22 Mar 2019, 11:00 p.m. ሞት የአራዳ ልጅ 4 ዝናው በአለም ተሰማ የ2011 ዓ.ም አጿማትን እንደሚከተለው እንገጻለን። 5500+2011=7511ዓ.ዓለምን ለ14 ዐብይ ቀመር 532 ጊዜ ሰጠን 63 ይተርፋል። ይሕን ለንዑስ ቀመር 19*3=57 ቀሪ 6 ይሆናል። ለዘመን 1 ይተወዋል 6-1=5 ይመጣል። አበቅቴ 11*5=55-30=25። መጥቅ 19*5=95-3*30=5። መጥቅ ከ14 በታች ስለሆነ በጥቅምት 5 ሰኞ ይውላል። የሰኞ ተውሳክ 6 ነው። 6+5=11 መባጃ ሀመር ይባላል። ጾመ ነነዌ ይካቲት 11። በዓተ ፆም 14+11=25(ይካቲት); ደ/ዘይት 11+11=22(መጋቢት); ሆሳዕና 2+11=13(ሚያዚያ); ስቅለት 7+11=18(ሚያዚያ); ትንሳኤ 9+11=20(ሚያዚያ); ርክበ ካህናት 3+11=14(ግንቦት); እርገት 18+11=29(ግንቦት) ጰራቅሊጦስ 28+11=39-30=9(ሰኔ); ፆመ ሐዋርያት 29+11=40-30=10(ሰኔ);ፆመ ድህነት 1+11=12(ሰኔ) ይሆናል። ሁሉም ምዕመን ጊዜውን ጠብቀው መፆም እንዳለባቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች። #Share the light ገምሃልያ ....ክፍል 1 .....; እንደወትሮዬ ሁልግዜ ቅዳሜ ወይ እሁድ ከሰአት እምሰራው ስራ ከሌለኝ ከመፅሃፍ መደርደሪያዬ ላይ ውድ ጓደኞቼ በስጦታ መልክ ከሰጡኝ መፅሃፎች አንዱን አነሳና ቦሌ ማተሚያ አከባቢ ትንሽ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኝ ደስ እሚል በዛፎች የተሞላ ፓርክ አለ። ብዙ ግዜ እዛ ሄጄ መፅሃፍ ማንበብ እወዳለው። ዛሬ እለቱ ቅዳሜ ነው እዛ ሄጄ ለማንበብ የመረጥኩት ብርቅርቃ እሚለውን መፅሃፍ ነበር አሜን እምትባል ጓደኛዬ የሰጠችኝ መፅሃፍ ነው እሚገርመው ብርቅርቅታን የመሰለ አሪፍ መፅሃፍ እስከዛሬ አላነበብኩትም ነበር ከመደርደሪያው ላይ ስቤ ጠቅለል አድርጌው ይዤ ወጣው። መንገዴን ከቦሌ ድልድይ ጫፍ ወደ ስታዲየምና ሚክሲኮ በሚወስደው መስመር ታክሲ ተሳፍሬ ወደ ማተሚያ ቤት ሄድኩ። ማተሚያ ቤት ጋር ስደርስ ወርጄ በእግር መንገድ ወደ ውስጥ ወደፓርኩ ገሰገስኩ መንገዱ ቁልቁለት ስለሆነ ሳልወድ በግድ ያሯሩጠኛል። እዛ ሰፈር ያሉት ፍየሎች ሁሌም ሳያቸው ያስቁኛል በጣም ትልልቅ ጥጃ ነው እሚያክሉት ምን እንደሚቀልቧቸው እንጃላቸው። እነሱን በአይበሉባ እየታዘብኩ ፓርኩ ጋር ደረስኩ ለመቀመጥ ሁለት ብር ከከፈልኩ በኃላ ሁሌም ወደምቀመጥባት ሰላማዊ ቦታ አቀናው ቦታዋ ጥግ ላይ ሁና ከሁሉም እይታ ገንጠል ብላ ጀርባዋን ሰጥታ ያለች ቦታ ናት ከፊትለፊቷ እሚያምር፤ ትንሽ ራቅ ብሎ የሚገኝ የሙዝ እና የበቆሎ እርሻ ማሳ ይታያል። እናም ወደቦታዬ እየሄድኩ በልቤ ሌላ ሰው እንዳይቀመጥባት እየቋጠርኩ ሄድኩ ቦታዬ ላይ ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ ከጀርባ ከሚታዩት ክብ መቀመጫዎች ላይ አንዲት በግምት በእኔ እድሜ አከባቢ እምትሆን ሴት ሲጋራ እያጨሰች አየኃት ለሽራፊ ሰከንዶች ቆም ብዬ ካየኃት በኃላ ወደቦታዬ ሄድኩ ማንም አልተቀመጠባትም ደስ አለኝ። በሸክላ ጡብ እና በሲሚንቶ የተሰራችውን መቀመጫ በሶፍት ጠረግኩና ተቀመጥኩ ቦታዋ ደስ ትላለች ሙሽሮች ሲጋቡ ለመድረክነት የሚጠቀሙባት ባለግርማሞገስ የድንጋይ ዙፋን ትመስላለች መደገፊያዋ ረጅም ስለሆነ ካልቆምኩ በስተቀር ከኃላዬ ምን እንዳለ አይታይም ያውም በኔ መለሎ ቁመት። ቦታዬ ላይ ተረጋግቼ ከተቀመጥኩ በኃላ መፅሃፌን ከፈትኩና ሀ ብዬ ማንበብ ጀመርኩ.... ግን ቅድም ሲጋራ እያጨሰች የነበረችው ሴት በአእምሮዬ ተመላለሰች ፊቷ የተከፋ ይመስላል ሲጋራውን በብሽቀት እየማገች ጭሱን ሽቅብ ትለቀዋለች ሄጄ ምን እንደሆነች ልጠይቃት አሰብኩና ምን አገባኝ ብዬ መልሼ ተውኩት መፅሃፌን ማንበብ ቀጠልኩ። ግን የልጅቷ ሁኔታ አእምሮዬ ውስጥ እየተመላለሰ ሰላም ነሳኝ በመጨረሻም ሄጄ ምን እንደሆነች ልጠይቃት ወሰንኩና መፅሃፉን ከድኜ አስቀመጥኩት። ወደሷ ሄድኩ እሷ የተቀመጠችበት ቦታ ከኔ ጀርባ ሆኖ ቅርብ ርቀት ላይ ነው ሄጄ ሰላም አልኳት የደረቀ ሰላምታ ሰጠችኝ። ሲጋራ ማጨስ እችላለው አልኳት ገልመጥ እያለች በእጇ መሃል የሚጤሰውን ሲጋራ ሰጠችኝ ተቀበልኳትና በጣቶቼ መሃል አድርጌ ጭሱ ሲበን ትንሽ ተከዝ ብዬ አየሁት በጎን በኩል የሸክላው ጡብ ወንበር መደገፊያ ላይ ወጥቼ እግሬን ደግሞ መቀመጫው ላይ አድርጌ ተቀመጥኩ። እሷን ምንም ሳልናገራት ሲጋራውን ዝም ማየት ቀጠልኩ ውስጡ የሷን ጭንቀት ይሁን ሃሳብ ይነግረኝ ይመስል ከጭሱ ውስጥ መልስ ፍለጋ ገባው። ልጅቷ ከሁኔታዋ ማውራት እምትፈልግ አትመስልም እንዲያ ባይሆን ኖሮ እንደዚ አይነት በብቸኝነት ሰላም እሚሰጥ ቦታ ባልመጣች ነበር። እሷ ማውራት ባትፈልግም እኔ ግን ማውራት ነበረብኝ። ሲጋራውን ትንሽ ካየሁት በኃላ ወደታች ዘቀዘቅኩት እሳቱ ሲጋራውን በፍጥነት ወደላይ ይበላው ጀመር ጭሱ ወደላይ ይበናል አመዱ ደግሞ ወደመሬት ይወድቃል። ልጅቷ እማደርግውን ዝምብላ እያየችኝ እንደሆነ ሳውቅ ምን ይታይሻል አልኳት ሲጋራ አለችኝ። እኔ ግን ህይወት ይታየኛል ምስቅልቅሉ የወጣ ህይወት ከላይ ወደታች የተገለበጠች ህይወት አመድ እና ጭስ የሆነ ህይወት እሳት የሆነ ፈተና። ህይወት እንደሲጋራው ቀጥ ተደርጋ በምቾት ስትያዝ እኛ የህይወትን ትርጉም አናውቅም እሳቱ ቀስ እያለ ሲጋራውን ይጨርሰዋል ነገር ግን ሲጋራው ሲገለበጥ መከራ ሲበዛብን እሳቱ ቶሎ ሲጋራውን ይበላዋል በመከራ ውስጥ ሆነን የህይወት ትርጉም ይገባናል ህይወታችችንን አጣጥመን ቶሎ ቶሎ እንኖራታለን እዚች ምድር ላይ ያለን ግዜ ውስን ስለሆነ ሲጋራው ወደታች ቢዘቀዘቅም ጭሱ ግን ወደላይ ነበር የሚጨሰው ፈተናውን የሚያልፍ ሰውም እንደዛ ነው ግን...... አልኳትና ዝም አልኩ ሲጋራውን ለልጅቷ መለስኩላት እና ተነስቼ ወደቦታዬ ለመመለስ ስዘጋጅ ግን ምን አለችኝ ? ይቀጥላል በፌደራል መንግሥት ከወልዲያ -ወረታ-ፍኖተ ሰላም እንዲሁም ከወረታ- መተማ-ሱዳን ለመዘርጋት የታቀዱ የባቡር መሥመር ፕሮጀክቶች በፍጥነት ሊጀመሩ ይገባል”ዶ/ር አምባቸው መኮነን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር:: በአማራ ክልል ይገነባሉ ተብሎ በፌደራል መንግሥት የታቀዱ የባቡር መሥመር ፕሮጀከቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ጠየቁ። በደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ የሚገነባውን የደረቅ ወደብና ተርሚናል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ ዶክተር አምባቸው በዚሁ ወቅት እንዳሉት ባቡር ለአገሪቱ የሚያበረክተውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከግምት በማስገባት የተያዘው ዕቅድ ወደ ተግባር መግባት ይኖርበታል። መሥመሮቹ ከወልዲያ -ወረታ-ፍኖተ ሰላም እንዲሁም ከወረታ- መተማ-ሱዳን ለመዘርጋት የታቀዱ እንደሆኑም አስታውሰዋል፡፡ በዕቅድ ከተያዙት መሥመሮች አንዱም ሥራ ባለመጀመሩ በሕዝቡ ዘንድ ቅሬታ መፍጠሩን ዶክተር አምባቸው ገልጸዋል። በወረታ ከተማ በ20 ሄክታር መሬት የሚያርፈው የደረቅ ወደብና ተርሚናል ግንባታም አስፈላጊው የመሠረተ ልማት አቅርቦት ካልተሰራለት ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ከ420 ሺህ በላይ ሕጋዊ ነጋዴዎች እንዳሉ ያስረዱት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ነጋዴዎቹ ተገቢ የመሠረተ ልማት ባለመኖሩ ወደ ክልሉ የሚያስመጡትንም ሆነ ወደ ውጪ የሚልኩትን ምርት በመንገድ መሠረተ ልማት እጥረት አለመሟላት ችግር እንደሚያጋጥመው ተናግረዋል። ይህም ተገቢ ላልሆነ የጊዜና የገንዘብ ወጪ እንደሚዳርጋቸው ዶክተር አምባቸው አስረድተዋል። ክልሉ ትርፍ አምራችና የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላለው የፌዴራል መንግሥት ለክልሉ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። በመንግሥት ላይ ሙሉ ተስፋ ያለው የክልሉ ሕዝብ ይገነባሉ ተብለው ግንባታውን በጉጉት እየተጠባበቀ ነው ብለዋል። የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በበኩላቸው በክልሉ ለመገንባት የታቀዱትን የባቡር መሥመር ዝርጋታ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። ለዚህም የወረታ-ጎንደር-መተማ 504 ኪሎ ሜትር፣በሱዳን በኩል ጋላባት፣ ገዳሪፍ፣ከሰላና ሃያ ሱዳን ወደብ የሚዘረጋ ደረጃውን የጠበቀ የባቡር መሥመር ፕሮጀክት ግንባታ እውን ለማድረግ ከሱዳን መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል። ለፕሮጀክቱ መሳካት አስተዋጽኦ የሚያደርግ የአዋጪነት ጥናት በአፍሪካ ልማት ባንክ አማካኝነት በቅርቡ እንደሚጀመርም ተናግረዋል። የወረታ ደረቅ ወደብ ግንባታም ይህንን የባቡር መሥመር ግንባታ ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሚገነባ ገልጸዋል። የወረታ የደረቅ ወደብና ተርሚናል ግንባታ በ20 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን፣ ለመጀመሪያው ምዕራፍ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ኢ.ፕ.ድ "ወይኔ ልጅነቴ" በአጭር አስቀረዋት ወይኔ ልጅነቴን ስበር እንዳሞራ ላይሞላ ስኳትን ላልሰራ ልሰራ የምድራዊ ቤቴን ላይማላ ልሞላ ስጋዊ ምኞቴን ሳላድግ አድጌ ሳስብ ወደፊቱን ለስጋየ እየሮጥኩ ሳላስባት ነፍሴን እኖራለው እያልኩ ሳላቀው መሞቴን በአጭር አስቀረዋት ወይኔ ልጅነቴን፣ እባክህ አንተ ሞት መልሰኝ አንድ አፍታ ያለምኩት ህልም አለኝ ምንም ያልተፈታ መልሰኝ እባክህ ተናግሬ ልምጣ አልተሰናበትኩም ጠዋት ከቤት ስወጣ ለእናቴ ልናገር እሽ ሌላው ይቅር ለአባቴም ይወቀው መሄዴ ይነገር ላልመጣ እንደሄድኩኝ ከላይኛው ሀገር በእሳት መቃጠሌን እንደአማራ ስበር እንደተቋረጠ ልጅነቴ በአጭር፣ የልጅነት እድሜየን በተስፋ ሞልቻት የነገን ብርሀን ስጠብቅ በጉጉት ዘመድ ጎርቤትም ሲያደንቁኝ በኩራት ክብር ሆኖላቸው የእኔ ፓይለትነት እኔም ሳልረዳው እነሱም ሳያቁት እንዲህ እንደወጣው ድንገት እንደምሞት በርሬ እንዳሞራ ተቃጠልኩኝ በእሳት ምንም ስንቅ ሳልይዝ እዛ ላይ ላለው ቤት ይህ ሆነ ውጤቱ የእኔ ፓይለትነት ሮጠው ሳይጠግቡ ልጅነትን መቅጨት ወይኔ ልጅነቴን በአጭር አስቀረውት። ስሙኝ ወገኖቸ ትንሽ ልንገራችው ወረፋችው ሳይደርስ በምድር ያላችው ትናት በእኔ መሞት እጅግ ያዘናችው አትዘኑ ለእኔ እኔ አዘንኩላችው ዘር ስትቆጥሩ ነበር ትናት ያየዋችው ብሄር ሀይማኖትን የከፋፈላችው ቀድሜ ስለሄድኩ እኔ ልንገራችው ሁሉም በወረፋ ተፅፏል ስማችው ጠባብና ሰፊ ተሰርቷል ቤታችው ይታደላችዋል እንደየ ስራችው የሚያሳዝን አለ ደግሞ ልንገራችው እልፍ አላፍ አላችው መግቢያ የሌላችው ልክ እንደኔ ስጋ ሚቃጠል ነፍሳችው እጅግ አለቀስኩኝ እኔ አዘንኩላችው ከፍቶ ስላየውት የመጨረሻችው። ከተመለሳችው ግን ይህን ሰምታችው አንድ ከሆናችው ፍቅርን ሰብካችው ዘርና ብሄርን ንቃችው ትታችው በአንድነት ለአንድነት ከተባበራችው እውነት ነው ምላችው ይሰራል ቤታችው ለእናንተ ነው ደሙን ያፈሰሰላችው ሀጥያትን ደምስሶ ፅድቅ የሚያወርሳችው ከልብ ይቅር የሚል ደግ አባት አላችው ትናት በአደጋው የተለየን ወንድማችን መልክት መታሰቢያነቱ ለሁሉም በአደጋው ላጣናቸው ወገኖቻችን በሙሉ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን። n የዐቢይ ጾም ሦስተኛው ሳምንት ምኩራብ ይባላል! #ምኩራብ፦ ማለት ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያኸል ታላቅ ሕንጻ ማለት ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ወይም ቤተመቅደስ ማለት ይሆናል፡፡ ዐቢይ ፍሬ ቃሉ ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በትምህርቱ፣ ድውያነ ነፍስን በታምራቱ ሲፈውስ በምኩራብ እየተገኘ የፈጸመውን የማዳን ሥራ በኀሊና እያሳሰበ የሚያስተምር ሦስተኛ ሳምንት ነው፡፡ ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡ ትርጉም:- ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው፡)፡ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነነቁ የእለቱ መልክታትና ምሥባክ #የካቲት_18 ፫ተኛ መዝሙር ዘምኵራብ ቦአ ኢየሱስ ምኵራበ ይሁዳ፡፡ #ዘቅዳሴ #ቆላስ_2:16-ፍጻሜ፡ዑቁ እንከ አልቦ ዘይግእዘክሙ"እንግዲህ በመብልም ቢሆን በመጠጥም ቢሆን በልዩ ልዩ በዓላትም ቢሆን በመባቻም ቢሆን በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡........................................................ .......................ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለውም፡፡" #ያዕቆብ_2:14-ፍጻሜ፡ምንተ ይበቁዕ አኃዊነ"ወንድሞቻችን ሆይ እምነት አለኝ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል?.................................................... .......................ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ አንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው፡፡" #የሐዋ_ሥራ_10:1-9፡ወሀሎ ፩ ብእሲ በሀገረ ቂሣርያ"በቂሳርያም ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ................................................................. ........................ነገሩንም ሁሉ ነግሮ ወደ ኢዮጴ ከተማ ላካቸው፡፡" #ምስባክ እስመ ቅንአተ ቤትከ በልዐኒ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡ #ትርጉም የቤትህ ቅናት በልታኛለችና የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና ነፍሴን በጾም አስመረርኋት፡፡ #መዝ_68:9-10 #ወንጌል #ዮሐንስ_2:12-ፍጻሜ፡ወእምድኅረ ዝንቱ ወረዱ ቅፍርናሆም"ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ.................... ................................................የሰውንም ግብሩን ሊነግሩት አይሻም እርሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና፡፡" #ቅዳሴ፡ዘእግዚእነ፡፡(ነአኵተከ) ወሥብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መሥቀሉ ክቡር