሰ ሃሳብ...ከብዙ ዉጣ ዉረድ
በኋላ...የራቁ ጥንታዊ መዛግብትን በርብሬ... ከሳይንስ…
ፍልስፍናና መንፈሳዊነት አንፃር አጥንቼ 5መቶ ገፆች ያሉት
መፅሃፍ ኾኖ ተዘጋጅቷል።... ከእኔ ጨመርኩት የምለዉ ነገር
168
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ቢኖር እንዲህ ማሰብ ለፍጡራን የተፈጥሮን ሚዛን ጠብቆ
ለመኖርና ከመጠፋፋት እንዴት ሊታደግ እንደሚችል እንደ
ተለዋጭ ወስጄ ያብራራኹበት ምዕራፍ ነዉ።
...ግን ባዶነት ይሰማኛል። ዛሬ ድረስ ሳሊል እንዳጎ ደለችኝ
አስባለኹ።... ሀገሬ ገብቼ ቢያንስ ከጎኗ ኾኜ ዐይኗን እያየኹ
ልኑር እላለኹ።...ሽበት መልቀም ጀምሬም እንደ ጎረምሳ
አፍቃሪ ይቃጣኛል።
169
| ናትናኤል ዳኛው
ምልልሱ
ጋ:- ፈቃደኛ ስለኾንክ አመሰግናለኹ።
ደ:- እሺ
ጋ:- አኹን የሚወጣም ስንተኛ መፅሃፍህ ነዉ?
ደ:- አስራ አንድ መሰለኝ
ጋ:- በምን ያህል ጊዜ ማለት ነዉ?
ደ:- መፃፍ ከጀመርኩ 50 ዓመት ይኾናል። ማሳተም
የጀመርኩት ከ30 ዓመታት ወዲህ ነዉ።
ጋ:- ረዥም ጊዜ ነዉ። እንደአዲስ የመነበብህ ምክንያት
ምን ይመስልሃል?
ደ:- እሱን 'ርግጠኛ መኾን አልችልም። ምናልባት ነፃ
አንባቢ ተፈጥሮ ይኾናል!?
ጋ:- ነፃ ስትል?
ደ:- ያዉ ነፃ ነዋ ማለቴ ወገንተኛ ያልኾነና ከስም የተሻገረ።
ጋ:- የመጀመሪያ መፅሃፍህ "ስም ለማያነቡ" ነዉ
መሰለኝ?
170
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ደ:- አዎ ቀላል እንደማይኾንልኝ ቀድሜም አዉቅ ነበር።
ሀገሬን መች አጣኋት።
ጋ:- እስቲ ስለ ፅሑፍ አጀማመርህ እናዉራ። እንዴት ነበር?
ለምንድን ነዉ የምፅፈዉ ብለህስ ታስባለህ?
ደ:- የምፅፈዉ ህይወቴን ለመተርጎም ነዉ በርግጥ ከዛም
ያለፈ ነገር አለዉ...ልየዉ በሚል በህይወት ከመመራት ይልቅ
መምራት እችል ይኾን? የሚል። በራሷ ስነ-ፅሑፍም ኃይለኛ
ናት...ፈቃደኛና ነፃ ሰዉ ኾኖ የቀረባትን እንደ በርባሮስ ዉጦ
የማስቀረት... ከዛ በኋላ ለሚኾነዉ 'ሳሩን እንጂ ገደሉን መች
አየኹ' እያልክ ከማፏጨት የዘለለ አማራጭ አይኖርህም።
እምልህ መካድ አልችልም። ብዙ chaos ነዉ ያለዉ በሰዉ
አኗኗር ዉስጥ...እሱን የኾነ ፈር(order) ለማሲያዝ የመፃፍን
ያህል አጋዥ ነገር አላየኹም። ሲጀመር መፃፍ የጀመርኩት እንኳ
ፀሐፊነት ስጦታዬ ነዉ ብየ አይደለም... ተማሪ ነዉ የነበርኩት
የምር ተማሪ ወድዶ የሚማር ግን የምማረዉን ከዕዉነታዉ
ጋር ሳነፃፅር ሃሳበ ብዙ እየኾንኩ ለጉርምስና ዕድሜየ የኾነ
ዐይነት ግራ መጋባት፤የኾነ ዐይነት ፈር መፈለግ ይሰማኝ ነበር።
ከዛ በኋላ ነዉ ለብቻዉ የኾነች ማስታወሻ አዘጋጂቼ
የሚሰማኝን የተረዳኹትን መፃፍ የጀመርኩት። እንጂ በቤቴ
ወይም በአካባቢየ የማዉቀዉ የፅሑፍ ጎዳና ይኼነዉ ብሎ
ያሳየኝ የለም። በአካባቢየ ከትምህርትህ ዉጭ መፅሃፍ
መግለጥ ዋልጌነት...ከት/ቤት ዉጭ ደብተርህን ይዘህ መፃፍ
171
| ናትናኤል ዳኛው
አጉል መለክለክ ነዉ። ድህነታችን የወለደዉ ሊሆን ይችላል።
ግን ድንቁርናም አታጣበትም።
በዚህም ምክንያት የምሞነጫጭረዉን ለሌላ ሰዉ
የማሳየት ድፍረቱም ኾነ ፍላጎቱ አልነበረኝም። ሌላዉ ቀርቶ
አኹን ደረስ ወገንተኛ ለኾነ አንባቢ ወይንም ስነ-ፅሑፍን
ያዉቃል ለማልለዉ ሰዉ ፅሑፍ የማንበብ የማስነበብ ወኔዉ
የለኝም። ለ'ንደዚህ ዓይነት ሰዎች ሃሞቴ የፈሰሰ ነዉ...ወዳጆቼ
ቢኾኑ እንኳ ከፅሑፌ ከህትመት በፊት አጠገቡ እንዲደርሱ
አልፈቅድም።
~
* ~
እንዳልኩህ ፅሑፍ ለኔ በዚህ በተዝረከረከ አኗኗራችን
ዉስጥ ከራሴና መንገዴ እንዲኾን ከተለምኩት ፈር
ላለመዉጣት የምጠቀምበት ኃይለኛ መሳሪያየ ናት። በህይወቴ
ደግሞ ከንደዚህ ዓይነቱ መሳሪያ አብልጨ ልወደዉ የምችል
አይኖርም።
ሳጠቃልልህ ወደፅሑፍ የመግባቴም በፅሑፍ ዉስጥ
የመቆየት ምክንያቴም በChaos ዉስጥ Order የመፈለግ
መሻት ነዉ።
ጋ:- ለምንስ ከተለመደዉ በተለየ መልኩ መፃፍን
መረጥክ?
172
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ደ:- የተለመደ ኹሉ ልክ ወይም ብቸኛ አይደለም። ብዙ
ሉዳይት* ፀሃፊያን እና አሳታሚዎች እንዳሉ ጠንቅቄ
አዉቃለኹ። ግን እኔ መስመሩን ሰብሬ የሀገሬ የስነ-ፅሁፍ
መልክ እንዲቀየር መልፋት ነበረብኝ።
ጋ:- አኹን በወጣቱ ጉራማይሌና አዳዲስ የአፃፃፍ ቅርፆችን
እያየን ነዉ።... ከአሳታሚዎች ከባድ ፈተና ይገጥምህ ነበር?
ደ:- ማንሳቱ ስለማይጠቅም እንጂ በጣም ከባድ
ነበር...በተለይ ሻማ ማተሚያ ቤት ለ'ኔ ጥሩ አልነበረም።
ጋ:- "ስም ለማያነቡ" እንዴት ታተመ
ደ:- አንድ ዉጭ የሚኖር ዘመዴ ነዉ ኬንያ ያሳተመልኝ።
ይገርምሃል እስካኹን ብድሩን አልከፈልኩትም።
ጋ:- በጣም ቮራሽየስ* የሚባል አንባቢ መኾንህ
ይነገራል...ምን እንደምታነብና ከሀገርህ ስነ-ፅሁፍ ምን
እንደምትጠብቅ ንገረን?
ደ:- አወ በዓመት ዓመት ያህል ቀናት አነባለኹ። በቀን
1000 ጥሩ ቃላት ለማግኜት 2000 ያህል ቃላት እፅፋለኹ።
ከሀገሬ ስነ-ፅሁፍ የምጠብቀዉ ስነ-ፅሁፍ ኾኖ ማየት
ነዉ።
173
| ናትናኤል ዳኛው
ጋ:- የፅሁፍህን ክብደት ያህል ግን የተረኮቹን አጨራረሱን
ያቀለዋል የሚሉህ ሀያሲያን አሉ። ሱርሪያሊስት ነዉ የሚሉም
አሉ ይኼን ጨምሮ በጠቅላላዉ ስለ ፅሁፍ ጉዞህ ንገረን?
ደ:- ሱርሪያሉስት ነኝ ወይ?...አይአዎ ነዉ መልሴ።
የሱርሪያሉዝም አርቱን ባደንቅም ተራተርታ ተብሎ በተጣለዉ
የህይወት ዉሉ ትርጉም መፈለግ ግን ለ'ኔ የተለየ ነገር አለዉ።
አንባቢን የሚያከብድበት ይኼ ይመስለኛል ንቆ የተወዉን
መተዉ አትችልም ብየ ስሰጠዉ አርቱ እምቢ እንዳይል
ስለሚያስገድደዉ እንጂ ያን ህይወት ላይፈልገዉ ይችላል።
ሌላዉ አጨራረሱ ምንምን ለተባለዉ...ምንም ጨለምተኛ
የሚያረገኝ ነገር የለም...ሰዉ የተስፋ ግዞተኛ ነዉ ብየ
አስባለኹ።..ከትዝታና ከተስፋ መሸሽ የሰዉ መንገድ
አይመስለኝም። ስለዚህ ምንም እንኳ በተወሳሰብ የህይወት
መንገድ ዉስጥ የሚያልፉ ቢሆኑ ነጋቸዉን ብሩህ አድርገዉ
እንዲያስቡ አድርጌ ነዉ መጨረስ የማስበዉ። ይሄ የኔ ጣልቃ
ገብነት ልክ እንዳልሆነ ባዉቅም ግን እያደረግኹት ነዉ።
የሚያነበኝ አለ...አንብቦ ሲጨርስ ፊቱ ላይ ወለላ መሳይ ነገር
እንዲታይ ነዉ የምፈልገዉ...አንተ ናቅከዉ እንጂ ይኼም ፍሬ
ይወጣዋል ማለት ነዉ የምፈልገዉ። ይህን ሳደርግ ግን
ለቋንቋና ስነ-ፅሁፍ ታማኝ ሆኜ ነዉ። ምንም ግልብ ነገር
እንዳይኖር እጥራለኹ ለዛም ነዉ ገፀ ባህርያቱ ሀይለኛ
የሚሆኑብኝ...አብዛኞቹ ዐብይ ገ.ባዎች አናተ ጠንካራ ይሆናሉ።
አየህ በጠንካራና ዉስብስብ ፈተና ዉስጥ እንደማለፋቸዉ
የማሸነፍ ዓቅምና ሞራላቸዉም ያን ያህል ጠንካራ ነዉ
174
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የሚሆነዉ። ለሚያነባቸዉ የሚረሱ ዓይነት አይሆኑም...ትንሽ
heroic ሆንኹ አይደል?...አበጀኹ። ጀግና አምላኪነት እንጅ
ጀግንነት የሚነቀፍ አይመስለኝም። ደግሞስ ጀግኖች አይደሉ
"የአማርኛ ስነ-ፅሁፍ" የሚባል እንዲኖር ያስቻሉት?.
ጋ:- ግሩም ነዉ። እስቲ ስለቋንቋ እናዉራ?...ቋንቋ እና
ሀሳብ ምንናምን ናቸዉ?
ደ:- ቬሪ ኢንተርስቲንግ ጨዋታ አመጣህ...ቋንቋ መሳሪያ
ነዉ...ሀሳብ
ኢዝ
ሰምቲንግ
ኤልስ*...ምንአልባት
ከኒዩሮንስ...ኬሚካልስ ምናምን አገናኝቶ ሊገልፀዉ የሚችል
ሳይንስ ነዉ። እኔ ኢሉዥን ነዉ ብየ ነዉ የምነሳ..በኔ ዉስጥ
እያለ እንኳ በሰለጠንኩበት ቋንቋ ካልገለጥኩት እኔም
አላዉቀዉም...ያንኑ በቋንቋየ የገባኝነዉ ሌላዉ በሚገባዉ
ቋንቋ የምገልፅለት። ስዕልም እንኳ የሃሳብ ማስተላለፊያ አንድ
መንገድ ነዉ። ግን በስዕል የምትገልፀዉ በቋንቋህ ያሰብከዉን
ነዉ። ሀሳብ ሲመጣ አብሮ ቋንቋም መምጣት አለበት። ካለዛ
አሳቢዉ ራሱ አያዉቀዉም። ሀሳብ ከቋንቋ የተለየ መኾኑን
የምታዉቀዉ ደግሞ ተመሳሳይ ሀሳብ በተለያየ ቋንቋ
ታገኛለህ። its wondering እኮ አኹን አንድ ድመት የኾነች ሲላ
ለመያዝ ፈልጎ እንዴት ነዉ "አድብቼና ጊዜ ጠብቄ ልያዛት"
የሚለዉ?...ማሰቢያ ቋንቋ አለዉ?...ደግሞስ እሱ ሊመገባት
የሚችላት መኾኗን ተፈጥሮ በደመነፍስ ስለነገረችዉ ነዉ ብቻ
ነዉ?...በትክክል መመለስ የሚችለዉ ሳይንስ ቢኾንም እኛን
በቋንቋችን እያሰብን ከመደነቅ አያግደንም።
175
| ናትናኤል ዳኛው
ለአንድ ጋዜጣ በእንግሊዝኛ ከፃፍኩት essay የተወሰነ
ልጥቀስልህ:-
(...)
Language is only for the expression. But idea is
something beyond that. You as a being is trained in
some languages and you choose to organize those
illusional things into the language you are trained.
Someday you may have said that "oh! this
language is too lazy to express what i am feeling,
what i am thinking.". And then you may jump to
another, you think is better in some ways, to form
those feelings or ideas.
(...)*Herald 311th ed.
ጋ:- ይደንቃል!!...ሌላ ጥያቄየ ከደራሲና ከማህበረሰብ
ማነዉ የሀሳብ መሪ??
ደ:- አንተ ሰዉ እየወደድኩህ ነዉ ሃ ሃ ሃ....እ እ
በድርሰት ከሰዉ ወደ ሰዉ ነዉ የምትመላለሰዉ።
የመምራትና የመመራት ነገር ብዙ አስጨናቂ አይመስለኝም።
አያ ሙሌ ይመስለኛል የዜማ ስራ ልሳን እንደመተርጎም ነዉ
የሚለዉ...እኔም ከዚህ የተለየ አልልህም የምፅፈዉ ሰዉን ነዉ
176
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በገባኝ ልክ...ያን ከየት አመጣኹት? ከሰዉ?...ከተፈጥሮ?
የምፅፈዉም ለሰዉ ነዉ...መቼም ስለእርግብ ብፅፍ...አእዋፋት
ያነቡልኛል ብየ አይደለም...ለሰዉ ነዉ...ያች የተፃፈች ወፍ
እራሷን የምትመስላት እንስት አትጠፋም። ታዲያ ማን ነዉ
የመራ ያች ሴት ስትኖረዉ ወይስ እኔ ስፅፈዉ? እንጃ ነዉ
የምልህ።
እኔ ልብወለድ ነዉ የምፅፍ...ልብወለድ ደግሞ ሃሳብ ብቻ
አይደለም ህይወት አለዉ...ያ ህይወት ከትዝታ አልያም
ከምኞት ይቀዳ ይሆናል። ብቻ ግን የሚኖር ነዉ...ልዩነቱ እኔ
ስፅፈዉ አልኖርኩት...የሚያነበኝ ደግሞ ኖሮት ግን
አስተዉሎት አያዉቅ ይሆናል...የዛኔ ነዉ እራሱን የእኔ ተከታይ
አድርጎ የሚያጨዉ...ተርጓሚዉ ነኛ!!
የመሪና የተከታይነት ነገር ለኔ ብዙ አሳሳቢ
አይደለም...ተሻጋሪ ህይወት እስከፃፍኩ ድረስ እና እንጃ ነዉ
መልሴ።...አንተም አያሳስብህ የምትፅፍ ከኾነ ዝም ብለህ ፃፍ።
...የምትከተለዉም የምትመራዉም አታጣም ሰዉ ነህና።
ጋ:- እሺ። እ ሌላዉ አስረኛዉ መፅሃፍህ "ምስላል ትዝ
ሲለኝ" ላይ ይመስለኛል "የምንኖረዉ አዋላችንን ነዉ።
አዋዋልህን አይቼ አኗኗርህን እነግርሃለኹ።" የምትል ነገር
አየኹ... እንዳነበብኳት ብዙ ነገር ነዉ ያወጣኹ ያወረድኩት...
ራሴን አጠገቢ ያሉትን ፈተሽኩ...ሃቅነቱን ተረዳኹ። ወዲያዉ
ነዉ አኗኗሬ ከአዋዋሌ የተቀዳ መኾኑን ተረድቼ ለለዉጥ
177
| ናትናኤል ዳኛው
የተወጋጄኹት። የምፈልገዉን አለመስራቴ ያስከፋኝ ነበር።
አኹን መስመር ላይ ያለኹ ይመስለኛል...ግን ሪጅድ* ሰዉ
አደረገኝ... የለመድኩት ቀላል ህይወት ራቀኝ። እስቲ ለኔም
ለሌሎችም በዚህ ጉዳይ?
ደ:- በመጀመሪያ እዚያ ላይ በራስጌ ፅሁፍ
እንደጠቆምኩት አባባሉ አነ ዲላርድ የተባለች ደራሲ ነዉ።
"የምንኖረዉ አዋዋላችንን ነዉ" የሚለዉ ሌላዉ የኔ ነዉ።
ህይወቱ ግን የኹላችንም። አንተ የከበደህ የለመድከዉ ቀላል
ስለነበረ ሳይኾን የምትፈልገዉ በዛ በኩል ስለሚገኝ ነዉ።
ከጓደኞችህ ማየት ትችላለህ...የሚፈልጉት በዛ በእናንተ አዋዋል
ዉስጥ የሚገኝ ስለነበረ ተሳክቶላቼዉ የሚፈልጉት ላይ ይገኙ
ይኾናል። የ'ኔ አዋዋልና አኗኗር ከማህበራዊ ህይወት በእጅጉ
የሚያርቅ ግን በስኬጁሌ መሰረት ዋና የምላቼዉ ማህበራዊ
ነገሮች ላይ ብቅ እላለኹ። በነገርህ ላይ እንደ ሀገር በማህበራዊ
ህይወት ብቻ የምንኖር የሚመስለን ነን። ይኼ ደግሞ ብዙ
ስለማያራምድ ስኬትና አዲስ ነገርን የተዓምር ስራ
አድርጎብናል። በተዓምር የምናምን ዜጎች መኾናችን ደግሞ
በተለያየ መስክ ጀግኖች እንዳናፈራ ያደረገን ይመስለኛል።...
የምናሞግስና የምናደንቃቸዉን እንኳ ዉጤታቼዉን እንጂ
እንዴት አልፈዉ በየት አልፈዉ እዚህ ደረሱ የሚለዉን
አናዉቀዉም። በቃ የ40 ቀን ዕድላቼዉ እንዲያ ቢኾን ነዉ
ብለን ዝም እንላለን። አደም ቦርጊን የሚያህል ደ ያላት ሀገር
የእሱን ዉሎና አከራረም...የእሱን የንባብ አሻራ የሚያዉቅ ዜጋ
ግን የላትም። አኹን አኹን እሱን የሚያደንቅና መከተል
178
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የሚፈልግ ወጣት እንደ አሸን እየፈላ ነዉ። ግን እንዴት?
የሚለዉ ግልፅ የሚኾንላቼዉ አይመስለኝም። ሀገራችን
የሌላት አንዱ ነገር ሰዉ የቀኑ ባለቤት መኾኑን ማወቅ
የሚባለዉ ነዉ። ቀንህ ያንተ መኾኑን ስታዉቅ ዉሎና
አዋዋልህን ትመርጣለህ። ያ አዋዋልህ ነዉ ቀጣይ ህይዎትህን
የሚወስነዉ። እኔ በግሌ አደም የቀኑ ባለቤት መኾኑን ገና
ከአነሳሱ ወስኖ የተነሳ ይመስለኛል። ነሲብነትና መጠላለፍ
የበዛዉን የሀገሩን ፖለቲካና ማህበራዊ ህይወትየሚሸሸዉ ለዛ
ይመስለኛል።
ጥንቅቅ ያለ የስኬጁል ሰዉ ይመስለኛል... በየቀኑ
ማንበብና መፃፍ አለብኝ ብሎ የተነሳ...አለ አይደል በስነ-ፅሁፍ
ኦብሰስድ* የኾነ ሰዉ። ስራዎቹን ሰብስበህ... የተፃፉበትን
ወቅት ለማስተያየት ብትሞክር ተከታታይነት አታጣባቼዉም።
ከመፃፍ የቦዘነበት ጊዜም ያለ አይመስለኝም። ከእኔ በኋላ
ከመጡ ደያን ከምኮራባቼዉ አንዱ እሱ ነዉ።... ስጠቀልል ይች
እኔና አንተ ያሳለፍናት ደቂቃ እንኳ የኹለታችን ህይወት ላይ
አሻራ አላት እንኳንስ 24ሰዓት ይቅርና።
ጋ:- ብዙ ጊዜ አምርረህ ትናገራለህ። "በኛ ልክ የሰዉን ልጅ
አቅም
የሚጠራጠር
ህዝብ
አላዉቅም!"
እያልክ...ሃይማኖታችን ሰዉን የሚያገዝፍ ኾኖ እያለ
ስራዎቻችንን ግን የተዓምር የማድረግ አባዜ አለብን። ላሊበላን
የሚደግም ትዉልድ አጣን እያልን ብንወቃቀስም...
179
| ናትናኤል ዳኛው
በተቃራኒዉ ደግሞ የላሊበላ ዉቅር በመላዕክት ነዉ የተሰራዉ
እንላለን።
ደ:- በነሲብ ስለምንነዳ አንድ ነገር ላይ መሰልጠንን
አልተለማመድነዉም። በምሳሌ ማሳየት እኮ ይቻላል። ዛሬ
ድረስ በበሬ እናርሳለን... የኾነ ቦታ ደግሞ ፋብሪካ በሽ ኾኖ
ታያለህ... መሃል አገር በIT ልዘምን ብሎ ሲንደፋደፍ
ታገኘዋለህ።... አንዱንም ግን ጠንቅቀን መከወን አልቻልንም።
በሰለጠኑት ፍጥነት ልክ እንጓዛለን ስለምንል ነዉ አንዱን
እንዳዝረከረክን ወደ ሌላኛዉ የምንሸጋገረዉ። ሶስት የስልጣኔ
ሽግግሮችን አንድ ላይ ልታስኬድ የምትለፋ ሀገር ኢትዮጵያ
ብቻ ትመስለኛለች።
በጊዜ ተመልሰን ያዝረከረክነዉን እየሸከፍን ካልሄድን
ከባድ የሚኾን ይመስለኛል። አልያ ደግሞ አኹን ሰለጠን የሚሉ
መንግስታት የኼዱበት የመዘመን መንገድ ተፈጥሮን
አዉድሞ ብቻዉን የሚያቆም ነገር ባለመኾኑ የራሳቸዉ ዜጎች
'ኤጅ ኦፍ ዊዝደም' በሚል አምስተኛ የስልጣኔ ዘመን
ተነስተዉባቸዋል። ወደ ተፈጥሮ ወደ መንፈሳዊነት ተመልሶ
ስልጣኔን የመምራት ዘመን ነዉ። በለመድነዉ የጥንቸል ዝላይ
ወደ ዚህ ዘመን መሻገርና ወደተፈጥሯችን መመለስ ያለብን
ይመስለኛል።
ኹሉም ነገር ሂደት አለዉ...በአንድ ጀምበር ማስተር*
የምታደርገዉ ነገር የለም። ዛሬ ደ ነህ ብለህ ስታዋራኝ
180
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
በስህተትና በትክክል መሃል 50 ዓመታትን በመዉደቅና
በመነሳት
አሳልፌ
ነዉ።
ስራየ
የተሰጥኦ
ብቻ
አይደለም...ያልሞከርኩት የአፃፃፍ አይነት የለም...ከተ እስከ
ሳፊ...ከባዮፊ እስከ ማ ሪዝም።...ዛሬ የኔ የምለዉ የአፃፃፍ ቅርፅ
ዉስጥ የገባኹት በእንደዚህ ዓይነት መልክ አልፌ ነዉ።
ሳላነብ አልፅፍም ማንበብ ከጀመርኩበት የልጅነት ዕድሜ
እስከ ዛሬ ጉልምስናየ አስገዳች ከኾነባቸዉ ጥቂት ቀናት ዉጭ
መፅሃፍትን ያልገለጥኩበት ቀን የለም። ይህን ኹሉ የምልህ
አንባቢ ነኝ ለማለት አይደለም የልፋት ዉጤት ነኝ ማለቴ ነዉ።
ጋ:- ሰዉ የፈለገዉን መኾን ይችላል ብለህ ታምናለህ?
ደ:- እንደሱ አይነት የተምኔት ቅዠት ዉስጥ መግባት
አልፈልግም። ግን የምትወደዉን ካወቅክ ልብህ እዛጋ ከሆነ
ሂደቱን የመታገስ አቅም ይኖርሃል ማለት ነዉ። ያ
የሚወልደዉን ነዉ እንግዲህ ዉጤት ብለን የምናቆለጳጵሰዉ።
... አንተ የተለመደዉን አይነት ተራ ጋ ኾነህ ማለፍ
ትችላለህ...ግን ጋ መኾን ማለት ምን ማለት ነዉ? ከሚለዉ
ተነስተህ...መልሱን በመኾን እስከ ምታገኘዉ ድረስ ስትጓዝ
ደግሞ ሌላ መቻል ታገኛለህ። እስከዛ የምትጓዘዉ ግን በቀላሉ
በስም ብቻ ጋ በመባል የምታገኘዉን ድለላ ጥለህ እስከ ጥልቁ
ስትጓዝ ያለዉን ህመም የመታገስ አቅሙን ስታገኝ ነዉ።
ጋ:- እግረመንገዴን ልጠይቅህ እና አንተ በምትለዉ
መንገድ ያለፈ የምታደንቀዉ ጋ አለ?
181
| ናትናኤል ዳኛው
ደ:- ይኖር ይኾናል.. ከናንተ የሚለዩትና ነጥረዉ
የወጡትንና በዛዉ ለመቆየት የሚተጉትን አንተዉ ፈልገህ
አግኛቼዉ።
ጋ:- ህህህ...ለዛሬ ጥያቄየን ጨርሻለኹ።
ደ:- ....
ጋ:- አመሰግናለኹ
ደ:- እኔም
182
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ሳይረን
"አንቺ የኔ ጥለሸት" ነበር የሚለኝ አባቴ...መልከጥፉነቴን
ቢነግረኝም ቢያንስ ግን የኔ ብሎ የሱ አድርጎኛልና አልከፋም
ነበር።...ተገኝቶ ነዉ ከነ እንከን የሚወድ?...እናቴ ለ'ኔ በግልፅ
ባትነግረኝም
የሚሰማትን
አላጣዉም..."ማህፀኔን
አማኹት...እነዛን የመላእክት ቁራጭ እንዳልሰጠኝ ይችን
ልዉለድ!?" ማለቷን ሳልሰማ አልቀረኹም። ግን አንደበቴ
መፍታት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ "ያች መልከጥፉዋ" ወደ
"ያች ድምፀ መልካሟ" ተሸጋግሪያለኹ።... ግን ልጉም ነበርክ
ቶሎ ቶሎ የማዉራት ልምድ አልነበረኝም። ታዲያ ድምፄን
መስማት ሲፈልጉ ቡና ተፈልቶ ጎረቤት በተሰበሰበበት ተረት
ካላወራሽ እባላለኹ። ደስ ይለኛል በመልከጥፉነቴና ጥቁረቴ
አሳንሰዉ በሚያዩኝ መሃል ተፈልጌ ተጠርቼ ኹሉም እኔን
ለመስማት ፀጥ ሲል ከአኹን አኹን ቃል ወጣት ሲጠባበቅ
ማየት ልቤን ሞላት። ግን ምን ይደርጋል ድምፅን እንደ ፊት
ለብሰዉት አይዞሩ። ትንሽ ከፍ ማለት እንደጀመርኩ ለመዘፍን
ሞካከርኩ። ግን የፆታ ፍቅር ዘፈን ስለሚበዛ በአደባባይ አፌን
ከፍቼ ለመዝፈን እፈራ ነበር። ጥቂትም ቢኾኑ ለሀገር እና
ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የተዘፈኑትን ግን አንጎራጉር ነበር። በዚህ
ድምፄን የሰሙ ዝፈኝልን ይሉኛል። ሰፈር የሚቀመጡ
ጎረምሶች ጠጠር ማስቲካ* ይገዙልኝና የሚወዱትን ሙዚቃ
ያዘፍኑኛል። እየቆየ ግን ይኼ ነገር እየተሰማማ ተቀጣጥሎ
183
| ናትናኤል ዳኛው
ከቤት መዉጣት እስክፈራና እስክከለከለ አደረሰኝ። አንድ ቀን
ት/ቤት ረፍት ወጥተን ተማሪዎች ከበዉኝ እየዘፈንኩላቼዉ
ነበር። የት/ቤቱ ደወል ተደጋግሞ ቢደወልም ተማሪዉ ግን
የሰማዉ አልነበረም። ወዲያዉ ረዣዥም ልምጭ የያዙ ዩኒት
ሊደር መምህሮች ወደ ተሰበሰብንበት መጡ። ሌሎች
ተማሪዉን በትነዉ ወደ ክፍሉ እንዲገባ ሲያሯሩጡ የሂሳብ
አስተማሪያችን የኾነዉ ዩኒት መሪ እኔን ጆሮየን እየሳበ ወደ
ርዕሰ መምህሩ ቢሮ ወሰደኝ።
ርዕሰ መምህሩ ፊት ለፊቴ አይናቸዉን የተኳለ
የሚያስመስለዉን ባለወፍራም ቢጋር የዐይን መነፅር ለብሰዉ
ተቀምጠዋል። ወዲያዉ ወደአግዳሚዋ እየጠቆሙ በእጃቸዉ
ምልክት ተቀመጡ አሉን
"ምን አጥፍተሽ ነዉ አንቺ ባሪያ?" አሉኝ
"እንጃ" አልኳቸዉ መምህሩን በሃፍረት እያየኹ
"ምንም ሳታጠፊ ነዉ እዚህ ያመጣሽ!"
"ለተማሪዎች እየዘፈንኩላቼዉ ነበር"
"እሱ ምን ችግር አለዉ ታዲያ?"
"እንጃ!!"
ወዲያዉ ዩኒት ሊደሩ
184
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"መዝፈኗ ሳይኾን ችግሩ በት/ት ሰዓት መኾኑ ነዉ" አለ
ርዕሰ መምህሩ "በረፍት ነዉ የምትለዉ እኮ" አሉት
"ደወሉን እየሰሙ እንዳልሰሙ ኾነዉ ነዉ ትዘፍንላቼዉ
የነበረዉ።"
ትንሽ እያፈራረቁ ሲያዩን ከቆዩ በኋላ...ተነስተዉ
የቢሯቸዉን በር ዘግተዉ ተመልሰዉ ወንበራቸዉ ላይ
እየተቀመጡ
"እስቲ ዝፈኝ?" አሉኝ
ደንግጨ
አልኳቸዉ
ቆሜ
ዞሬ
ተቀመጥኩና
"አይይ...ይቅር"
"ግዴለም
ለተማሪዎች
የዘፈንሽዉን
ለኛም
ዝፈኝልን...አይደለም!?" ብለዉ ወደ መምህሩ አዩ...ትንሽ በፈራ
አኳሃን
"አ አ አወ" አለ እሱም
ዐይኔን ጨፍኜ ራሴን ካረጋጋኹ በኋላ የእጂጋየኹ
ሽባባዉን "አድዋ ዘፈንኩላቼዉ።... ዘፈኑን ጨርሼ አይኔን
ስገልጥ ርዕሰ መምህሩ እያለቀሱ እንባቼዉ ከመነፅራቸዉ ስር
ተዝረክርኳል። ዩኒት መሪዉ በመገረም ያያኛል። አንገቴን
አቀረቀርኩ። መነፅራቸዉን አዉልቀዉ በመሃረብ እንባቸዉን
185
| ናትናኤል ዳኛው
ከጠረጉ በኋላ ተነስተዉ ግንባሬን ስመዉ አምስት ብር እጄን
አስጨበጡኝና ዩኒት መሪዉን "ከክፍሏ መልሳት" አሉት
እኔን ደግሞ "በርች!..የሚቀጥለዉ የወላጆች በዓል ይህን
ዘፈን ትዘፍኛለ" አሉኝ
እንደደነገጥኩ ስለነበረ በራሴ "እ ሺ" አልኳቸዉ
ጆሮየን ይዞ እየጎተተ ያመጣኝ መምህሬ አቅፎ ክፍሌ
አድርሶኝ ተመለሰ።
ከዛን ጊዜ ጀምሮ ት/ቤት ዉስጥ ስሜ ገነነ። ረፍት ሰዓት
የምማርበት ድረስ እየመጡ አንጎራጉሪልን የሚሉ ተማሪዎች
በዙ። የመጀመሪያዉ ዓይነት ስህተት እንዳዬደገም
እየተጠነቀቅኩ እንደነገሩ እወፋፍንላቸዋለኹ እንደዛም ኾኖ
ግን እጃቸዉ እስኪቀላ ያጨበጭቡልኛል።
የወላጆች በዓል ከዘፈንኩ በኋላ ደግሞ በሰፈሬ የነበረዉ
ነገር ተቀየረ...አባቴ "የኔ መረዋ!...አኮራኸሽኝ እኮ?" ማለት
ጀመረ
እናቴ "ከሞተ አንበሳ ማር ይወጣል አለ መፅሃፍ... አኹን
ከዚህ መልክ ይኼ ድምፅ ይፈልቃል ብሎ ያስባል!" ማለቷን
ሰምቻለኸሉ።
ዉበት ያላት ኹሉ የኔን ያህል የምትከበብ አይመስለኝም።
... ት/ት ቤት የማዉቃቼዉ እነዛ ቆነጃጅት ከሚያበራ
186
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ዉበታቼዉ ይልቅ የኔ ድምፅ አስቀንቷቸዋል።...ድምፄ
ወጥመድ ነበር... የሰማዉን ኹሉ ወደራሱ የሚስብ።
ዕድሜየ ሲጨምር በወንድ የመከበበብ ናፍቆቴ አብሮ
አደገ። የሰፈር ጎዳና ላይ ወጥቼ አንጎራጉራለኹ...ሰወች
መጥተዉ ይከቡኛል...ነገሩ እንደልክፍት ኾነብኝ።
ብቻየን ይበርደኛል...ቤተሰቦች እኔን ከብቦ ድምፄን
ለመስማት ያንሱብኛል...መንጋ ፍለጋ እወጣለኹ።... መሽቶ
እንኳ ቤቴ መግባት ያስፈራኝ ጀመር።
አንድ ምሽት ላይ እዛዉ እኛ ሰፈር ልጀች ተሰብስበዉ
እየዘፈንኩላቼዉ ነበር። ከመሃል ግን ከዚሄ በፊት የማላዉቀዉ
ፂማም ወጣት አየኹ። ያዉ የተለመደ የድምፄ ወጥመድ
ዉስጥ የወደቀ ነዉ በሚል አላዳነቅኩትም ነበር። ልጆቹን ሸኝቼ
ወደቤቴ እየሄድኩ እያለ "ለምን ክለብ አትዘፍኝም?" የሚል
ድምፅ ሰምቼ ስዞር ያ ፂማም ወጣት ነዉ። ሰላም ብሎኝ
"ዝናሽን ሰምቼ ነዉ የመጣኹት" ብሎ ቀጠለ
"ፒያሳ የምሽት ክለብ አለኝ...ልቀጥርሽ እችላለኹ"
"ማለት ልትከፍለኝ?"
"አዎ...እዚህ በነፃ ከምትዘፍኝ...እኔ እከፍልሻለኹ!"
"ግን ፒያሳ እኮ ሩቅ ነዉ"
187
| ናትናኤል ዳኛው
"እኔ መኪና አለኝ...አመላልስሻለኹ"
"ነገ ልደዉልልህ?"
"ደስ ይለኛል...አደራ እ!"
ተባብለን ስልክ ቁጥሩን በወረቀት ሰጥቶኝ ሄደ። ቤቴ
እንደገባኹ ራት ልበላ ቀጥታ ወደ ሩሜ ሄጄ አልጋየ ላይ ሆኜ
ማሰብ ጀመርኩ። በብዙ የከተማዉ ጮሌ ወጣት ወንዶች
ስከበብ እንደ ህልም ይታየኝ ጀመር። ሌሊቱን ሙሉ ስገለባበጥ
እህቴ አልፎ አልፎ ስትነቃ "አንቺ ጥላሞት አትተኝም!?"
ትለኛለች
ቀን ቢኾን በትምህርት እየቀጠኹ መሄድ እችል ነበር።
ማታ መኾኑ መላ አሳጣኝ።...ሌት እቤት ቀን ት/ቤት ባወጣ
ባወርድም መላ እማደርገዉ አጣኹ። ቢኾንም ግን መደወል
አለብኝ ብየ ወሰንኩ።... ለእረፍት በወጣንበት ሩቅ ምስራቅ
እያልን በምንጠራዉ መምህራንም ኾነ ተማሪዎች
ወደማያዘወትሩት አካባቢ እየተጣደፍኩ ሄድኩ። በዛዉ በኩል
ተማሪዎች አርፍዶ ለመግባትና ቀድሞ ለመዉጣት አጥሩን
ቀደዉ ያዘጋጇት የዉሻ ቀዳዳ እንዳለች ስለሰማኹ ነዉ ወደዚህ
የመጣኹት። ቀዳዳዋን ለማግኜት ትንሽ ደከምኩ... ሳገኛትም
ለመሹለክ
ቀላል
አልኾነልኝም...የአካል
መተጣጠፍ
የምትጠይቅ አይነት ናት። ክፋት በጥበብ የሚከወንበት ዘመን
ነዉ...ሰዉ ለስሜቱ ግሪንላንድ ድረስ እርቆ ሊጓዝ ይችላል።
188
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
እየወጣኹ እየገባኹ በቀዳዳዋ ተጋግቼም ቢኾን ሾልኬ
የግድግዳ ስልክ ወደ ወደማገኝበት ሮጥኩ።
"እንደምትደዉይ አዉቅ ነበር።" አለኝ...ታዲያስ ምን
አዲስ አለዉ "እንድደዉል አይደል የሰጠኸኝ" ልለዉ
ነበር...ቆይቼ ነዉ የገባኝ... የሀሰት ቁጥጥር መቀባበል
እንዳለ...እደዉልልሃለኹ...እደዉልልሻለኹ ተባብሎ ቁጥር
ተቀያይሮ እግር ሳይርቅ ነፈዝ መባባል እንዳለ።
እንደጨነቀኝ ነገርኩት...ከቤት ወጥቼ ለማምሸት
ያዘጋጀኹት ዉሃ የሚያነሳ ምክንያት እንደሌለኝ አስረዳኹት።
የምሩን ነበር የተጨነቀልኝ...ለመኮብለል እንኳ የሚያስችል
የልብ ሙላት የለኝም። እስቲ ደግመሽ ነገ ደዉይልኝ ብሎኝ
ስልኩን ዘጋኹት። ተመልሼ ወደ ት/ቤቴ መግባቱን
ፈራኹት...ኾዴን አመመኝ በሚል የዉሸት ሰበብ ቤቴ ሄድኩ።
አልጋየ ላይ ኾኜ ስገለባበጥ መሸ። ሳሎን ወጥቼ ቴሌቪዥን
እያየኹ እያለ እህቶቼ ከት.ቤት ተመልሰዉ መጡ። አንዳቼዉ
ለምን ቀድመሽ መጣሽ አላሉኝም...ታላቋ ሶፋ ላይ የተኛችዉን
ጥቁር ድመት አስደንብራ ከሳሎን አባራት ተዘርግታ
ተቀመጠች። ታናሼ የኹለቱንም ቦርሳ ክፍል ዉስጥ አስቀምጣ
የእጅ ማስታጠቢያ ይዛ ተመለሰች። እየበሉ "ስለቀደምሽን
በልተሽ ይኾናል ብየ ነዉ "አለችኝ
ስሜቴ ተቀያይሮ ወደ ዉሳኔ ስገባ ይታወቀኝ ነበር...ላባቴ
መንገር እንዳለብኝ ወሰንኩ። እህቶቼን እዛዉ ሳሎን ትቼ ክፍሌ
189
| ናትናኤል ዳኛው
ስገባ አልጋየ ላይ ድመቷ ተኝታ አገኘኋት። በተኛችበት
እየዳበስኳት የአባቴን መምጣት ስጠባበቅ ቆየኹ።...ቀድማ
ግን እናቴ ብቻዋን መጣች ከኋላ ይኖራል ብየ ብወጣ ለእህቶቼ
"ሆስፒታል ሄዶ ነዉ" ስትላቼዉ ሰማኋት...ሁለቱም እኩል ነዉ
የደነገጡት
"...አረ እሱ ደህና ነዉ።...የእርጎየ ልጅ ታሞ እሱን ሊያይ
ነዉ።"
"እ" ደግመዉ እኩል ደነገጡ
...እኔ ፈገግ ብየ እናቴንም እነሱንም አየኋቼዉ።
የእማየን ጥበብ የማደንቀዉ እዚህ ላይ ነዉ...በወሬ
የሚረታ ልቦና የላትም። የእህቶቼን ድንጋጤ አይታ እንኳ ቅር
አላላትም...እርጎየ በአባታችን ቅምጥነት እንደምታማ
ታዉቃለች። ልጁ ይኼ አኹን ታመመ የሚባለዉ አባታችንን
የሚመስሉ ነገሮች እንዳሉት ታዉቃለች። ግን ምንም አዲስ
ነገር እንዳልተፈጠረ ነዉ ልጆቿ ፊት እንኳ የምትኾነዉ። እህቶቼ
እጃቸዉን እያወናጨፉ ሲበሳጩ ቁብ ሰጥታ እንኳ
አላየቻቼዉም...ከቢሮ እንደተመለሰች መክሰስ እንኳ ሳትበላ
ነጠላ ለብሳ እሷም ወደ ሆስፒታል ሄደች።
ተመልሼ ክፍሌ ከገባኹ በኋላ እንኳ...ሳሎን ዉስጥ "የዛ
ቅንዝር ሰዉየስ እሺ...የሷ መደነዝ አይገርምሽም"
"እዉነት ሳይከፋት ቀርቶ ነዉ?"
190
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
"ደግሞ የዚህ ዲቃላ ነገር እንጂ...ከጀርባ እኮ አባን ነዉ
የሚመስል
"እኔ ግን ሳየዉ እደነግጣለኹ"
"አረ ይኼ እኔስ ባጮለዉ ነዉ የምል" ይባባላሉ
...ከድመቷ ጋር እየተላፋኹ እስቃለኹ።
ሶስት ሰዓት አካባቢ የግቢ በር ተንኳኳ። እህቴ ልትከፍት
ስትሮጥ ተከትያት በረንዳ ላይ ቆምኩ። ኹለቱ ፊትና ኋላ ኾነዉ
ገቡ። ቤቱ ዉስጥ ታናሿ ተኝታ እኔና ታላቋ ብቻ ነበር
የቀረን...ቃል ሳንለዋወጥ እማና አባ መጡ። "አንቺ መረዋ"
ብሎ ግንባሬን ሳመኝ...እኔና እሱ በረንዳ ላይ እንዳለን እናቴና
እህቴ ተከታትለዉ ገቡ። ፊቱ እንደደከመዉ ያስታዉቅ ስለነበር
ጉንጩን ስሜዉ ብቻ ገባኹ።
ሳሎኑ በፀጥታ ተዋጠ አባ ደጋግሞ ያስፏሽጋል እማዬ
የቡና ስኒ ታቀራርባለች...እህቴ ዐይኗን ቴሌቪዥኑ ላይ
አታነቃንቅም። እኔ ድመቷን ጭኔ ላይ አድርጌ ከሷ ጋር
እላፋለኹ።
ራቴን በልቼ ወደ ክፍሌ ሳመራ "ቡና አትጠጭም" አለችኝ
እማየ ...ዘወር ብየ
"ልተኛ ነዉ...ይቅርብኝ" አልኳት
191
| ናትናኤል ዳኛው
አባቴ "አንች ልጅ ደህና እደሩ ማለት ይልመድብሽ" አለኝ
ፈገግ ብየ "ደህና እደሩ" አልኳቸዉ
በዓይኑ ጠቀሰኝ።
በቀጣዩ ቀን ት/ት ቤት ሆኜ ሃሳቤ ኹሉ የክለቡ ጉዳይ ኾነ።
አባን
እንዴት
ነዉ
የማሳምነዉ
የሚለዉ
አስጨነቀኝ...መንፈሱን አዉቃታለኹ ነፃ ናት...የሰዉን መንፈስ
መሻት የምትጋፋ አይደለችም...ግን ሴት ልጁ ነኝ ደህንነቴን
የሚያረረጋግጥበት ይፈልጋል። ያስጨነቀኝ ይኼን ማረጋገጨ
ማግኘቱ ነዉ። እንደለመድኳት በዛችዉ የዉሻ ቀዳዳ ሾልኬ
ለባለ ክለቡ ደወልኩለት እሱ "እስቲ አንድ ቀን አምሽተሽ
ሞክሪያቸዉ"
አለኝ...ደስ አላለኝም...ግድየለህም አባቴን
አናግረዉ ብየ የመስሪያ ቤት አድራሻዉን ሰጠኹት።...ዛሬ ሄዶ
እንደሚያገኘዉ ቃል ገብቶ ቻዉ አለኝ።
ከት/ቤት መልስ በረንዳ ላይ ድመቷን ጭኔ ላይ አድርጌ
እየዳበስኩ የአባንና የእማን ከቢሮ መመለሻ ስጠባበቅ ቆየኹ።
ሲዘገዩብኝ ድመቷን ትቼ ወደ ግቢዉ በር ወጣኹ።በር ላይ
ቆሜ መተላለፊያ መንገዱን አያለኹ። መሃል መንገድ ላይ
ህፃናቱ ሰንጠረዥ አበጅተዉ ሰኞ ማክሰኞ ይጫወታሉ። ከነሱ
ራቅ ብሎ የሃኪሟ ልጅ እንደወትሮዋ ተሽቀርቅራ ተቀምጣ
እነሱን እያየች ትተክዛለች። ልብሳቼዉና ገላቼዉ በአቧራ
ከተዋጠዉ ቦራቂ ህፃናት እሷ ታሳዝነኛለች። በእናቷ
አዝናለኹ...ከተፈጥሮዋ ያናጠቧት...ለእነሱ ስም እሷን ያሰሯት
192
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ይመስለኛል። ንፁህ መልበሷ ብቻ ሳይኾን እንዳታቆሽሽ የሚል
ማስጠንቀቂያም ስለሚሰጣት ይኾናል እንዲህ አፈር ዓይንካኝ
የሚያስብላት። ሲጫወቱ ማየቷ የመጫወት ፍላጎት እንዳላት
ጠቋሚ ይመስለኛል።
ወደ ሚጫወቱት ህፃናት ሄጄ "አጫዉቱኝ" አልኳቸዉ
አንዷ ህፃን "ትልቅ እኮ ነሽ" አለችኝ
"ቢኾንም" አልኳት.
የጀመሩትን አቋርጠዉ እንደ አዲስ ጀመርን...ጫማየን
አዉልቄ በባዶ እግሬ ተጫወትኩ። የሃኪሟን ልጅ ዘወር እያልኩ
አያታለኹ። ዐይኗ መጫወት እየፈለገች የፈራች ትመስላለች።
በእጄ "ነይ" አልኳት... በፊቷ "እምቢ" አለች
ሄጄ እጄን ዘረጋኹላት...ጫማና ልብሷን እያየች አንገቷን
አቀረቀረች
ዝቅ ብየ በጆሮዋ "ልብስሽ አይቆሽሽም...ጫማሽን
አዉልቀሽ በባዶ እግርሽ ትጫወቻለሽ...ከዛ ከኔ ጋር ታጥበን
ወደ ቤትሽ ትኼጃለሽ" አልኳት
ቀና ብላ አየችኝ...በፊቴ "አወ" አልኳት
እጇን ይዤ ወደ ህፃናቱ ኼድን።
193
| ናትናኤል ዳኛው
ለህፃናቱ "የኔን ተራ የምትጫወት እሷናት" ብያቸዉ
እያየኹ ቆምኩ
እየተጫወተች ትፍለቀለቃለች... ከእኩዮቿ ስትቦርቅ
የበለጠ አምሮባት አየኋት በዉስጤ "ምንአለ እናትሽ ባየችሽ
ደግማ በእቃ አታስርሽም ነበር" አልኩ
ጨዋታዉን እንደጨረሱ ኹሉንም ስሜ እሷን ወደ ቤት
ወሰድኳት...እግሯን አጥቤ ጫማዋን አልብሼ "ከእንግዲህ
እቆሽሻለኹ ብለሽ አትፍሪ ተጫወች እሽ...ከቆሸሽ ደግሞ እኔ
አጥብሻለኹ" አልኳት
"እማየ ስቆሽሽ ትቆጣለች" አለች...እንደዚህ ስትል የበለጠ
ታሳዝናለች
" እንደ ልጅ መጫወት መቆሸሸ አይደለም እሺ!?"
"..."
"ደግሞ ከፈራሽ ወደ'ኔ ነይ እኔ እጥብ አድርጌሽ ንፁህ ኾነሽ
ወደ እማየሽ ትኼጃለሽ"
"እሽ"
...በር ላይ ቆሜ ወደ ቤቷ ሸኘኋት...እንደ እንቦሳ ትዘላለች።
የቀሚሷን ወገብ ላይ የሚንዘላዘሉትን ጨርቆች በእጆቿ
እያወናጨፈች...በቀጭን የተጎነጎነ ፀጉሯ አብሮ እየዘለለ...ራሷን
194
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ግራና ቀኝ እያደረገች ስትቦርቅ ታሳሳለች። ወደ ቤቷ ስትቃረብ
ዝላዯን አቁማ በቀስታ መራመድ ጀመረች። በርቀት በሩን
ከፍታ እየገባች ግራ እጇን እያወዛወዘች ቻዉ አለችኝ። እኔም
እጄን ስሜ ቻዉ አልኳት።...እዛዉ እንደቆምኩ ከርቀት ወደኛ
ሰፈር የምታገባዉ እጥፋት ላይ አማዬና አባ ብቅ ሲሉ
አየኋቼዉና...ተንደርድሬ ወደ ዉስጥ ገባኹ።
.
.
.
195
| ናትናኤል ዳኛው
መንገድ አያደርስም
ፊት ለፊት በልጅነቴ ድመቷን አቅፌ የተነሳኹት ፎቶ አለ።
በቀኝ በኩል ፒያሳ ክለብ ዉስጥ የመጀመሪያ ቀን ስዘፍን
የተነሳኹት ፎቶ አለ። በግራ በኩል የሰርጌ ፎቶ። የቤቴ ግድግዳ
እነዚህን ብቻ ነዉ የያዘዉ።
ሶፋ ላይ ኾኜ ቴሌቪዥን እያየኹ የልጄን ከት/ቤት
መምጣት እየተጠባበቅኩ ነዉ። ባሌ ከሞተ ሶስት ዓመት
ኾኖታል። ከ'ሱ ሞት በኋላ የዘፈን ድምፅ ከጉሮሮየ ወጥቶ
አያዉቅም።
በቴሊቪዥንን አልፎ አልፎ የሚለቀቁ የድሮ ሙዚቃዎቼን
እየሰማኹ እተክዛለኹ።
አንዳንድ የሬድዮ ጣቢያዎች...ለቃለ መጠይቅ ፈልገንሽ
እያሉ ይደዉላሉ። ከዚህ በፊት ከኾነዉ እና ከተናገርኩት ዉጭ
አዲስ ነገር የለም በሚል እምቢ እላቼዋለኹ። ታዲያ አንዳንዶቹ
"የጤና መታወክ አጋጥሟታል" እያሉ የአየር መሙያ
ያደርጉኛል። ጓደኞቼ ደዉለዉ ሊያዳንቁት ይፈልጋሉ...ደህና
ነኝ...እነሱ ነዉ የታወኩት...ብየ ስልኬን እዘጋለኹ።
በኳኳታ መኃል ኖሮ...ፀጥታን መናፈቅ...የጤና መታወክ
ተብሎ ይተረጎማል። ይኼ ሟች ባሌ አኳሽቶ የክለቡ ዘፈኝ
ካደረገኝ በኋላ ያረፍኩበትን ጊዜ አላስታዉሰዉም። ድምፄ
እርግማኔ እስኪመስለኝ ድረስ ነበር። አትዉደዱኝ አይባል ነገር።
196
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የሌሎችን ትኩረት ለማግኜት ወጥመድ አድርጌ የቆጠርኩት
የኔኑ ሰላም የሚነጥቅ ኾነብኝ። ዝና ና ሃብት ባልጠነከረ ጫንቃ
ላይ ሲያርፍ ከራስ ያቃቅራል። መልከ ነቴን በገንዘቤ ላሽንፈዉ
ጥሪያለኹ... በመስታዉት ቆሜ ከማየዉ የእጂ ስራ መልክ ጋር
ግን የሚያቆራኜኝ አልነበረም። እሱ ይሰብረኛል። ራሴን
መፍራት ጀመርኩ። የባሌ ብልግና በየጊዜዉ ይግላል። አልጋየ
ላይ ከጓደኞቼ ጋር ይወሰልታል። ይኼን ኹሉ ባዉቅም እሱን
ያስቀየምኩበት ጊዜ የለም። እኔም ከፕሮሞተሮቼ ጋር
ቀብጫለኹ። በየፊናችን የልቦናችንን ፈቃድ ከመከወን ዉጭ
አፍ ተካፍተን የተነጋገርንበት ጊዜ የለም። ስንገናኝ እንደ አዲስ
ሙሽሮች
ያደርገናል...ፆም
እንደከረመ...ቤታችን
በፍቅር...አልጋን በወሲብ ፍሲካ ይሞላል። ግን እየሞትን ነበር።
ኬንያ ነበርኩ...ሞምባሳ እርጥብ አሸዋ ላይ ተዘርግቼ
ሰማዩን እያየኹ። ቆዳቼዉ የኔን በሚመስል ተከብቤ። የጋበዘኝ
ደግሞ ካርኒቫል ላይ የተዋወቅኩት ኬንያዊ ዘፋኝ ነዉ። ከ'ኔ ራቅ
ብሎ እሱ በሀገሩ ሴቶች ተከብቦ ፊርማዉን ይበትናል። ሴቶቹ
ከሰዉነቱ እየተለጠፉ...እጃቼዉን ራቁት ደረቱ ላይ እያንሸራሸሩ
ያወሩታል። እሱ በተደጋጋሚ ወደ'ኔ እየዞረ መረበሹን በሚነግር
ኹኔታ እየታገሰ ያስተናግዳቼዋል። የሀገሬ ወንድ አድናቂ
ምንአለ እንዲህ ቢኾን አልኩ።
ተነስቼ እዛዉ ላዉንጅ ዉስጥ ወደ ተከራየናት የሆቴል
ክፍል ሄድኩ። ተከትሎኝ መጥቶ ኖሮ...በሩን ከመዝጋቴ
አንኳኳ። እንደከፈትኩለት ተወርዉሮ ከንፈሬ ላይ
197
| ናትናኤል ዳኛው
አረፈ...ፈርጣማ እጇቹ አካሌን ጨመቋት። የማላዉቀዉ ከዚህ
በፊት ያልለመድኩት የወሲብ ሰርግ ላይ አሳተፈኝ።
አልጋዉ ላይ ተንጋልየ ጣራ ጣራዉን አያለኹ...እሱ ከጎኔ
እያንኮራፋ ተኝቷል። ድንገት ስልኬ ጠርቶ አባነነኝ።
ባሌ ነበር... ልብሴን ለብሼ እስክወጣ ጥሪዉ ተቋረጠ።
ወደ ወንዙ ዳርቻ እየኼድኩ ስደዉልለት በፍጥነት
አነሳዉ...ደጋግሞ
ያስላል...ደም
እንደሚያስተፋዉ
ነገረኝ...ከቻልሽ ዛሬ ማምሻዉን አልያ ነገ ጠዋት መድረስ
አለብሽ ብሎኝ...ዘጋዉ። እቆምኩበት ምድር ስትከዳኝ
ታዉቆኛል...በፍጥነት ወደ ወደ ሆቴሉ ስመለስ ፈርጣማዉ
ጥላሞት ራቁቱን እንደተዘረረ ነበር...ወረቀት ጭሬ 'ጎኑ
አስቀምጨለት ሻንጣየን ይዤ ወጣኹ።
.
ቤቴ ስደርስ እኩለ ሌሊት ኾኖ ነበር። ግቢዉ በዉሻ
ማላዘን ይታመሳል። ልጄ ተኝታለች። ባሌ ሳሎን ወለል ላይ
ተዘርግቶ ያጣጥራል...ዙሪያዉን የአርቲስት ሰልፍ ከቦታል።
እግሬ እንክት እንክት እያለብኝ ቀርቤ ሳየዉ ትንፋሹ
ይቆራረጣል። በእጁ እጄን ለመያዝ ሲሳብ እጄን አቀረብኩለት።
እጄን እንደያዘ ፀጥ አለ። ጣቶቹ ጣቴን ቆልፈዉ እንደያዙ
ትንፋሹ ቀጥ አለ። ደንግጨ መነጨቅኩት። ዐይኑ ወደ ላይ
198
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ተስጎ የአይን ቆቡ ስር ተሸጎበ። በድንጋጤ ጮህኩ። እኔን ከጎኑ
አስነስተዉ ወደ በረንዳ አስወጡኝ። ለቅሶ ኾነ።
199
| ናትናኤል ዳኛው
ነገ ሶስተኛ ሙት ዓመቱ ነዉ።
200
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
ልጄ እንኳ ቤቱ አስጠላት። የለቅሶዉ ድንኳን
አልተነሳም...ሰልስት ኾኖ ለቀስተኛዉ አልተበተነም። በጥቁር
ልብስ ተጠቅልየ ፍራሽ ላይ እግሬን ዘርግቼ ከተጠቀመጥኩበት
መጥታ አንገቴ ዉስጥ ተሸጎጠችና "እማ አያቴ ጋር ልሂድ"
አለችኝ
...ከባድ ነበር ምልክቴ ልሽሽ ስትል...ቤቴ በሙት መንፈስ
ተዉጦ ብቸኝነቱን ሳስብ ቢከብደኝም "እሽ" አልኳት
ከጎኔ እህቶቼና እናቴ ነበሩ።
...የእሷ መሄድ ሲጨንቀኝ ባሌ በሞተ በአምስተኛ ቀኑ
ዉሻዉ ሞተ። እሱን የማስታዉስባቼዉ ነገሮች ከ'ኔ እየሸሹ
መኾኑ አሳሰበኝ። ይኼ በ'ሱ ጀመርኩት የምለዉ ሙዚቃ እንኳ
ከዉስጤ ተሟጦ ወጣ።
ዙሪያየን አጠርኩ።
ኑሮየ የምናኔ ኾነ...የአሳለፍኩትን ተጠየፍኩት። የ'ኔ
አልመስልሽ አለኝ። መርጨዉ ነዉን በዛ መንገድ
የተጓዝኩት?...ከዛ የተለየ መንገድ የለዉም?...ወይንስ
አልታይሽ አለኝ?...አኹን ነዉ የገባኝ በቀናዉ መንገድ መራመድ
የልቦና ማስተዋል እንደሚጠይቅ። በከባቢየ አላየኹም...መኖር
የመወለድ ጣጣ መኾኑ ብቻ ነዉ የተተረከልኝ።...በወገኔ 'ቀናት
አማልክት መኾናቸዉ አይታወቅም' ኤመርሰን
201
| ናትናኤል ዳኛው
ልጄ ስትናፍቀኝ ገላየን በጀለቢያ ሸፍኜ ወደ እናቴ ቤት
እሮጣለኹ።...ፍቅሯ ይቀዘቅዝብኛል...ልጅነቷ ከእኔ ይልቅ
ከአባቷ ጋር የተገመደ ነበር። አንቀባሮ ነዉ ያሳደጋት...ከጎኗ
ስኖር ባላጎድልባትም እጇን በምትዘረጋበት በማንኛዉም
ቅፅበት ግን አባቷን እንጅ እኔን አታገኝም ነበር።..ከማህፀኔ
ወጥታ እንደታቀፋት እንደዛዉ ነዉ እስከለተሞቱ ድረስ
የኾነዉ።...በዚህ
ልትወቅሰኝ
እንደምትችል
አዉቃለኹ...አንገቴን አቀርቅሬ ልሰማትና ይቅር በይኝ ልላት
እንጂ ዐይኔን በጨዉ አጥቤ ልጋተራት እንደማይገባ
አዉቃለኹ። ግን እንድክሳት እድል ነፈገችኝ...ከአባቷ ሞት
ማግስት ወደ አያቷ ሸሸች።...ኦና ሲከበኝ ነዉ በመልካም ባልና
ልጂ የተከበብኩ ንደነበርኩ የታወቀኝ።... ለራሴ ወስልቶብኛል
አልኩ ግን
ፊቴን አላጨፈገግኩበት አልያ "ለምን
ወሰለትክብኝ?" ብየ አልጠየቅኹትም። በበለጠ ፈገግታና ፍቅር
አሞቅኩት ስህተቱን ሸሸኹለት እንጂ። የ'ሱን ስህተት ሸሽቼ
የራሴዉ ማጥ ዉስጥ ተነከርኩ። አቤት የቅጥፍናየ ጥበብ።...
ብቁ የወንጀል መርማሪ የብልግናየን ዳና መርምሮ የሚያገኘዉ
አይመስለኝም ነበር። ራሴዉ የራሴዉ መርማሪ ልኾን
እንደምችል አልተገለጠልኝም። ከዉጭ ስመለስ የቅንዝር
ማዕድ ዉስጥ የከረመች አልመስልም በባሏና ልጇ ናፍቆት
የተቃጠለች...በባሏ ገላ ጥማት የነኾለለች ምስኪን እንጂ።...
ክፋትን በብልሃት መከወን የለመድኩት ከት/ቤት አጥር
የአይጥ መሽሎኪያ በምትመስል ቀዳዳ በቅልጥፍና ሾልኬ
ማምለጥ የጀመርኩ ጊዜ ነዉ። ልጂ ኹኜ አባቴ ደጋግሞ
202
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የሚያወራለት አንድ የገጠር ዘመድ ነበረዉ..."አቤት እሱ!!"
ይላል...በቆዳ በሽታ መላላጥ የጀመረ እጁን ራሱ ላይ ጭኖ
"ማታ የሚገድለዉን ሰዉ ቀን በሳቅ በጭዋታ መጠጥ
ሲጋብዘዉ ይዉላል።" ብሎ ይቀጥላል።
አደንቀዉ ነበር ያን የሩቅ ዘመዴን...የደረሰኝ በጂን ይኹን
በጆሮ ባላዉቅም ያ ገድል የኔም ኾነ።
መሻቴን ማገት የሚችል ኃይል አልነበረም። ለመላ-ምድር
የሚኾን ልብ ነበረኝ።*moliere, don john or libertine
ከበቀለኛ የከፋኹ በቀለኛ ነበርኩ?...በ'ኔ ያለፈዉ የዘመኔ
መንፈስ ይመስለኛል... እባብ ለእባብ ትከሻ ለትከሻ ነዉ
ስንተሻሽ የምንዉለዉ ...ዛሬ እንደ ትናንት ክፉነቱን አዉጆ
የሚመጣ ክፉ የለም። ሳያስብና ሳያቅድ የሚሳሳትም ያለ
አይመስለኝም።... ምድር ያልተዘራባትን አብቀለንባታል።
...የክፋት ሳይንሳችን እሷን እንኳ ከማታለል አልተመለሰም።
ማርነትን ከፊታችን አጥልቀን የምንኖር ልበ-እሬቶች ነን።
...ቢያንስ እኔ እንደዛ ነኝ።...አእምሮየ ወደኋላ እየመለሰ
የእህቶቼን በደል የኔን ደግሞ ቻይነት ሊያሳየኝ ቢሞክርም እኔ
ግን እላለኹ "ከእኔና ከ'ነሱ ማነዉ ክፉ?"...መቅናታቼዉን
በግልፅ ያወጁ እነሱ ወይስ እየሳቅኩ ኹሌም እነሱን ልበልጥ
እጋጋጥ የነበርኩ እኔ??
203
| ናትናኤል ዳኛው
ከስህተተታቼዉ ተመልሰዉ እህት የኾኑልኝ እነሱ ወይስ
ወይስ ዘወትር በዉስጤ ዝናየን ብለዉ ከበቡኝ እያልኩ ለገዛ
ልቤ ትዕቤትን እሰብክ የነበርኩ እኔ?
እነሱ ጋ ግን ያለኹት ለኹሉም ፈገግ ከማለት ዉጭ ምላሽ
የሌለኝ...አንደበቴ የክፋት ቃላትን ያልተለማመደ...አትለወጧ
ብፅዕት ነኝ። ያ ኹልጊዜ ራሳቼዉን በዳይ አድርገዉ እየወቀሱ
እንዲኖሩ አመቻቻቼዉ...ፍቅራቼዉ ማቀማጠላቼዉ ሞቆኜ
ነበር...ሃሜቴ በዉስጤ ነዉ።...ለዝች ልጄ የፍቅር አክሊል
እንደኾንኩ ልሰብካት እጥር ነበር...ክፍሏን ስላዘመንኩ
ከባቢዋን ከሀገሯ የአኗኗር ኹኔታ ስላራቅኩ በቁስ
ስላቀማጠልኳት...በልቧ የምታቆየኝ ይመስለኝ ነበር...የእኔና
የእሷ የልጅነት ዉል ያለዉ በጡቴ ወተት በኩል ነበር። የእናትና
የልጅነት ምስጢር እጄን ይዛ መዳኋ ነበር። ለመቆም
የሚዉተረተር እግሯን የተከተልኩ "ወፌ ቆመች" ማለቱ...
ስትወድቅ "እኔን" ብሎ መርበትበት ነበር እናትነት።
ቶሎ ቶሎ ይደክመኛል...የበረታ ሳል ያጣድፈኛል። አዉቅ
ነበር በባሌ እጣ እንደማልፍ...ስጠብቅ ከነበረዉ ጊዜ ዘግይቶ
ነዉ ምልክቱ የመጣዉ።...አሉኝ የምላቼዉን ንብረቶቼን ቤቱን
ሳይቀር ጠበቃ ቀጥሬ በልጄ ስም አዙሪያለኹ።...ሞትን ቆሜ
አልጠብቀዉም። መቼ እንደሚመጣ ባላዉቅም ቃሉን
የማያብል ፍጡር የማዉቀዉ እሱን ብቻ ነዉ። እስከዛዉ ግን
ስህተቶቼን በማረም ልቀድመዉ ፈለኩ።...ልጄን፣እናትና
እህቶቼን ቤቴ ቀጥሪያቼዉ እስኪመጡ እየጠበቅኩ ነዉ።
204
ወደ ራስ | ናትናኤል ዳኛው
የሞት ዜናየን ወደ ማይሰሙበት ገዳም 'ርቄ መጓዝን
መርጫለኹ።... ከእንግዲህ በክፋት መኖርን ከጠየፍኩ በዓለም
መኖርን አልመርጥም።...የራሴንም ኾነ የባሌን ስህተት
በእንባየ አጥባለኹ። ቅድስና አይደለም መሻቴ...እድፌን
ማስለቀቅ እንጂ።
"ኹለተኛዉ ህይወቴ ለቀሪዉ ዘመኔ የልደት ቀን ኾኖ
ይጀምራል።" ፊትዝሮይ
205
| ናትናኤል ዳኛው
"The blossom has not opened yet; only the wind
seighing by it."
R. Tagore
206
Download