የለውጥ ሥራ አመራር ስልጠና ደንብ እና ግዴታዎች (Terms of Reference) መግቢያ:- የለውጥና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤትን ተቋማዊ አሠራር ከመልካም አስተዳደር ጉድለት የጸዳ፣ ውጤታማና ቁጥብ ይሆን ዘንድ እንከን ያለባቸውን የአሠራር ሂደቶች በመፈተሽ በተለዋጭ ዘይቤ እንዲተኩ የማስደረግ አላማ ነው መነሻው። ስለሆነም ይህን መሠረታዊ አላማውን እውን ማድረግ ይችል ዘንድ ወቅታዊና ታዳሽ የእውቀትና ክህሎት ማዳበሪያ፥ በተለይ የለውጥ ሥራ አመራር ስልጠና በሥራ ክፍሉ ላሉ ባለሙያዎች ማስፈለጉ ታምኖበታል። የሥልጠናው አላማ፦ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤት ወቅታዊ እውቀትንና ክህሎትን በመጠቀም ተቋማዊ ለውጥንና መልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በውጤታማነት ለማከናወን ይቻል ዘንድ በሥራ ክፍሉ ባሉ ባለሙያዎች የስልጠናው ተፈላጊነት ታምኖበታል። የሥልጠናው ወሰን፦ ስልጠናው የሚካሄድበት ቦታ፦______________________________________ የሠልጣኝ ባለሙያዎች ብዛት፦ ____________________________________ የስልጠናው ቆይታ ጊዜ፦__________________________________________ በአሠልጣኝ የሚቀርቡ የስልጠና ቁሳቁሶች፦____________________________ በጀት ተግባር የስልጠናው አይነት ትራንስፖርት የስልጠና አቅርቦቶች የስልጠና ሰነድ አቅርቦት ሌሎች ተጨማሪ ወጪዎች ጠቅላላ ወጪዎች ድምር መግለጫ የሰልጣኝ ብዛት የነጠላ ዋጋ ጥቅል ዋጋ